በኢትዮጵያ እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ውስጥ መጀመር የምትችላቸው ብዙ ንግዶች አሉ። አንተ ሥራ ፈጣሪ ከሆንክ፣ እነዚህ ሊመለከቷቸው ከሚችሏቸው አንዳንድ ምርጥ የንግድ ሐሳቦች ናቸው።
Contents
በአፍሪካ ውስጥ የንግድ ስራን በምን ምክንያት ትጀምራላችሁ?
- የሰው ካፒታል ወይም ሀብት ባለፈው አስር አመት ውስጥ፣ ቁጥራቸው የበዛ በጥሩ ሁኔታ የተደራጁ ተቋማት ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል። ይህ ደግሞ ለተጽዕኖ አምጪ የስራ ፈጠራ ሞዴል (ኢምፓክት አንተርፕረነርሺፕ ሞዴል) ሀብቶች የሆኑ በህብረተሰቡ ውስጥ ቁጥራቸው የበዛ የተማሩ ወጣቶች እንዲፈሩ አስችሏል።
- የቢዝነስ ወይም የንግድ ስራ ጅማሮ(ቢዝነስ ኢንኪዩቤሽን)። ለጀማሪ የንግድ ስራ አከናዋኞች የስራው የመጀመሪያ ምዕራፍ በጣም ፈታኝ ሊሆን ይችላል። የንግድ ስራ ጅማሮ አመቻቾች (ቢዝነስ ኢንኪዩቤተርስ) አነስተኛ እና ጥቃቅን የንግድ ተቋማት ከመሰረተ ልማት፣ ከገበያ ትስስሮች፣ ፋይናንስ፣ እና ከስራ ፈጠራ ወይም አንተርፕረናል ክህሎቶችጋር በተያያዘ የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ይችሉ ዘንድ እገዛ ሊያደርጉላቸው ይችላሉ። አፍሪካ ውስጥ፣አፍሪላብስን, አይኸብ, and ኮ- ክሬሽን ኸብን ( Co-Creation Hub)ጨምሮ የተለያዩና ውጤታማ የንግድ ስራ ጅማሮ አመቻቾች (ቢዝነስ ኢንኪዩቤተርስ) ይገኛሉ።
- ከፍ ያለ ዘመናዊነት እና ከተሜነት። ብዙ አፍሪካዊያን በአህጉሪቱ ውስጥ ባሉ ባደጉ እና እያደጉ ባሉ ከተሞች ውስጥ ሰፍረው መኖራቸውን ቀጥለዋል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ከጊዜው ጋር የሚሄዱ እና ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤም የእነዚህ ከተሞች መለያ ወይም መገለጫዎች ሆነዋል። እነዚህ መለያዎች ታዲያ በአፍሪካ ውስጥ በ 2022 ዓ.ም. ለተለያዩ አይነቶች የንግድ ስራ መነሻ ሃሳቦች አመቺ መሰረቶች ሆነዋል።
አፍሪካ ውስጥ የንግድ ስራ ለማከናወን ያሉ ተግዳሮቶች ወይም መሰናክሎች ምንድን ናቸው?
