ቢትኮይን ኢትዮጵያ ግዛ

ትርጉሞች:
en_US

ቢትኮይን እና ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ እ. ኤ. አ በ 2009 ዓ.ም. ከተዋወቁበት ወቅት አንስቶ ዝናቸውና ጥቅማቸው እያደገ መጥቷል። በዚህ ጽሁፍ ውስጥም ኢትዮጵያ ውስጥ ቢትኮይንን እና ሌሎች ክሪፕቶከረንሲዎች እንዴት በጥንቃቄ መግዛት እንደሚቻል እናሳያችኋለን።

ይህን ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ያንብቡ: How to Buy Cryptocurrency in Ethiopia

ቢትኮይን በኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ ነውን? ቢትኮይን በኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ እውቅና የተሰጠው የመገበያያ ገንዘብ አይደለም፣ ማዕከላዊ ባንኩም የቢትኮይን ግብይቶችን አይቆጣጠርም።

ስለክሪፕቶከረንሲ መታወቅ የሚገባቸው ጉዳዮች

 • ክሪፕቶከረንሲ ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን ለመግዛት እንዲሁም ለክሪፕቶ ኢንቨስትመንት የሚውል ዲጂታል ገንዘብነው።
 • በርካታ ክሪፕቶከረንሲዎች፣ ቢትኮይኖች እና ሺትኮይኖችአሉ። በጣም የታወቀውና እኛም የምንመክረው ክሪፕቶ ቢትኮይን ነው። ቢቲኮይን ኦሪጂናሉና በግንባር ቀደምትነትም በመምራት ላይ የሚገኝ የዲጂታል ገንዘብ ነው።. ለመጀመሪያ ጊዜ የተፈጠረውም እ. ኤ. አ በ 2009 ዓ.ም. ሳቶሺ ናካሞቶ በተባለ ሰው ሲሆን የዚህ ሰው እውነተኛ ማንነት እስካሁን አይታወቅም።
 • እ. ኤ. አ ከጥር 10 ቀን 2023 ዓ.ም. አንስቶ፣ 1 ቢቲኮይን ከኢትዮጵያ ብር 932.187,22 ጋር እኩል ነው። የኢትዮጵያ ብር በ 100 ሳንቲሞች ሊከፋፈል ቢችልም፣ የቢትኮይን የመጨረሻው ዩኒት የሆነውና ሳቶሺ ተብሎ የሚጠራው ግን የአንድ ቢትኮይን አንድ መቶ ሚሊዪነኛ (0.00000001 ቢቲሲ) ነው።

የክሪፕቶከረንሲ ማጭበርበሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ በጠቅላላው በጣም እየጨመረ መጥቷል። “ቢትኮይንን ተቀላቀሉ” እና በፍጥነት ሀብታም ሁኑ የሚሉ የማህበራዊ መገናኛዎች መልዕክቶችን ወይም የኢሜይል ጥያቄዎችን ፈፅሞ ማስተናገድ የለባችሁም። በክሪፕቶ ኢንቨስትመንት ከፍተኛ ትርፍ ታገኛላችሁ ከሚሉ የግለሰቦች ወይም የኩባንያዎች ቃሎች ተጠንቀቁ፣ ራሳችሁንም ጠብቁ። ስለክሪፕቶከረንሲ ማጭበርበሮችና እነሱንም እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል የበለጠ ለማወቅ.

በኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶከረንሲን ከመግዛታችሁ አስቀድሞ ልታውቋቸው የሚገቡ ጉዳዮች

በኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶከረንሲን ከመግዛታችሁ አስቀድሞ፣ የሚከተሉትን ማወቅ አለባችሁ፤.

 • የክሪፕቶከረንሲ ገበያ በኢትዮጵያ የክሪፕቶ ግብይት ተጠቃሚዎች ክሪፕቶከረንሲዎችን መግዛትና መሸጥ የሚያስችላቸው አሰራር ወይም መድረክ ነው። በአጭር አነጋገር የክሪፕቶከረንሲ ገበያ (ወይም የክሪፕቶከረንሲ “ሱቅ”) ነው። የክሪፕቶከረንሲ ግብይት የበርካታ ገንዘቦች ድጋፍ ያለው ከመሆኑም ባሻገር አገር አቀፋዊ ወይም ዓለም አቀፋዊ ሊሆን ይችላል።

 • የክፍያ ዘዴ የክፍያችሁ ዘዴ የሚመሰረተው የክሪፕቶከረንሲ ግብይቱን በሚደግፈው የክፍያ ዘዴ ላይ ነው። በተንቀሳቃሽ ስልክ ማለትም ሞባይል ስልክ የሚደረግ የገንዘብ ልውውጥ፣ በብድር ካርድ፣ በክሬዲት ካርድ፣ በባንክ ማስተላለፍ፣ የገንዘብ ልውውጥ አገልግሎቶች ለምሳሌ ዌስተርን ዩኒየንን መጥቀስ ይቻላል፣ ወዘተ ሊሆን ይችላል።, Wise

 • ክሪፕቶ ዋሌት Crypto wallet. ክሪፕቶከረንሲዎች ግዝፈት ያላቸው ወይም በሌላ አነጋገር ባካል የሚያዙና የሚዳሰሱ ገንዘቦች አይደሉም። ስለሆንም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶዎቻችሁን ለማስቀመጥ ደህንነቱ የተጠበቀ የክሪፕቶከረንሲ ዋሌት ያስፈልጋችኋል ወይም ሊኖራችሁ ይገባል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ አይነቶች የቢትኮይን ዋሌቶች አሉ፤ እነዚህም: ሞባይል ወይም ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ በይነ መረብ፣ ዴስክቶፕ እና ሀርድዌር ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ ምርጥ የሚባሉት የቢትኮይን ዋሌቶች ሶፍትዌር ክሪፕቶከረንሲ ዋሌቶችን ይጨምራሉ፣ ለአብነትም Samourai ወይም ሀርድዌር ዋሌት ለምሳሌ፣ Trezor እና Ledgerሊጠቀሱ ይችላሉ።. እነዚህ ሁሉ እንግዲህ ለኢትዮጵያ ምርጥ የተባሉ የክሪፕቶከረንሲ ዋሌቶች ናቸው!!

