FiFi Finance አማርኛ

ትርጉሞች:

ፋይ ፋይ ፋይናንስ ብለን በሰየምነው ድረ ገጽ በዋነኛነት ዓላማ ያደረግነው በዓለም ዙሪያ በጠቅላላ ፋይናንስ ነክ እውቀቶችና ግንዛቤዎች ማጎልበትን ነው። በተቻለን መጠን ሁሉ ምርጥ መገልገያዎችን እና የፋይናንስ መረጃዎችን ለሰዎች በማቅረብ ፋይናንስ ነክ ህየወታቸውን ቀለል ባለ ሁኔታ እንዲመሩ ለማገዝ እንፈልጋለን። ብዙ ሰዎች በተለይም የፋይናንስ ትምህርትን ፈጽሞ አግኝተው ለማያውቁቱ ጥሩ የሆኑ የፋይናንስ ውሳኔዎችን መስጠት ቀላል አይሆንላቸውም። እኛ እነዚህ አይነቶቹ ሰዎች ጋር ለመድረስና ለማገዝ እንሻለን።

ስለፋይናንስ ጉዳዮች ምርጥና ትክክለኛ መረጃዎችን በማግኘት ህይወትዎን ያሻሽሉ።

እኛ በዓለም ዙሪያ በጠቅላላ ይህንን ጥራት ባላቸው የፋይናንስ መረጃዎች የምናከናውነው ለተጠቃሚዎችም ሆነ ለአነስተኛ እና ጥቃቅን የንግድ ስራዎች በፋይናንስ ውጤቶች መካከል ጥሩ ማነፃፀሪያዎችን በማቅረብ ነው። ሰዎች ለሚከተሉት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እንዲችሉ እናግዛቸዋለን: ገንዘብን እንዴት አድርጌ መያዝ ወይም ማስተዳደርና መቆጠብ እችላለሁ? የትኛው ብድር አቅራቢ የበለጠ ጠቃሚና አዋጭ ነው፤ የትኞቹ አይነቶች ኢንቨስትመንቶችን ወይም የባንክ ሂሳቦች (አካውንቶች) ማግኘት ወይም መሰረዝ አለብኝ፣ በምንስ ምክንያት? ለፕሮጀክቴ፣ ለንግድ ስራዬ መነሻ ወይም ለእኔ አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ትክክለኛውን የገንዘብ ድጋፍ ከየት አገኛለሁ?

የፋይ ፋይ ተልዕኮ: ፋይናንስ ነክ ጉዳዮች ሁሉ ለእያንዳንዱ ሰው እንዲሰራ በማድረግ የፋይናንስ እውቀት እንዲሻሻልና እንዲጎለብት ማድረግ ነው።

ፋይ ፋይ አፍሪካ

ከዕለት በዕለት ትዝብታችን እንደምንታዘበው፣ አብዛኞቹ የፋይናንስ ነክ ጉዳዮች ድረ ገጾች ዋነኛ ትኩረቶቻቸው በርካታ የገቢ አቅም ባላቸው ገበያዎች ላይ ነው፤ እኛ ግን ነገሮችን ወደተለየ ደረጃ በመውሰድ እንደ አፍሪካ እና ላቲን አሜሪካ ባሉ አዳጊ ገበያዎች ላይ ትኩረት ማድረግን መርጠናል። በአፍሪካ በተለይ፣ ለሰዎች ፋይናንስ ነክ ጉዳዮችን በመጀመሪያ ወይም እናት ቋንቋቸው እንዲያገኙ ለማድረግና ፋይናንስ ነክ ችግሮቻቸውን በተመለከተ ለማገዝ የሚያስችል እምቅ ሀብት አለ።
በዚህም ምክንያት ነው እኛ የድረ ገጽ መግቢያችን ወይም ፖርታላችን እንደ ኬንያ፣ ዛምቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ታንዛንያ፣ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ ያሉ አገራት ህዝቦችን ኢላማ ማድረግ የወደድነው። ይህን በእንግሊዘኛ፣ በፖርቹጊዝ እና በፈረንሳይኛ ቋንቋዎች ብናከናውንም እንደ ስዋህሊኛ እና አማርኛ ባሉ አፍሪካዊ ቋንቋዎች ጅማሮዋችንን አድርገናል። እነዚህ ቋንቋዎች በተለያዩ የአፍሪካ ክፍሎች ይነገራሉ። ከስዋህሊኛ እና አማርኛ በተጨማሪም፣ እንደ ዩሩባ፣ ኢግቦ፣ ዙሉ፣ ዎሎፍ፣ ቤምባ፣ ወዘተ ባሉ አፍሪካዊ ቋንቋዎች ጥራት ያላቸውን መረጃዎች ለማቅረብም አቅደናል።