- ደካማ መሰረተ ልማት። የአፍሪካ አገራት ዋና ዋና የመጓጓዣ መንገዶች ላይ መሻሻሎች ቢኖሩም፣ በአንዳንድ መንገዶች ላይ መጓጓዝ ግን አሁንም ቢሆን አስቸጋሪ ነው። ከዚህ በተጨማሪም፣ አሁን ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል ያልደረሰባቸው ቦታዎች ወይም ሥፍራዎች አሉ።
- ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች ። በአንዳንድ የአፍሪካ አገራት ውስጥ፣ መንግስት በተለወጠ ቁጥር ጦርነት መፈንዳቱ የተለመደ ጉዳይ ሆኗል። በእንደዚህ ያሉ ጊዜያቶች፣ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች እና ደንበኞች ሰልፍ የሚያካሂዱ ሰዎች ንብረታችንን ያወድሙብናል የሚል ስጋት ስለሚያድርባቸው የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን ይቀንሳሉ፤ ይህ ደግሞ የአገሩን ኢኮኖሚ በጣም ሊጎዳው ይችላል።
- ከፍተኛ የታክስ ወይም ግብር መጠን። በአንዳንድ አፍሪካ አገራት ውስጥ ያሉ ኩባንያዎች ከፍ ያለ የታክስ ወይም የግብር መጠን መኖርን አፍሪካ ውስጥ የንግድ ስራ ለማከናወን ካሉት ችግሮች መካከል እንደ አንድ ቁልፍ ተግዳሮት ወይም መሰናክል አድርገው ይጠቅሱታል። የሁለት ጊዜ ታክስ መኖር እና ከፍተኛ የገቢ ታክስ ወይም ግብር አፍሪካ ውስጥ የተለያዩ የንግድ ስራ ጀማሮዎችን ስኬታማነት ይጎዱታል።
በአፍሪካ ውስጥ የንግድ ስራ ለመጀመር የሚያስችሉ ሃሳቦች
የከተማ አቅርቦቶች ወይም ሎጂስቲክስ
በአፍሪካ ውስጥ የከተሞች ቁጥር እያደገ ይገኛል፤ አስቀድሞ በነበሩት ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎ ቁጥርም በፍጥነት እያደገ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ትንበያዎችም እንደሚያመለክቱት፣ አፍሪካ ውስጥ በከተሞች የሚኖረው ህዝብ እ.ኤ.አ. 2010 ከነበረበት 11.3 % በ 2050 ወደ 20.2 % እንደሚያድግ ነው። እነዚህ የከተማ ማዕከላት ለአፍሪካ አገራት ኢኮኖሚያዊ እድገት ወሳኝ ሚናን ይጫወታሉ። ለዚህም ደግሞ ምክንያት የሚሆኑት እነዚህ የከተማ ማዕከላት ለተለያዩ ለምርቶች እና አገልግሎቶች ከፍተኛ ፍላጎቶችን የሚፈጥሩ በመሆናቸው፣ በልዩ ልዩ ዘርፎች ውስጥ ላሉ ኩባንያዎች መቀመጫ በመሆናቸው፣ እና አገራትንም ስለሚያገናኙ ነው።
የከተማ ማዕከላቱ ለኢኮኖሚያዊ እድገት ያላቸውን ሚና በውጤታማነት እንዲወጡ፣ በአንድ አገር ውስጥም ሆነ ወደ ውጭ እቃዎች ከገጠር አካባቢዎች ወደ ከተሞች በነፃ መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል። ይህ ደግሞ የከተማ አቅርቦቶችን ወይም ሎጂስቲክስን ሚና የሚገልጽ ነው። እንደአለመታደል ሆኖ ግን፣ ይህ ዘርፍ ደካማ መሰረተ ልማትን እና የህዝብ በብዛት ተጨናንቆ መኖር የመሳሰሉት አይነት ሰፊ ችግሮች የተጋረጡበት ነው። ግን ደግሞ እንደ ሌላ ማናቸውም ኢንደስትሪ በችግሮች ወይም ተግዳሮቶች መካከል ዕድሎችም ብቅ ብቅ ይላሉ።
አሁን ስራቸውን በማከናወን ላይ ያሉ እንዳረጋገጡት ይህ አፍሪካ ውስጥ ምርጥ የሆነ የንግድ ስራ ማስጀመሪያ ሃሳብ ነው። አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ፣ በከተሞች አካባቢ ከፍተኛ የግብርና ምርቶች ፍላጎት ቢኖርም በገጠር በአነስተኛ ደረጃ ላይ ያሉ አርሶ አደሮች በመሰረተ ልማት ችግሮች ምክንያት የግብርና ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ለማጓጓዝ ብዙ ጊዜ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል።
እንደ ኬንያው ትዊጋ ፉድስ ያሉ ጀማሪዎች የገጠር አርሶ አደሮችን ከከተማ ነጋዴዎች ጋር በማገናኘት ይህን ክፍተት እየሞሉት ነው። ይህ በእርግጥም አዋጪነት ያለው የንግድ ስራ ማስጀመሪያ ሃሳብ ነው፤ ምክንያቱም አንድ ጀማሪ የንግድ ስራ አከናዋኝ ጥሩ ጥራት ያላቸው የግብርና ምርቶችን ዝቅ ባለ ዋጋ ከሚሸጡበት የአገሪቱ አንድ አካባቢ ፍላጎት ከፍ ወዳለባቸው የከተሞች አካባቢ አምጥቶ ገበያ ላይ ማዋል ስለሚችል ነው።
ቢዝነስ ለ ቢዝነስ (ቢቱቢ) (B2B) አቅርቦት ወይም ሎጂስቲክስ እና የቀረቡ አገልግሎቶችን ዲጂታል ማድረግ አንድ ጀማሪ የንግድ ስራ አከናዋኝ ሌላው በከተማ አቅርቦቶች ወይም ሎጂስቲክስ ዘርፍ አትራፊ ሊያደርገው የሚችል የንግድ ስራ ነው። ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ጥሩና ፍትሃዊ በሆነ ዋጋ አገልግሎቶችን ወይም ንግዶችን ለማቅረብ ሊወስን ይችላል። በዛሬው የኢ-ኮሜርስ ዘመን አፍሪካ ውስጥ ለእነዚህ አይነቱ አገልግሎቶች ያለው ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነው።
መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ
በቂ የሆነ መጠለያ ማግኘት የሰው ልጆች አንዱ መሰረታዊ ፍላጎት ነው። እንደአለመታደል ሆኖ ግን፣ በገጠርም ሆነ በከተሞች ለሚኖሩ ቁጥራቸው የበዛ አፍሪካዊያን ይህ የማይጨበጥ ህልም መሆኑን እንደቀጠለ ነው። በገጠር አብዛኛው ህዝብ የሚኖረው እጅግ አነስተኛ በሆነ ገቢ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ነው። አንዳንዶች ለጥገኞቻቸው ወይም ለቤተሰባቸው አባላት ምግብ ለማግኘት የሚታገሉ በመሆኑ የራሳቸውን በቂ የሆነ ቤት ለማግኘት ለመሞከር እንኳ አይችሉም።
ተመሳሳይ የሆኑ ችግሮች በከተሞች አካባቢም ይታያሉ። በከተሞች አካባቢ የሚታዩ የቆሸሹ ሰፈሮች መኖሪያ ቤት መከራየት ለማይችሉ በድህነት ውስጥ ላሉ ሰዎች መኖሪያ በመሆን ያገለግላሉ። መካከለኛ ገቢ አላቸው የሚባሉትም ሰዎች ከዚህ ችግር አላመለጡም። እነዚህ መካከለኛ ገቢ አላቸው የሚባሉት የህብረተሰብ ክፍሎች ሰላማዊ በሆነ አካባቢ የራሳቸው መኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ያላቸው ህልም ሊሳካላቸው አልቻለም። አሁን ላይ በከተሞች ውስጥ እና በከተሞች አካባቢ አንድ አነስተኛ መሬት እና አፓርትመንት የሚጠየቀው ክፍያ እጅግ ውድ የሚባል ነው፤ ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት ለእነዚህ ሀብቶች ያለው ፍላጎት በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱ ነው።
እነዚህን እውነታዎች ከግምት በማስገባት፣ አንድ ሰው በተመጣጣኝ ዋጋ መኖሪያ ቤቶችን በማቅረብ በተለየዩ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ለሚታዩት እነዚህ ችግሮች መፍትሄ የሚሰጥ ስኬታማ የንግድ ስራን ሊያከናውን ይችላል። ከዚህ ጋር አብሮ ተያይዞ ያለው የንግድ ስራ ማስጀመሪያ ሃሳብ እያደጉ ባሉ ወጣ ያሉ የከተማ አካባቢዎች መሬት በመግዛት ለደንበኞች ተመጣጣኝ ወይም እንደ አቅማቸው ሊከፍሉ በሚችሉት ዋጋ መሬቱን ሸንሽኖ መሸጥ ነው። የዚህ ንግድ አከናዋኝ የአካባቢውን ባለ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያለው ህዝብ ሊስብ በሚችል መልኩ ቤቶችን ገንብቶ ሊሸጥም ይችላል። ከመኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ምርቶችን ፍትሃዊ በሆነ ዋጋ ለሰዎች እና ለአልሚዎች ማቅረብ እንደ ኬንያ፣ ታንዛንያ፣ ሩዋንዳ፣ እና ኢትዮጵያ ሌሎችም ላሉ አዲስ የአፍሪካ ገበያዎች ሌላው አዋጪና ትርፋማ የንግድ ስራ መጀመሪያ ሃሳብ ነው። ምርቶቹ ከግንባታ ቁሳቁሶች ጀምሮ ሌሎች የመኖሪያ ቤቶችን ማሻሻያ ማናቸውም ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ።
ከሌሎች ጋር በጋራ የሚከናወን የግብርና ወይም የእርሻ ስራ (ክራውድ ፋርሚንግ)
አንድ ሰው የሚከተለውን ሊጠይቅ ይችላል፤ ከዓለም በአጠቃላይ 60% ያህሉ ሊታረስ የሚችል መሬት ያለው አፍሪካ ውስጥ ከሆነ፣ አፍሪካ ዘወትር በምግብ እጥረት እና በደሃ አርሶ አደሮቿ የምትገለጽበት ምክንያት ምንድን ነው? ለዚህ በርካታ መሰረታዊ ምክንያቶች ቢኖሩም፣ በግብርና ስራ የተለያዩ ደረጃዎች ወቅት አስፈላጊ የሆኑ ሀብቶች እጥረት ቀዳሚው ምክንያት ነው። አብዛኞቹ አነስተኛ አርሶ አደሮች በተለመደው አይነት የአስተራረስ ልማድ ላይ ብቻ እንዲተማመኑ መሆኑ የስራቸው ውጤት በጣም ያነሰ ምርታማነት እንዲኖራቸው አድርጓል።
ለዚህ ችግር ከአስተማማኝ መፍትሄዎች አንዱ የሆነው ተጽዕኖ አምጪ የስራ ፈጠራ (ወይም ኢምፓክት አንተርፕረነርሺፕ) ነው። ይህ ከሌሎች ጋር በጋራ የሚከናወን የግብርና ወይም የእርሻ ስራ (Crowd Farming) መሰረታዊ መርህ ነው። የተባበሩት መንግስታት እንደሚተነብየው፣ የአፍሪካ የግብርና ንግድ ወይም አግሪቢዝነስ እ.ኤ.አ በ 2030 ዓ.ም. የ 1 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዋጋ ይኖረዋል። የዚህን ‘ዳቦ’ ቁራሽ ለማግኘት እጆቻችሁን ማቆሸሽ አያስፈልጋችሁም። ክራውድ ፋርሚንግ (ከሌሎች ጋር በጋራ የሚከናወን የግብርና ወይም የእርሻ ስራ) በየትኛውም የዓለም አካባቢ ያሉ ሰዎች በተለይ በግብርና ፕሮጀክቶች ላይ ገንዘባቸውን በማፍሰስ ወይም ኢንቨስት በማድረግ አርሶ አደሩ ካመረተው ምርት ላይ ድርሻውን የሚያገኝበት የአግሪቢዝነስ ሞዴል ነው።
(https://www.farmcrowdy.com/) ፋርምክራውዲ አፍሪካ ውስጥ ትርፋማ የሆነው የክራውድ ፋርሚንግ መዋቅር አንድ ምሳሌ ነው። ይህ ድርጅት ኢንቬስተሮችን ከአርሶ አደሮች ጋር እንደሚያገናኝ በክፍለ አህጉሩ የመጀመሪያው የግብርና ወይም የእርሻ ቴክኖሎጂ (አግሪቴክ) ኢንተርፕራይዝ በመሆን እ.ኤ.አ በ 2017 ዓ.ም. በናይጄሪያ ተመስርቷል። የሚገኙትን ገቢዎች ኢንቬስተሮቹ፣ አርሶ አደሮቹ እና ኩባንያው ይከፋፈሏቸዋል። በዚህ ሞዴል አማካኝነትም ኢንተርፕራይዙ ከ 38 ሚሊዮን በላይ የሆኑ በአነስተኛ ደረጃ ላይ ያሉ አርሶ አደሮችን ለመድረስ ችሏል።
ፋርምክራውዲ አንድ ሰው በግብርና ወይም በእርሻ ስራ ቦታ ላይ በተግባር መሳተፍ ሳያስፈልገው ሰፊ በሆነው የግብርና ዘርፍ ላይ እንዴት ስኬታማ ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ ትክክለኛ ወይም ፍጹም የሆነ ምሳሌ ነው። ከዚህ በተጨማሪም፣ አንድ ሰው መጀመሪያ ላይ ትልቅ ኩባንያን ማንቀሳቀስ አያስፈልገውም። ከጓደኞቹ ወይም ከዘመዶቹ ጋር በጋራ በመሆን ኢንቨስት የሚያደርግባቸውን አርሶ አደሮችን መፈለግ ይችላል። ለክራውድ ፋርሚንግ ፍሬያማነት ወይም ውጤታማነት ቁልፍ የሆነው ጉዳይ ከፍ ያሉ ተስፋ ሰጪ እና ዝቅተኛ ጉዳቶች (ሪስክ) ያላቸው እህሎችን እና የግብርና ስራ አተገባበርን (farming setup) መለየት ነው።
ኢ-ጤና (E-Health)
ከዓለማችን ህመሞች ወይም የጤና እክሎች 25% ያህሉን የተሸከመችው አፍሪካ ብትሆንም ከአጠቃላይ ህዝቧ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ከፍ ያለ ጥራት ላላቸው የህክምና አገልግሎቶች ተደራሽ አይደለም ወይም ደግሞ የጤና መድህን ዋስትና የለውም። አሁን ላለው ለዚህ አሳዛኝ ሁኔታ እንደ የፖለቲካ መደቡ ወይም አስተዳደሩ ብቃት አልባ መሆን የመሳሰሉ ተጨማሪ ምክንያቶች አስተዋፃኦ ቢኖራቸውም ቁልፍ ከሆኑት ምክንያቶች አንዱ ግን ድህነት ነው። የሶስተኛው ዓለም አገራት ተብለው የተፈረጁት አብዛኞቹ የአፍሪካ አገራት፣ ለዜጎቻቸው በቂና ዘመናዊ ሆስፒታሎችን ለማቋቋም ወይም ለመገንባት አስፈላጊ የሆነው የገንዘብ አቅም የላቸውም። በእርግጥ ለመናገርም፣ መሰረታዊ የሆኑ የጤና አገልግሎቶችን ለማግኘት እጅግ የረዘመን ርቀት የመጓዝ ግዴታ ውስጥ የገቡት አፍሪካዊያን የመገናኛ ብዙሃኑ የተለመዱ ታሪኮች ወይም ዘገባዎች ሆነዋል።
እስቲ ይህን ሁኔታ በምናባችሁ ሳሉት፡ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት በአካላዊ ባህርይዋ ላይ አንዳንድ ለውጦችን ማስተዋል ብትጀምርም ለውጡ ጤናማ የእርግዝና ክስተት ስለመሆን አለመሆኑ ወይም ስጋት ላይ ሊጥላት የሚገባ ሁኔታ ስለመሆኑ እርግጠና አይደለችም። የህክምና ምክር ለማግኝት 10 ኪሎ ሜትሮችን መጓዝ እንዳለባት እንዲሁም ለምክሩ የሚከፈለውን ገንዘብ ስታስብ መንፍሷ ሙትት አለባት። በአሁኑ ወቅት አብዛኞቹ አፍሪካዊያን የተንቀሳቃሽ ወይም ሞባይል ስልክ ባለቤት መሆናቸውን ስናስብ፣ ይህቺ ሴት ቤቷ በምቾት ተቀምጣ ላሏት ጥያቄዎች ሁሉ ምላሾችን ማግኘቷ ደስተኛ እንድትሆን አያደርጋትምን?
