የኦንላይን ስራዎች ገቢ ለማግኘትና በዲጂታል ኢኮኖሚው ውስጥም ክህሎቶቻችሁን ለማሳደግ ላቅ ያለ ዕድልን ያስገኛሉ። ለአፍሪካ አገራት በሙሉ ጊዜም ሆነ በትርፍ ሰአት ሠራተኞች ከፍተኛ ገቢን የሚያስገኙ በረካታ የኦንላይን ስራዎች አሉ። የኮቪድ – 19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ ለኦንላይን ስራዎች ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። መደበኛ የስራ ቅጥር ውል ሳይኖራቸው ለሚሰሩ አፍሪካዊያን (ፍሪላንሰሮች) የኦንላይን ክፍያ ፕላትፎርሞች መኖር አፍሪካዊያን ፍሪላንሰሮችን ለመቅጠር ያለውን ዕድል ቀላል አድርጎታል። በወረርሽኙ ምክንያት በነበሩት መዘጋጋቶች በርካቶች ስራቸውን ሲያጡ ሌሎች በረካቶች ደግሞ ከቤታቸው ሆነው ስራቸውን ለመስራት ተገደዋል። የሆነ ሆኖ ግን፣ ከኮቪድ – 19 ወረርሽኝ መከሰት አስቀድሞም የኦንላይን ስራዎች አፍሪካ ውስጥ በሺህዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የስራ ዕድሎችን አስገኝተዋል። ከዚህ በታች የተመለከቷቸው አፍሪካ ውስጥ መስራት ከምትችሏቸው የኦንላይን ስራዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።
እነዚህን ስራዎች እንደ የትርፍ ሰዓት ሥራ መጠቀም ይችላሉ. እነሱ የሙሉ ጊዜ ስራዎ መሆን የለባቸውም።
Contents
- 1 በትብብር ወይም በቁርኝት የሚሰራ የንግድ ስራ (Affiliate Marketing)
- 2 መደበኛ የስራ ቅጥር ውል ሳይኖር የሚሰራ ስራ ወይም ፍሪላንሲንግ
- 3 በትዕዛዝ የሚፈጸም የንግድ ስራ እና ኢ – ኮሜርስ ወይም በኤሌክትሮኒክስ መላ የሚካሄድ ንግድ (Drop Shipping and Ecommerce)
- 4 የጽሁፍ ትርጉም ስራ
- 5 ዩቲዩብ (YouTube)
- 6 ድረ ገጽ ላይ ዋጋ ያላቸው መረጃዎችን መጻፍ ወይም ብሎጊንግ (Blogging)
- 7 በፌስቡክ ላይ የሚከናወን ሽያጭ
- 8 ዲጂታል ማርኬቲንግ
- 9 ክፍያ ለማግኘት መጻፍ
- 10 የርቀት ስራ (በትርፍ ጊዜ የሚሰራ ስራ)
በትብብር ወይም በቁርኝት የሚሰራ የንግድ ስራ (Affiliate Marketing)
በትብብር ወይም በቁርኝት የሚሰራ የንግድ ስራ ለበርካታ በመደበኛነት በኦንላይን ጆርናሎች ወይም ድረ ገጾች ላይ ለሚጽፉ (ብሎገሮች) እና በማህበራዊ ሜዲያው ላይ ብዙ ተከታዮች ላሏቸው በርካቶች ገቢን የሚያስገኙ የተለመዱ ዘዴዎች ናቸው። በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራው የንግድ ስራ በኢ – ኮሜርስ (በኤሌክትሮኒክስ መላዎች በሚሰሩ የንግድ ስራዎች) መደብሮች የሚሸጡትን አገልግሎቶች ወይም ምርቶች በማስተዋወቅ በቁርኝት ሊንካችሁ (affiliate link) ባከናወናችሁት እያንዳንዱ ምሪት (ሊድ) ወይም ሽያጭ የኮሚሽን ክፍያን ታገኛላችሁ። በድረ ገጻችሁ ላይ ስለምታስተዋውቅቋቸው አንዳንድ ምርቶች አጠር ያለ መግለጫ የምትሰጡበትን ብሎግ በራሳችሁ መጀመር ትችላላችሁ። ልትጠቀሟቸው ከምትችሉባቸው በትብብር ወይም በቁርኝት የሚሰራ የንግድ ስራ ፕሮግራሞች መካከል አንዳንዶቹ አማዞንን፣ ጁሚያን እንዲሁም ፋይቨርን ይጨምራሉ።
መደበኛ የስራ ቅጥር ውል ሳይኖር የሚሰራ ስራ ወይም ፍሪላንሲንግ