የፋይናንስ ነክ ጉዳይ ርዕሶች

በመጀመሪያ ደረጃ የእኛ ትኩረት እንደ ብድሮች፣ የባንክ ሂሳቦች ወይም አካውንቶች፣ የመድህን ዋስትና እና መዋዕለ ነዋይ ወይም ኢንቨስትመንት ባሉ መደበኛ የፋይናንስ ርዕሶች ላይ ነው። ከዚህም አንድ ደረጃ ከፍ ብሎ በመሄድም የፋይናንስ ስራዎችን ስለመጀመር፣ የአቻ ለአቻ ንግድ ስራ፣ እና ቢትኮይንን የመሰሉ አዳዲስ ርዕሶችን ለመሸፈን እንሻለን።
በተጨማሪም፣ አማራጭ ፋይናንስ ማግኛዎች፣ ስጦታ፣ ምጣኔ ሀብታዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ልማት፣ ሁሉን አቀፍ የጤና እንክብካቤ እና በዓለም ዙሪያ የመሰረታዊ ገቢ ጉዳዮችን ወደመሳሰሉ ርዕሶችም መግባት እንሻለን።

ፋይ ፋይ መፍትሄ ሊያገኝለት የሚሻው ችግር ምንድን ነው?

እኛ ይበልጥ ማተኮር የምንሻው መሰረታዊ ካልሆኑት ይልቅ ለሰዎች ኑሮ በጣም አስፈላጊና መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ነው። አንድ ምሳሌ ለመስጠት ያህል፣ አንድ ሰው “በበይነ መረብ ቀጥታ ግንኙነት ወይም ኦንላይን እንዴት ገንዘብ እንደሚሰራ” ማወቅ ቢፈልግ፣ እኛ በአንድ ሰው ህይወት ላይ ልዩነት ሊያመጡ የሚችሉ መፍትሄዎችን እንጠቁመዋለን። የዕለታዊ ንግድ ስቶኮች፣ የውጭ ምንዛሪ ግብይት፣ እና ውርርድ የመሳሰሉ መፍትሄዎች ህይወታችሁን ለማሻሻል ከፈለጋችሁ ጠቃሚዎች ወይም አጋዦች አይደሉም። እኛ እነዚህ ፈጣን ገቢ ማግኛዎች ጭንቀትን እንደሚጨምሩ እንጂ እንደ ዕሴት ጨማሪ አድርገን አናስባቸውም።
ሰዎች እንዲያውቁልን የምንሻው ዋነኛ ነጥብ ሰዎች ስኬታማነትን በእጃቸው ሊያስገቡ የሚችሉት በህይወታቸው ላይ ዕሴትን የሚጨምሩ መፍትሄዎች ላይ ሲያተኩሩ መሆኑን ነው። ይህ በአንጻራዊነት ቀላል የሆኑ እንደ አፕወርክ ወይም ፊቨር ያሉ ኦንላይን ስራና ሰራተኛ አገናኞች፣ አዲስ ክህሎትን መማር፣ ድረ ገጽ መክፈት ወይም መጀመር፣ ነፃ ስራ ፈጣሪነት እና የመሳሰሉ ነገሮችን ይጨምራል። የእኛ ዓላማ እነዚህ መፍትሄዎች ላይ በማተኮር ለሰዎች አዳዲስ ሃሳቦችና ሊያስተውሏቸው የሚገቡ ነገሮችን መስጠት ነው።
ለሰዎች የሚቻለውን ምርጥ የፋይናንስ ምክር ለመስጠት እንሻለን። የምንሰጠውም ምክር ሰዎች ራሳቸውን ከጭንቀት ገለል አድርገው ህይወታቸውን ወደፊት እንዲያራምዱ የሚረዳቸው ነው።

ፋይ ፋይ እንዴት ነው መፍትሄ የሚሰጠው?

