በኦንላይን የጽሁፍ እርማትን (proofreading) በመስራት ገንዘብ ስለማግኘት

ትርጉሞች:
en_USsw

የንግዱ ዓለም እና ቴክኖሎጂ በጊዜ ሂደት እያደጉ በሄዱ መጠን በይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት ትልቁ የስራ ዕድል አቅራቢ ሆኗል። አሁን ላይ ሁሉም ነገር እየሆነ ያለው በኦንላይን ወይም በቀጥታ የበይነ መረብ ግንኙነት ነው፤ ከዚህም ጋር ተያይዞ የሁሉም አይነት የስራ ዕድሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዙ ነው። የመስመር ላይ ስራዎች ተስፋ ሰጭ የስራ እድሎችን በሚፈልጉ በመስመር ላይ ነፃ አውጪዎች ዘንድ ተወዳጅ እየሆኑ ነው። በተማርክበት መስክ ሙያ የምትፈልግ ከሆነ፣ በማረም ሥራ ገንዘብ ማግኘት ትችላለህ።

ይህን ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ያንብቡ፡- Make Money By Proofreading Online

የጽሁፍ እርማት (proofreading) ምንድን ነው?

ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት አስተዋዋቂዎች (ወይም በእንግሊዘኛው promoters የሚባሉት ማለት ነው) እና የንግድ መሪዎች በይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት፣ የስራዎቻቸው ባህሪይ ምንም ይሁን ምን፣ ስራቸውን ለማስተዋወቅ ያለውን ወሳኝነትና አስፈላጊነት ተገንዝበዋል።። ከዚህም ጋር ተያይዞ፣ በኤሌክትሮኒካዊ መላ ራሳቸውን ለሌሎች የማሳየትን ወይም ተደራሽ የማድረግንም አስፈላጊነት ትልቅ ቦታ ሰጥተውታል።

በይነ መረብ ሁሉንም ነገር ለዓለም ክፍት እንዲሆን አድርጓል፤ ሆኖም ግን ብዙ ተመልካች እንዲኖራችሁ ለማድረግ፣ ጥራት ያለው ይዘት (quality content) ማምረት ወይም ማዘጋጀት እጅግ አስፈላጊ ነው። የዚህ ግቡ ደግሞ በጥሩ ሁኔታ ራሳችሁን ተጠቃሽ እንድትሆኑ ማድረግ ነው። በመሆኑም፣ ብዙ የድረ ገጽ ፕሮሞተሮች እና የይዘት አዘጋጆች (ፕሮዲዩሰሮች) ስራቸው በአርታዒዎች ወይም በኤዲተሮች የተፃፉ ጽሑፎችን ማረም የሆነ ወጣት የጽሁፍ እርማት አከናዋኞችን እገዛ ይፈልጋሉ።

የጽሁፍ እርማት ስራ የምንለው እንግዲህ ይህንኑ ነው።

የጽሁፍ እርማት ስራ አከናዋኝ መሆን እንዴት እንደሚቻል

በኦንላይን ልታገኟቸው የምትችሏቸውና የጽሁፍ እርማት ስራ ላይ ብቻ የሚሰሩ (ወይም ስፔሽያላይዝ ያደረጉ) በርካታ ድረ ገጾች አሉ። የጽሁፍ እርማት የሚሰሩ ሰዎችን የሚፈልጉ የድረ ገጽ ፕሮሞተሮች የስራ ሁኔታዎችን፣ የጽሁፎቹን (ቴክስቶቹን) አይነትና ባህሪያት፣ እንዲሁም ለስራው የመደቡትን በጀት ጭምር ዘርዝረው ጥያቄያቸውን የሚለጥፉባቸው ወይም ፖስት የሚያደርጉባቸው ፕላትፎርሞችም አሉ። እዚህ ላይ ግን ኃላፊነቱ ሁሉ የእናንተ ነው። ስራውን ሰርታችሁ ካስረከባችኋቸው በኋላ ተገቢውን ክፍያ ለመክፈል እምቢተኛ የሚሆኑ እምነት አጉዳዮች የሚያጋጥሟችሁ ከሆነ ራሳችሁን አደጋ ውስጥ ልታገኙት ትችላላችሁ።

ስራችሁን የበለጠ ለማስጠበቅ ወይም ዋስትና እንዲኖረው ለማድረግ እያሰባችሁ ከሆነ፣ በዚህ የጽሁፍ እርማት ስራ ላይ ብቻ ባደረጉ (ወይም ስፔሽያላይዝ ባደረጉ) ኩባንያዎች ልትቀጠሩ ትችላላችሁ። እነዚህ በአብዛኛው በጽሁፎች ወይም በአርቲክሎች ላይ የጽሁፍ እርማት የሚሰሩላቸውን ሰዎች የሚፈልጉ የድረ ገጽ ጽሁፍ ኤጀንሲዎች ናቸው።

ፍላጎቱ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ለእዚህ ስራ ለቀረበው ጥሪ ምላሽ መስጠት ይችላሉ። አራሚው ወይም የጽሁፍ እርማት ስራውን የሚሰራው እና ፕሮሞተሩ ወይም አስተዋዋቂው በአገልግሎቱ (ስራውን በተመለከተ) ላይ ግንኙነት በመፍጠር የሚያደርጉት ውይይት ሁለቱም ውገኖች ተጨማሪ መረጃ እንዲኖራቸውና በተቻለ መጠንም ስምምነቱን እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል። በአብዛኛዎቹ ጉዳዮች፣ ስራውን የመሥራት ችሎታዎን ለማረጋገጥ ማረም እና መመለስ ያለባችሁ የሙከራ ጽሑፍ ይላክላችኋል። ይህ ሙከራ ወይም ፈተና ቀጣሪው ወይም ፕሮሞተሩ ክህሎታችሁን እንዲገመግም ያስችለዋል። ከዚህ አኳያ ታዲያ ይህንን ሙያ ለመለማመድ ምን ምን ነገሮች ያስፈልጋችኋል? ይኽን ጥያቄ ለመመለስ የሚከተሉትን ማጤን ጠቃሚ ይሆናል።

ጽሁፍ አራሚ ለመሆን የሚያስፈልጉ ክህሎቶች

ለዚህ ዓይነቱ ሥራ የተለየ ዓይነት ብቃት አያስፈልግም። ነገር ግን፣ እንደ አጥጋቢ የሆነ የእውቀት ደረጃ፣ የመደበኛ ሰዋሰው (grammar) እና የፊደል አጻጻፍ እና የስራ ባህልን የመሳሰሉ አንዳንድ ብቃቶች መኖራቸው አስፈላጊ ነው። በተጨማሪም፣ ንቁ እና ክፍት አእምሮ ሊኖራችሁ ይገባል። በትኩረት የመስራት ብቃት መኖርም ጠቃሚና ተፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ጥሩ ስራ ለመስራት ስራውን የምር ማለትም በሙሉ ፈቃደኝነት መኖር አስፈላጊ ጉዳይ በመሆኑ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ እየዋሉ ያሉትን እንደ MLA፣ APA፣ እና የቺካጎ ማንዋል ኦፍ ስታይል ያሉ የአሰራር ዘይቤ (style) መመሪያዎች ማወቁ ደግሞ ጥሩ ተወዳዳሪ እንድትሆኑ ያስችላችኋል። በእርግጥም አንዳንድ የጽሁፍ እርማት ስራዎች እንደዚህ አይነት እውቀት ሊፈልጉ ይችላሉ።

ጽሁፍ አራሚ መሆን የሚያስገኛቸው ጥቅሞች:

  • ጀማሪዎች እንኳ ቢሆኑም ስህተቶችን ለሚያርሙ ሰዎች ያለው ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነው። በመሆኑም፣ ስራውን ለማግነት ከባድ ወይም አስቸጋሪ አይሆንም።
  • የጽሁፍ እርማት ስራን ለመስራት የሚፈለጉት የመነሻ ወጪዎች እጅግ ዝቅተኛ ናቸው፤ ይኽን ስራ ለመስራት የሚያስፈልጓችሁ ኮምፒውተር እና የበይነ መረብ ወይም የኢንተርኔት ግንኙነት መኖር ብቻ ናቸው።
  • በበርካታ የእርማት ስራ ገጾች (sites) ላይ መመዝገብ የምትችሉ በመሆኑ ሁሌም ስራ ማግኘት ትችላላችሁ።