መደበኛ የስራ ቅጥር ውል ሳይኖር የሚሰራ ስራ ወይም ፍሪላንሲንግ በአፍሪካ ውስጥ በጣም ከተለመዱት የኦንላይን ስራዎች መካከል አንዱ ነው። ፍሪላንሲንግ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የግድ የረጅም ጊዜ ቀጣሪ ወይም የስራ ቅጥር ውል ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው የሚሰሩ ሰዎችን የሚያመለክት ነው። አፍሪካ ውስጥ በፍሪላንስ ለመስራት ለመጀመር በእነዚህ የኦንላይን ፍሪላንሲንግ ፕላትፎርሞች ላይ አካውንት መክፈት እነዚህ የመስመር ላይ ነፃ አውጭ መድረኮች
እና ሌሎች በርካታ አፍሪካዊያን ፍሪላንሰሮችን መቀላቀል ይኖርባችኋል።
ፍሪላንሲንግ ፕላትፎርሞች ለአብነትም እንደ አፕወርክ ያሉቱ ባለተሰጥዖዎችንና ቀጣሪዎችን ያገናኛሉ። የምርምር ስራ ወይም በማንበብ ስህተትን የማጥራት (ፕሩፍሪዲንግ) የመስራት ክህሎት ካላችሁ፣ ይህንኑ በፕላትፎርሞች አማካኝነት ለገበያ ልታቀርቡት ትችላላችሁ። ቀልብን ያዝ የሚያደርግና ማራኪ የጨረታ ወይም ቢድ ፕሮፖዛል መጻፍና ሊቀጥሯችሁ ወደሚችሉ ቀጣሪዎች መላክ ትችላላችሁ። ቀጣሪው ፕሮፖዛሉን ከወደደው፣ ሊቀጥራችሁ ይችላል። ከዚያም ክፍያውን ለማግኝት ስራውን ማጠናቀቅና ማስገባት ይኖርባችኋል። ቀጣሪዎች የሚከፍሉት ስራው እነሱን በሚያረካ ሁኔታ ከተሰራ ብቻ ነው።
በስልክ ገንዘብ ማግኘት : በPrizeRebel ላይ የዳሰሳ ጥናቶችን በመውሰድ በስልክ ገንዘብ ማግኘት ትችላላችሁ።
በትዕዛዝ የሚፈጸም የንግድ ስራ እና ኢ – ኮሜርስ ወይም በኤሌክትሮኒክስ መላ የሚካሄድ ንግድ (Drop Shipping and Ecommerce)
በአፍሪካ ውስጥ የኦንላይን ግንኙነት በማድረግ ዕዋዎችንና አገልግሎቶችን በኢ-ኮሜርስ እና በትዕዛዝ በሚፈጸም የንግድ መላ በመሸጥ ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ። በትዕዛዝ የሚፈጸም የንግድ ስራ (Drop Shipping) ዕቃዎችን በመደብር ወይም በመጋዘን ማስቀመጥ ሳያስፈልጋችሁ በችርቻሮ በመሸጥ ገቢን ለማግኘት ሁነኛ ዘዴ ነው። ይህ አሰራር ከሶስተኛ ወገን ምርቶችን መግዛትን እና ለአቅራቢዎች ጭኖ በመላክ የሚከናወን ነው። እንደ አንድ የመጋዘን ባለቤት ምርቱን መያዝ አያስፈልጋችሁም፤ ይልቁንም የምታደርጉት በአቅራቢው ስም ወይም እሱን በመወከል ግብይት መፈጸምና አንድ ደንበኛም ለመግዛት ትዕዛዝ ሲሰጥ ትዕዛዙን ወደ አቅራቢው ማስተላለፍ ነው። አቅራቢውም የታዘዙትን ምርቶች ወደ ደንበኛው ጭኖ ይልካል። ይህን ስራ ለማካሄድ እንደ ሾፒፋይ (Shopify) ያሉ ዓለም አቀፋዊ የንግድ ስራ ኩባንያ ፕላትፎርሞችን መጠቀም ትችላላችሁ።
በትዕዛዝ የሚፈጸም የንግድ ስራ (Drop shipping) ሻጩ የሚሸጡትን ዕቃዎች ወይም ምርቶች በመደብሩ ወይም በመጋዘኑ ሳያስቀምጥ የደንበኛውን ትዕዛዞች የሚቀበልበት የችርቻሮ ንግድ አይነት ነው። እንደ አንድ የአቅርቦት ሰንሰለት አሰራር ወይም አመራር፣ ሻጩ ትዕዛዞቹን እና የጭነት ዝርዝራቸውን ለአምራቹ፣ ለጅምላ ሻጩ፣ ለሌላ ቸርቻሪ፣ ወይም ለምርት ማዕከል (fulfillment house) ያስተላልፋል፤ እነዚህም ዕቃዎቹን ወይም ምርቶቹን በቀጥታ ለደንበኛው ጭነው ይልካሉ።
Qefira ገዥዎችን እና ሻጮችን የሚያገናኝ ትልቁ የኢትዮጵያ የመስመር ላይ ክላሲፍፋይድ መድረክ ነው። በመድረክ ላይ ሁሉንም አይነት ምርቶች መሸጥ ይችላሉ.
የጽሁፍ ትርጉም ስራ
መጣጥፎችን፣ ብሎግ ላይ የሚለጠፉ ጽሁፎችን፣ የምርት መግለጫዎችን፣ ወዘተ በመተርጎም በኦንላይን ገንዘብ መስራት ወይም ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ። በዋነኛው ወይም ኦሪጂናል ቋንቋውም ሆነ በሚተረጎምበት ቋንቋ ላይ ጥሩ የሆነ እውቀት ሊኖራችሁ የግድ ነው። የትርጉም ስራ ወይም ኢንዱስትሪው በጣም ፉክክር የበዛበት ስለሆነ ትዕግስተኛ እና ቁርጠኛ መሆን ይገባችኋል። በኦንላይን የትርጉም ስራ ለመስራት ከፈለጋችሁ ከብዙዎቹ መካከል የሚከተሉትን ጥቂት የኦንላይን ፕላትፎርሞች ማጤን ትችላላችሁ:
ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት የትርጉም ስራ ድረ ገጾች ሌላም፣ የትርጎም ስራዎችን እንደ አፕወርክ ፣ ፋይቨር፣ ጉሩ፣ ፒፕልፐርሀወር እና ፍሪላንሰር በመሳሰሉ አጠቃላይ የፍሪላንሲንግ ፕላትፎርሞች ላይ ማግኘት ትችላላችሁ።
ዩቲዩብ (YouTube)
በዩቲዩብ ቻነል ላይ ይዘቶችን በመጫን ገቢ ማግኝት ትችላላችሁ። ቻነሉ ላይ ለተመልካች ሳቢ የሆኑ ዋጋ ያላቸው የቪዲዮ ይዘቶችን መጫን የግድ ይላችኋል። በዩቲዩብ ላይ አገልግሎቶችን ወይም ምርቶችን በመሸጥ ወይም ማስታወቂያዎችን በማስቀመጥ ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ። የእኛን አጠቃላይ ማብራሪያ ወይም መግለጫ በዩቲዩብ ላይ ገንዘብ እንዴት እንደሚሰራየሚለውን አንብቡ።
ድረ ገጽ ላይ ዋጋ ያላቸው መረጃዎችን መጻፍ ወይም ብሎጊንግ (Blogging)
ለሰዎች ዋጋ ያላቸውና ጠቃሚ መረጃዎችን በማቅረብ ገቢ ለማግኘት ድረ ገጾችና ብሎጎች ሁነኛ መንገዶች ናቸው። ብሎጊንግ በአፍሪካ የኦንላይን ስራዎች በርካታ ዕድሎችን ከሚፈጥሩት መካከል አንዱ ነው። ብሎጊንግን ለመጀመር፣ የምትጽፉበትን ርዕስ አስቀድሞ መወሰን ያስፈልጋችኋል። የምትጽፉበት ጉዳይን ስሜት የሚሰጣችሁ፣ የምትወዱት እና የሚመቻችሁ ሊሆን ይገባል። ለአብነትም፣ የምትጽፉበት ጉዳይ ፋይናንስ፣ ጤና፣ የመድን ዋስትና፣ ሙያና ብቁነት ሊሆን ይችላል።
ብሎግ በምታደርጉበት ገጽ ላይ ማስታወቂያዎችን በማስቀመጥ፣ ወይም ምርቶችን እና አገልግሎቶችን በመሸጥ በትብብር ወይም በቁርኝት የሚሰራ የንግድ ስራ አማካኝነት ገቢ ልታገኙ ትችላላችሁ። መጠቀም ከምትችሏቸው የማስታወቂያ ኩባንያዎች መካከል ጥቂቶቹ ጎግል አድሴንስ እና ሜዲያቫይንን ያካትታሉ። የሚከተሉትን በመጠቀም ድረ ገጽ መፍጠር ትችላላችሁ:
- WordPress
- Blogger
- Medium
- Wix
- Site
በፌስቡክ ላይ የሚከናወን ሽያጭ
ምርቶችን እና አገልግሎቶችን ለመሸጥ ፌስቡክ ሁነኛ ስፍራ ነው። ፌስቡክ አብዛኞቹ አፍሪካዊያን አካውንት ከፍተው የሚጠቀሙበት ማህበራዊ ፕላትፎርም ወይም መድረክ ነው። ፌስቡክ ላይ የሽያጭ ስራ ለመጀመር፣ ስለምትሸጧቸው ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ የፌስቡክ ፕሮፋይል መፍጠር አለባችሁ። የቡድን (ግሩፕ) ገጾችን በመቀላቀል የንግድ ምርቶቻችሁን ምስሎች እዛ ላይ መለጠፍ ትችላላችሁ፤ ሰዎች የንግድ ምርቶቻችሁን ከወደዷቸው ከእናንተ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ግዢዎችን ይፈጽማሉ። ፌስቡክ ላይ መሸጥ ከምትችሏቸው ምርቶች መካከል አንዳንዶቹ አልባሳትን፣ ጫማዎችን፣ የቤት ዕቃዎችን (ፈርኒቸሮችን)፣ ተሽከርካሪዎችን እና የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ይጨምራሉ።
ዲጂታል ማርኬቲንግ
በርካታ ቢዝነሶች እና ኩባንያዎች በአሁኑ ወቅት ዲጂታል ማርኬቲንግን ስራ ላይ እያዋሉ ነው፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ይህ አሰራር ደንበኛን ማዕከል ያደረገ እና ከልማዳዊው የግብይት መላ ወይም ማርኬቲንግ ጋር ሲነፃፀር በጣም ርካሽ በመሆኑ ነው።
ገበያ ላይ ካሉ የዲጂታል ማርኬቲንግ ስትራተጂዎች ወይም ስልቶች መካከል የመረጃ ማፈላለጊያ ኦፕቲማይዜሽን (SEO)፣ የመረጃ ማፈላለጊያ ማርኬቲንግ (SEM)፣ የባለተጽዕኖዎች ማርኬቲንግ (influencer marketing)፣ በጎግል ወይም በፌስቡክ አማካኝነት የሚከናወኑት ኢ-ሜይል ማርኬቲንግ እና ኦንላይን አድቨርታይዚንግ ይገኙበታል።
ክፍያ ለማግኘት መጻፍ
መጻፍን የምትወዱ ወይም የመጻፍ ክህሎት ካላችሁ፣ መጣጥፎችን በመጻፍ ገቢ ማግኝት ትችላላችሁ። ለመገናኛ ብዙሃን ወይም ሜዲያዎች በመጻፍ ወይም የፈጠራ ጽሁፎችን ወይም ወጎችን (ኤሴይ) መጻፍ ትችላላችሁ። የምርቶች ማብራሪያዎችን ወይም ግምገማዎችን በሚለጥፉ ድረ ገጾችም ላይ መጻፍ ትችላላችሁ። በመጀመሪያ ልትጽፉበት የምትፈሉጉበትን ጉዳይ ምረጡ፣ ከዚያም ቀጣሪን አግኙ። በፍሪላንስ ፕላትፎርሞች ላይ ቀጣሪዎችን ማግኘት ትችላላችሁ። የጽሁፍ ስራዎቻችሁን ናሙናዎች (ሳምፕሎች) እንደ ሜዲያ ካምፓኒስ አድ ለመሰሉ አሳታሚዎች መላክም ትችላላችሁ፤ ጽሁፎቻችሁን ከወደዷቸው ይቀጥሯኋል።
የርቀት ስራ (በትርፍ ጊዜ የሚሰራ ስራ)
አፍሪካ ውስጥ በሩቅ ስፍራ ሆናችሁ የሙሉ ሰአት ወይም የትርፍ ሰአት ስራ በመስራት ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ። አሁን ላይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ባለበት ወቅት፣ በርካታ ኩባንያዎች ሠራተኞቻቸው ስራቸውን በርቀት ሆነው እንዲሰሩ እየመከሩ ይገኛሉ። የሚያስፈልጓችሁ ኮምፒውተር፣ ስልክ እና ጠንካራ የበይነ መረብ ግንኙነት ወይም ኔትወርክ ብቻ ነው። ከዚያም ስራችሁን የትም ሆናችሁ ሰርታችሁና በኦንላይን ልካችሁ ክፍያችሁን ማግኘት ትችላላችሁ።
የርቀት ስራዎችን ልታገኙባቸው የምትችሉባቸው ስፍራዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ:
ለአፍሪካዊያን የኦንላይን ስራዎችን በተመለከተ የበለጠ ለማወቅ
ከዚህ በላይ የተመለከቱት ለአፍሪካዊያን ካሉ የኦንላይን ስራዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው። በርቀት ከቤታችሁ ሆናችሁ ስራችሁን መስራትና ለክፍያም ማስገባት የምትችሉ በመሆኑ ምክንያት በአፍሪካ የኦንላይን ስራዎች አመቺ ናቸው። የሙሉ ሰአት ወይም የትርፍ ሰአት ስራን በኦንላይን መስራት ትችላላችሁ። ከተቀጠራችሁም የኦንላይን ስራችሁን የተመቻችሁን ሰአት በመምረጥ መስራት ትችላላችሁ። ይህም ስራችሁን ሳትለቁ በኦንላይን መስራት ትችላላችሁ ማለት ነው።