እኛ የምንሰራው ስንሰራው ጥሩ የሆንበትን ነው: ሰዎች ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች በመረጃ የተደገፉ ምላሾችን የያዘ በመረጃ ማፈላለጊያ ዘዴዎችም ላይ በክፍተኛ ተስማሚነቱ ደረጃ ያለው አነስተኛ ግን ደግሞ ማራኪና ሳቢ ድረ ገጽን መገንባት። እዚህ ላይ አንድ ሁለት የሆኑ መሪ መርሆዎች አሉን:
ሰዎች ላሏቸው ፋይናንስ ነክ ጥያቄዎች ምላሾችን እንዲገኙ ማገዝ ለእኛ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው።
እነዚህ ምላሾች በታማኝነትና መሰጠት አለባቸው። ምላሾቹ በሀቅ ላይ የተመሰረቱ እንጂ አሳሳች መሆን አይገባቸውም።
በምናከናውናቸው ስራዎች ራሳችንን ዘወትር ባማሻሻልና በመፈተን ለበለጠ ስራ መትጋትን እንሻለን።
ፋይ ፋይ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
የፋይ ፋይ ድረ ገጽን በባለቤትነት ለመያዝና ለማስተዳደር የገዛነው እ.ኤ.አ. በመጋቢት ወር 2019 ዓ.ም. ነው። ከጥር 2020 ጀምሮ በአምስቱ አህጉራት ባሉ አርታኢዎች ወይም ኤዲተሮች በእንግሊዘኛ፣ በጀርመንኛ፣ በስታኒሽ፣ በብራዚል እና ስዋሂሊ ቋንቋዎች የተጻፉ ከ 1000 በላይ ገጾች እና ቁጥራቸውም እጅጉን እየጨመረ የመጣ ጎብኝዎች አሉን። ትክክለኛውን እውቀት የያዙ ምርጥ ጸሀፊዎችን በመምረጥ ትኩረታችንን በይዘት ጥራት ላይ እናደርጋለን። በፋይናንስ፣ በእውቀት፣ በጥበብ እንዲሁም በሳይንስ ዘርፎች ሁሉ የአፍሪካን አህጉር እጅግ ከፍተኛ የሆነ የዕድገት እምቅ አቅም እንዳለው አህጉር እንቆጥራዋለን። አህጉሩ ከፈተኛውን ተግዳሮት ቢጋፈጥም የሚያሸልመውን ግዙፍ እምቅ አቅም የያዘ ነው።
ፋይ ፋይ አፍሪካን ለመገንባት በደስታ ያነሳሳንም በተለይ ይኸው እውነታ ነው። ስራችንንም በአፍሪካዊው ቋንቋ በስዋሂሊ ጀምረናል። ለዚሁ ጥረታችንም አንዱ አካል እንዲሆን በማሰብ የወርድፕሬስ መገልገያን ወደ ስዋሂሊ ቋንቋ አስተርጉመናል። ከዊኪፔዲያ ጋር ለማጣጣም በማሰብ የስዋሂሊው ትርጉም ወይም ቨርዥን በክሬቲቭ ኮመንስ ፈቃድ ወይም ላይሰንስ ስር ይገኛል። ሕክምና ነክ ጽሁፎችን ዊኪፔዲያ ላይ ወደ ስዋሂሊ በቀጥታ እንዲተረጉሙ ለባለሞያዎች ክፍያ መፈጸምም ጀምረናል። ይኽን የምናከናውንበት ምክንያት በአፍሪካዊ ቋንቋዎች ይዘቶች እንዲፈጠሩ ወይም እንዲጻፉ የሚያስችል ንቅናቄን ለማነሳሳት ስለምንሻ ነው፤ በመጪዎቹ ዓመታትም በዶዘን በሚቆጠሩ አፍሪካዊ ቋንቋዎች ስራችንን የመጀመር ዓላማም ይዘናል።

የገንዘብስ ጉዳይ?

እኛ ስራችንን መቶ በመቶ (100%) የምናከናውነው በራሳችን ገንዘብ ነው። መጠባበቂያ ገንዘብን ለማከማቸት ያስቻሉንን የድረ ገጽ ሀብቶች ባለፉት ጊዜያት ገንብተናል። አሁን ላይ ደግሞ ይህንን መጠባበቂያችንን ፋይ ፋይ ፋይናንስን ለመገንባት እየተጠቀምንበት ነው። ትኩረታችንን ፋይ ፋይ ላይ በማድረግም ቡድንናችንን በፍጥነት እናሳድጋለን።

ስፍራችን የት ነው?

ኩባንያችን መቀመጫውን ያደረገው ለማስተዳደር እጅጉን በተመቸችው፣ በጣም ዝቅተኛ ቢሮክራሲና የወረቀት ስራ ባለብት ኢስቶኒያ ነው። ስራችንን ከየትኛውም ስፍራ ከመካሄዳችንም ባሻገር ኢላማ ያደረግነውም መላውን ዓለም ነው። ከመስራቾቹ አንዱ በአሁኑ ወቅት በአምስተርዳም፣ ኔዘርላንድ የሚኖር ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ከቤተሰቡ ጋር በአውሮፓ እየተዘዋወረ ይኖራል። አርታኢዎቹ፣ ጸሀፊዎቹ እና ተርጓሚዎቹ በአብዛኛው በአውሮፓና በአፍሪካ ይገኛሉ።