የቢትኮይን ዋሌታችሁ በ “ግል ቁልፎች” (የይለፍ ቃል ወይም ፓስወርድ አይነት ነው) ይጠበቃል። የራሳችሁን ክሪፕቶከረንሲ በግል ቁልፋችሁ (የይለፍ ቃል ባለው ማለት ነው) ዋሌት ውስጥ እንድታስቀምጡ እንመክራለን። ከዚህ በታች እንደተዘረዘሩት ያሉ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያዎች የራሳቸው የሆነና እናንተም ቢትኮይኖን ልታስቀምጡባቸው የምትችሉበት ዋሌት ሊኖራቸው ይችላል፤ ሆኖም ግን በእነዚህ ላይ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር አይኖራችሁም። በክሪፕቶ ማህበረሰብ ገጽ ላይ እንደተገለጸውም፣ “ቁልፎችዎ ከሌሉ ሳንቲሞችዎም የሉም።” ሀርድዌር ዋሌቶችን ሁሌም በቀጥታ መግዛት ያለብዎት ከዋናው አምራች ወይም ከታወቁ ቸርቻሪዎች ወይም ሻጮች ነው። በበይነ መረብ በቀጥታ ማለትም ኦንላይን አማካኝነት በግል ሽያጭ የሚያከናውኑ ሌሎች ሻጮች ወይም ቸርቻሪዎች የእናንተን ክሪፕቶዎች ለመስረቅ ሲሉ ዋሌቱን ከመሸጣቸው በፊት ሊቀያይሩት ይችላሉ።

ክሪፕቶከረንሲን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት መጠቀም እንደሚቻል

“ስለቢትኮይን በመጀመሪያ የሰማሁት እ.ኤ.አ. በ 2015 ዓ.ም. ቢሆንም አመንትቼ ነበር። አስፈላጊነቱን የተገነዘብኩት ወደ ጥቂት አገራት በተጓዝኩበት ወቅት ባየሁት ነገር ነው፤ በእነዚህ አገራት ውስጥ ያሉ የገንዘብ ከፋይ ማሽኖች (ATMs) ለቢቲኮይን መደበኛውን የመገበያያ ገንዘብ ሊሰጧችሁ ይችላሉ። የመጀመሪያውን ቢትኮይን ከገዛሁ በኋላ ግን በርካታ ነገሮች ተለውጠዋል። አሁን ከአማዞን መግዛት እችላለሁ። በቢትኮይን ክፍያ ከፈጸምኩ በኋላ የፈጣን መልዕክት አገልግሎት ሰጪዎች የሆኑት ፌዴክስ ወይም ደግሞ ዲኤችኤል የገዛሁትን ሊያመጡልኝ ይችላሉ። አንድ ቶዮታ ቪትዝ መኪና በኢትዮጵያ ብር ከ 340000.00-345000.00 በግዢ ወደ አገር ውስጥ አስመጥቼ በቀን በብር 300.00 ላከራየው እችላለሁ። ሆኖም ግን፣ በቢቲኮይን በቀን ከ 400.00-460.00 ብር ትርፍ አገኛለሁ፤” በማለት አስተያየቱን የሚሰጠው ሽፈራሁ ታምራት የተባለና በአዲስ አበባ የሚኖር መኪና አስመጪ ነው። – ይላል። Shiferaw Tamirat, አዲስ አበባ ላይ ያለ መኪና አስመጪ.

ቢትኮይንን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት መግዛት እንደሚቻል

ኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶከረንሲን ለመግዛት የክሪፕቶከረንሲ ዋሌት እና እዛው ኢትዮጵያ ውስጥ የክሪፕቶ መገበያያ ያስፈልጋችኋል። ሆት ክሪፕቶ ዋሌትን ለምሳሌ ሳሙራይ እና ኮልድ ክሪፕቶ ዋሌትን ለምሳሌ ትሬዘር እና ሌዠርን መጠቀም ትችላላችሁ። እና coldcrypto wallet Trezor and Ledger.

አንዴ ዋሌቱን ካገኛችሁና መገበያያውንም ከመረጣችሁ፣ መግዛት ለምትሹት ቢትኮይን ክፍያ ለመፈጸም በርካታ የክፍያ ዘዴዎችን መጠቀም ትችላላችሁ። ከነዚህም መካከል እንደ ባንክ ማስተላለፊያዎች እና ዴቢት ካርዶች ያሉ ልማዳዊ የክፍያ ዘዴዎች ይገኛሉ። ሆኖም ግን፣ የክፍያ ዘዴዎቹ መኖር ወይም መገኘት የሚወሰነው በምትጠቀሙት መገበያያ ነው።

የክሪፕቶከረንሲ ግብይት በኢትዮጵያ

ፓክስፉል በኢትዮጵያ

paxfulethiopia

ኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶከረንሲን ለመግዛት ከምትችሉባቸው ምርጥ መንገዶች መካከል አንዱ የአቻ ለአቻ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ መድረክ ወይም ፕላትፎርም የሆነው ፓክስፉል ነው። ፓክስፉል ኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶከረንሲን ለመግዛት የምትችሉባቸው በርካታ የክፍያ ዘዴዎች አሉት። ኢትