በኢትዮጲያ ቢትኮይን እንዴት ማግኘት ይቻላል

ትርጉሞች:
en_USsw

ቢትኮይን ታዋቂነት እያደገ በመምጣቱ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ቢትኮይንን ለማግኘት በርካታ መንገዶች አሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ቢትኮይንን ከመግዛት፣ በተጨማሪ፣ አንድ ሰው ቢትኮይንን ማግኘት የሚችልባቸው ሌሎች ብዙ መንገዶች አሉ።

ቢትኮይንን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል

ኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶን ማግኘት የምትችሉባቸው በርካታ አማራጮች አሉ። ቢትኮይንን በፍጥነት በነጻ ለማግኘት ፈጽሞ አይቻልም ማለት ይቻላል፤ ይህንን በደንብ ማወቅ አለባችሁ። ከዚህ በታች የተመለከቱትን ዘዴዎች በመከተልና የራሳችሁንም በቂ ምርምር በማድረግ ቢትኮይንን ማግኘት ትችላላችሁ።

በቦትስዋና የሚገኘው የቢትኮይን ኤቲኤም ወይም የገንዘብ መክፈያ ማሽን አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙት 10 የቢትኮይን መክፈያ ማሽኖች አንዱ ነው።
የቢትኮይን መክፈያ ማሽን።

ቢትኮይንን እንደ የክፍያ ዘዴ መቀበል

ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን በቢትኮይን የምንዛሪ ልውውጥ ልትሸጡ ትችላላችሁ። ቢትኮይንን መቀበል አዳዲስ ደንበኞች ወደ እናንተ ንግድ ስራ እንዲመጡ ሊያደርጋቸው ይችላል። አፍሪካ ውስጥ ቢትኮይን nመቀበል ቢትኮይንን እንደ የክፍያ አንድ መላ አድርገው የተቀበሉ በርካታ ቢዝነሶች እና ሰዎች አሉ። ቤቲስ ፕሌስ ተብሎ የሚጠራው ኒዬሪ በተባለች የኬንያ የገጠር ከተማ የሚገኝውና በቤቲ ዋምቡጉ ባለቤትነት የሚተዳደረው ሬስቶራንት እንደ አንድ ምሳሌ ሊጠቀስ የሚችል ነው። ቤቲ በምስራቅ አፍሪካ ታዋቂ የሆነውንና ተወዳጁን “ኒያማ ቾማ” (የተጠበሰ የበሬ ስጋ ነው) ተብሎ የሚጠራውን ምግብ ትሸጣለች፣ ክፍያውንም በቢትኮይን ትቀበላለች።.

የበይነ መረብ ወይም ኢንተርኔት የቀጥታ ግንኙነት ያለው/የሌለው መደብር ወይም ሱቅ ልንለው እንችላለን ካላችሁ፣ ከእነዚህ የክሪፕቶ ክፍያ መግቢያዎችመካከል ማናቸውንም በመጠቀም ከደንበኞቻችሁ ቢትኮይንን መቀበል ትችላላችሁ።

የቢትኮይን ክፍያ የሚከፈልባቸውን ስራዎች መስራት

በቢትኮይን ክፍያ የሚከፈልባቸው ስራዎችን የሚያገናኟችሁ ድረ ገጾች አሉ። በቢትኮይን እንዲከፈላችሁ የማድረግ ፍላጎት ካላችሁ፣ ከድረ ገጾቹ መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉትን ይጨምራሉ።

ደምወዛችሁን ወደ ቢትኮይን መቀየር። በአሁኑ ወቅት እንደ ቢትዌጅየመሳሰሉ የክሪፕቶ የደምወዝ መዝገብ አገልግሎቶች ያሉትን በመጠቀም መንግስት ባተመው ገንዘብ የሚከፈላችሁን ደምወዝ ወደ ቢትኮይን መቀየር ወይም መለወጥ ይቻላል።

ማይክሮ ወይም ጥቃቅን ስራዎችን መስራት

ማይክሮ ስራ በአብዛኛው በበይነ መረብ ወይም በኢንተርኔት ምዝገባ የሚካሄድበት ጊዜያዊ የስራ አይነት ነው። እንደ ለ ኢሜይሎች መልስ መስጠት፣ አንድን ማስታወቂያ ሊንኩን ተጭኖ መመልከት፣ የጥናት ቅጾችን ወይም ፎርሞችን መሙላት፣ ቪዲዮን መመልከት፣ ወዘተ ለመሳሰሉ ቀላላል ስራዎች በቢትኮይን የሚከፈልባቸው በርካታ ድረ ገጾች አሉ።

በማይክሮ ስራዎች ቢትኮይን ከሚያስገኙላችሁ ድረ ገጾች መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፤

ማይክሮ ወይም ጥቃቅን ስራዎችን በመስራት ከፍተኛ ገንዘብ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ፣ አስቸጋሪ እና እጅጉን ጊዜ ወሳጅ ነው።

ስለቢትኮይን መጻፍ

ስለ Bitcoin በመጻፍ ገንዘብ ማግኘት ይችላሉ. ይህ አዲስ እና አስደሳች ርዕስ ከመሆኑ እውነታ በተጨማሪ ስለ እሱ ጥሩ ጽሑፍ እንዲጽፉ የሚፈልጉ ብዙ ድህረ ገጾች አሉ። ድረ-ገጾች ለጸሐፊዎች ከ Bitcoin ጋር የተያያዙ ርዕሶችን ለመጻፍ ይከፍላሉ. እንደ እንግዳ ጸሐፊ ወይም ጦማሪ በድረገጻቸው ሊከፈሉ ይችላሉ ወይም የሚከፈልበት የቢትኮይን ጋዜጠኛ መሆን ይችላሉ።

ጨዋታዎችን ወይም ጌሞችን በመጫወት ቢትኮይን ማግኘት

በኦንላይን ጨዋታዎችን ወይም ጌሞችን በመጫወት ቢትኮይን ማግኘት ትችላላችሁ። አንዳንድ ጨዋታዎች ወይም ጌሞች በመጫወት መጠኑ ከፍ ያለ ቢትኮይንን ለማግኘት ግን ረጅም ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ማስተዋል አለባችሁ። ጨዋታዎችን ወይም ጌሞችን በመጫወት ቢትኮይን ማግኘት ከምትችሉባቸው የኦንላይን ፕላትፎርሞች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡

ቢትኮይንን መበደር

በክሪፕቶ የሚደገፉ ብድሮችንየሚሰጡ ኩባንያዎች ቁጥር ከፍ እያለ መጥቷል። ይህ ምን ማለት ነው እናንተ ሌሎች ክሪፕቶዎች ካሏችሁ፣ እነዚህን ክሪፕቶዎች እንደመያዣ በማስያዝ ብድሮችን በቢትኮይን ማግኘት ትችላላችሁ። በክሪፕቶ ብድሮች ምህዳር ውስጥ ካሉ ግምባር ቀደም ፕላትፎርሞች መካከል ጥቂቶቹ ኮይንሎን (CoinLoan) እና አንቼይንድ ካፒታል (Unchained Capital) ናቸው።

በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ የንግድ ስራ ቢትኮይንን ማግኘት (Bitcoin Affiliates)

በትብብር ወይም በቁርኝት የሚሰራ የንግድ ስራ ወይም በእንግሊዘኛው አፊሊየት ማርኬቲንግ እናንተ በመራችኋዋቸው መሰረት ቢዝነሱን በጎበኙ በእያንዳንዱ ጎብኚ ወይም ወደ እሱ በመጡ እያንዳንዱ ደንበኛ ክፍያን ከቢዝነሱ ባለቤት የምታገኙበት የስራ ክንዋኔን ወይም ውጤትን መሰረት ያደረገ የግብይት ወይም የማርኬቲንግ አይነት ነው። በትብብር ወይም በቁርኝት የሚሰራ የንግድ ስራ ላይ ተዋናይ ወይም ተካፋይ ስትሆኑ፣ በእናንተ ድረ ገጽ ላይ ወይም በማህበራዊ መገናኛ ማለትም ሶሻል ሜዲያ ፕላትፎርሞች ላይ ለሌሎች ማጋራት የምትችሉትን ሊንክ ታገኛላችሁ። በእናንተ ጥረት ምክንያት ግዢ ሲፈጸም የኮሚሽን ክፍያን ታገኛላችሁ።

በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ የንግድ ስራ በቢትኮይን ክፍያን ማግኘት የምትችሉባቸው ፕላትፎርሞች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፤

የቢትኮይን ማይክሮ የማበረታቻ ክፍያዎች ወይም ቢትኮይን ማይክሮ ቲፒንግ

make money from bitcoin

ኦንላይን ላይ በሰራችሁት ስራ ምክንያት እንደ ማበረታቻ ክፍያ በቢትኮይን የሚያስገኙ የኦንላይን ፕላትፎርሞች አሉ። የማበረታቻ ክፍያው በፈጠራችሁት ይዘት ወይም ኮንቴንት ወይም ደግሞ ሌላ ሰውን በመርዳታችሁ ምክንያት ሊሆን ይችላል። የቢትኮይን የማበረታች ክፍያ (ቲፒንግ) መተግበሪያዎች ወይም አፕልኬሽኖች እና ፕላትፎርሞች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፤

ቢትኮይን መቆጣጠሪያዎች (Bitcoin Faucets)

ቢትኮይን መቆጣጠሪያዎች (https://en.wikipedia.org/wiki/Bitcoin_faucet) በድረ ገጽ ወይም በመተግበሪያ ማለትም አፕልኬሽን መልክ ያለው የሽልማት አሰራር ሲሆን ሽልማቱም የአንድ ሚሊዮንኛ ቢትኮይን አንድ መቶኛ በሆነው ሳቶሺ (የቢትኮይን የመጨረሻው ትንሹ ዩኒት ማለት ነው) መልክ ነው፤ ይህን ሽልማትም ድረ ገጹ በሚገልጸው መሰረት የድረ ገጹ ጎብኚዎች የትክክለኛነት ማጣሪያውን (captcha) ወይም ስራውን ሲያጠናቅቁ ነው። ማስታወቂያዎች ዋነኛ የገቢ ምንጭ ናቸው። ይህም ሲባል ማስታወቂያውን በመመልከታችሁ ወይም ጥናቶችን (ሰርቬዎችን) በመሙላታችሁ ምክንያት ክፍያን ታገኛላችሁ ማለት ነው።

በአጠቃላይ፣ ቢትኮይን መቆጣጠሪያዎች የሚመጡት ከአደጋዎች ወይም ሪስኮች ጋር ነው፣ ስራዎቹም በጣም አሰልቺ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቹ መቆጣጠሪያዎች (faucets) ሲፒዩዋችሁን (CPU) ማለትም የኮምፒውተራችሁን ዋናውን የስራ አከናዋኝ በመጥለፍ ቢትኮይን ለመስረቅ ይበረብራሉ። ቢትኮይናችሁን ለማስቀመጥ የመቆጣጠሪያ ዋሌቶችን (faucet wallets) ፈጽሞ መጠቀም እንደሌለባችሁ አስታውሱ፤ ከዚያ ይልቅ ምርጥ የቢትኮይን ካዝናዎችን ወይም ዋሌቶችንተጠቀሙ።

ቢትኮይንን መስራት (ቢትኮይን ማይኒንግ)

ቢትኮይን ማይኒንግ አዲስ ቢትኮይን የሚፈጠርበት ወይም የሚሰራበት ሂደት ማለት ነው። የቢትኮይን ሰሪዎች ወይም ቢትኮይን ማይነርስ በብሎክቼይን (Blockchain) የቢትኮይን ግብይቶች መደረጋቸውን በማረጋገጣቸው ወይም ቬሪፋይ በማድረጋቸው በሽልማት መልክ በቢትኮይን ክፍያ ይደረግላቸዋል። ለቢትኮይን ማይኒንግ የሚሰጠው ሽልማት በየአራት አመቱ በግማሽ ይቀንሳል። ቢትኮይን ለመጀመሪያ ጊዜ እ.ኤ.አ. በ 2009 ሲፈጠር አንድ ብሎክ መፍጠር ወይም መስራት 50 ቢትኮይን ያስገኝ ነበር። በህዳር 2019 ግን አንድ ብሎክ በመፍጠራችሁ ወይም በመስራታችሁ የምታገኙት 12.5 ቢትኮይን ነው።

ፈጣሪዎቹ ወይም ሰሪዎቹ በሽልማት መልክ ቢትኮይን እንደማበረታቻ የሚሰጣቸው የቢትኮይን ፈጠራ ሂደትን ማለትም የማይኒንጉን ተቀዳሚ አላማዎች እንዲያግዙ ነው፤ እነዚህ አላማዎችም፡ ለቢትኮይን ትስስሮሽ ወይም ኔትወርክ እና ለብሎክቼይኑ ድጋፍ መስጠት፣ ህጋዊ ቅቡልነት እንዲኖረው ማድረግ እና ቁጥጥር ወይም ክትትል ማድረግ – Investopediaናቸው።

የቢትኮይን ፈጠራ ሂደት ወይም ማይኒንግ ከፍተኛ የሆነ የሂሳብ ስሌት (ኮምፒውቲንግ) ችሎታን ከመጠየቁም ባሻገር በጣም ላቅ ያለ ጉልበትን ይጠቀማል። እንደ ኢዩጂን ሙታይያሉ አፍሪካዊያን የቢትኮይን ሰሪዎች ወይም ፈጣሪዎች በዚህ ስራ ላይ ኬንያ ውስጥ በንቃት በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን እንደ አብነት የጠቀስነውም ሙታይ በስራው ከፍተኛ መጠን ያለው ገቢ እያገኘ ነው። ቢትኸብ አፍሪካ Bithub Africa ተብሎ የሚጠራ የንግድ ወይም የኮሜርሺያል ብሎክቼይን አቀላጣፊ ያለ ሲሆን ፣ የፀሐይ ኃይልን በመጠቀም ክሪፕቶከረንሲ ማለትም ዲጂታል ገንዘብ መስራት ወይም መፍጠር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ እየሰራ ይገኛል። ይህ አፍሪካ ውስጥ ክሪፕቶን በተለይም ቢትኮይንን ለመስራት ወይም ለመፍጠር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ የሚያሳይ ነው።

ልትጠቀሟቸው የምትችሏቸው በርካታ የክሪፕቶ መፍጠሪያ ወይም መስሪያ ፕላትፎርሞች እና ሶፍትዌሮች አሉ። በክሪፕቶ ማይኒንግ አፍሪካ ውስጥ ቢትኮይንን ለማግኘት መጠቀም ከምትችሉባቸው ፕላትፎርሞች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡

ማጠቃለያ

ከላይ ከዘረዘርናቸው መካከል ማናቸውንም ለመጠቀም መጠቀም የምትፈልጓቸው ፕላትፎርሞች ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ጊዜ ወስዳችሁ ጥናት ማድረግና ተያያዥ አደጋዎችን ወይም ሪስኮችን መረዳት እነዚህን አደጋዎችን እንዴት መወጣት እንደምትችሉም መረዳት ይኖርባችኋል።