የስራ ፈጣሪዎች ወይም አንተርፕረነርስ > ህብረተሰቡን ከተለያዩ የህክምና ባለሞያዎች ጋር የሚያገናኝ ዲጂታል ፕላትፎርሞችን በመስራት ይህን ችግር ለመፍታት ያግዛሉ፣ በሂደቱም ትርፋማ የሆነ ቢዝነስን ወይም የንግድ ስራን ያከናውናሉ። አንድ ምሳሌ ለመስጠት ያህል፣ ይህ የቢዝነስ አሰራር ስርዓት በአንድ አገር ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በተገቢው አካል እውቅና የተሰጣቸው የህክምና ባለሞያዎችን፣ የድንገተኛ ህክምና አገልግሎት ሰጪዎችን፣ እንዲሁም የፋርማሲዎችን ወይም መድኃኒት መሸጫዎችን መገኛ አድራሻዎችና ተገቢ ዝርዝሮችን ሊያካትት ይችላል። የቱንዚያው የርቀት ህክምና አገልግሎት ወይም ቴሌ-ሜዲሲን Agence Française de Developpement የአንድ አዋጪ የኢ-ጤና (e-health) ፕሮጀክት ጥሩ ማሳያ ሊሆን ይችላል።
ኩነቶችን ማቀድና ማዘጋጀት(ኢቨንት ፕላኒንግ)
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ፣ በርካታ አፍሪካዊያን የኩነቶች አመራርን እየተረዱት ወይም እየተገነዘቡ መጥተዋል። አፍሪካዊያን የአንድ ልዩ ስነ ስርአትን መሰረታዊና ዝርዝር ነገሮችን ራሳቸው ከማደራጀት ወይም ከማዘጋጀት ይልቅ ሁሉንም ነገሮች የሚከኑ የባለሞያ አገልግሎቶችን በክፍያ ያገኛሉ። አንድ ሰው በዚህ አትራፊ ቢዝነስ ላይ ከሌሎች ጋር በሚኖረው ፉክክር አንፃራዊ ተጠቃሚነትን ለማግኘት የአገልግሎት አይነቱን ማብዛት ያስፈልገዋል።
በአንድ የተለየ ገበያ ላይ ብቻ ማተኮር የሚሰጠው ጥቅም እንዳለ ሆኖ፣ አንድ ሰው ግን የቀብር ፣ የሰርግ፣ የልደት፣ የድርጅቶች በዓል እንዲሁም የሌሎች መድረኮች ስነ ስርአቶች አገልግሎቶችን በማቅረብ የደንበኞች መሰረቱን ይበልጥ የማስፋት እድል አለው። ክዚህ በተጨማሪም፣ ሌላው አንድን ሰው በዚህ የቢዝነስ መጀመሪያ ሃሳብ አማካኝነት ወደ ስኬት ሊያስፈነጥረው የሚችለው አሰራር ደግሞ ጥቅል አገልግሎትን ወይም ፓኬጅን ለተገልጋዮች ማቅረብ ነው። ድንኳኖችን፣ ወንበሮችን፣ እና ጌጣ ጌጦችን ከማቅረብ ይልቅ፣ እንደ መጠጦችና ምግቦች፣ የስነ ስርአት ዋና አስተናባሪን፣ የመዝናኛ ዝግጅት አቅራቢዎችን፣ እና መጓጓዣ (ትራንስፖርት) ያሉ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ማቅረቡም እንዴት ጥሩ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ይቻላል። በአጭሩ፣ ከኩነቶች ዝግጅቶች ጋር በተያያዘ በአካባቢያችሁ በሰዎች የምትፈለጉና የምትመረጡ ለመሆን ጥረት አድርጉ።
ማጠቃለያ፡-የቢዝነስ ሀሳቦች በኢትዮጵያ
አፍሪካ ከታዳጊነት ወደ ጉልምስና የደረሰችበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። በአፍሪካ በ 2022 ዓ.ም. አዋጪነት ያላቸውን ምርጥ የቢዝነስ ማስጀመሪያ ሃሳቦችን የመለየትና የመተግበር ተመራጩ ወቅት አሁን ነው። ስራ ፈጣሪዎች ወይም አንተርፕረነሮች በንግድ ስራቸው ጅማር የመጀመሪያዎቹ አመታት በአብዛኛው ችግሮች የሚያጋጥሟቸው ቢሆንም፣ አህጉረ አፍሪካ እጅግ አትራፊ በሆኑ የቢዝነስ እድሎች የተሞላች ናት። በታጋሽነት እና ውጤታማ በሆነ ስልታዊ እቅድ ከተመራችሁ እናንተም በአፍሪካ ካሉት ስኬታማ የንግድ ወይም የቢዝነስ ሰዎች አንዱ መሆን የመቻላችሁ እውነታ አይቀሬ ነው።