ጽሁፍ አራሚ መሆን ያለው አሉታዊ ጉዳዮች፡

  • ስራውን ጨርሶ ለማስረከብ የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ የግድ ማክበር አለባችሁ፤ እናንተም በስህተት በአንድ ጊዜ ብዙ ፕሮጀክቶችን የምትስሩ ከሆነ፣ እጅግ ከፍ ያለ ጭንቀት ውስጥ ልትገቡ ትችላላችሁ።
  • የጽሁፍ እርማት ስራ የተቀመጡትን ቀነ ገደቦች ለማክበር ተቆጣጣሪ ለሚሹ (ወይም አብዝተው ቀነ ገደቦችን ለሚጥሱ) ሰዎች አመቺ አይደለም።
  • አንዳንድ የእርማት ስራዎች ከፍ ያለ የትምህርት ደረጃ ያላቸውን ሰዎች ይመርጣሉ።
  • ደንበኞችን የማፈላለጉና ስራውን መስራት እጅግ ጊዜ ወሳጅ ነው።

በኦንላይን የጽሁፍ እርማት ስራን መስራት ምን ያህል ገንዘብ ያስገኛል?

የፍሪላንስ አራሚ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚሰራ የሚወስኑ ብዙ ምክንያቶች አሉ። በአሜሪካ በአብዛኛው የሚሰራበትን እንደ አንድ ምሳሌ እንኳ ብናይ፣ ይኽን ስራ በመስራት በሰዓት ከ12-20 ዶላር መካከል ማግኘት ትችላላችሁ። አንዳንድ ኩባንያዎች ወይም ግለሰቦች ከዚህም ከፍ ያለ ክፍያንም ሊያቀርቡ ይችላሉ። ስራውን እንደ የሙሉ ጊዜ ስራ ስትሰሩ፣ ይህ ሙያው ምንም አይነት ኢንቨስትመንት ስለማያስፈልገው በፍጥነት ብዙ ገንዘብ ማግኘት ትችላላችሁ። ምን ያህል ገንዘብ እንደምታገኙ ሊወስኑ የሚችሉት ሌሎች ነገሮች ደግሞ የሰነዱ ውስብስብነት፣ የእናንተ ልዩ እውቀት (expertise) እና የልምድ ደረጃ ያካትታሉ። የጽሁፍ እርማት ስራዎች በአንድ ቃል ቆጠራ (per word count) ወይም በሰዓት ተወስኖ ክፍያ ሊፈጸምላቸው ይችላሉ።

የኦንላይን የጽሁፍ እርማት ስራዎች የሚገኙባቸው ፕላትፎርሞች

በኦንላይን የጽሁፍ እርማት ስራዎችን በመስራት ገንዘብ የማግኘት ፍላጎቱ እና ተፈላጊ የሆኑ ክህሎቶች ካላችሁ፣ የመጀመሪያ የኦንላይን የጽሁፍ እርማት ስራዎችን ለማግኘት መጠቀም ከምትችሏቸው ምርጥ ፕላትፎርሞች መካከል ጥቅቶቹ የሚከተሉት ናቸው፤

የጽሁፍ እርማት ስራ መሳሪያዎች ወይም መገልገያዎች

ጥሩ አራሚ ለመሆን፣ ስዋሰውን (grammar)፣ የቃላት ፊደሎችን፣ ስርአተ ነጥቦችን (punctuation)፣ ወዘተ በተመለከተ እጅግ በጣም ጥሩ የሆነ እውቀት ሊኖራችሁ ይገባል። የጽሁፍ እርማት ስራውን በፍጥነትና በበለጠ ትክክለኛነት ለመስራት የሚያስፈልጓችሁ መሳሪያዎችና ሀብቶችም አሉ።

ለማረም የመስመር ላይ ሥራ ማጠቃለያ

የጽሁፍ እርማት የህትመት መገናኛ ወይም የህትመት ሜዲያ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያለ አስተማማኝ ስራ ከመሆኑም ባሻገር የይዘት ግብይት (content marketing) ፍላጎትም እስካደገ ድረስ የሚቀጥል ነው። የጽሁፍ እርማት ስራ ሀብታም ሊያደርጋችሁ አይችልም፣ ሆኖም ግን የጽሁፍ አራሚ መሆን እንዴት እንደሚቻል በምታውቁበት ጊዜ ለራሳችሁ ከፍ ያለ ገንዘብ የሚያስገኝላችሁን የጎንዮሽ ተጨማሪ ስራ ልትፈጥሩ ትችላላችሁ።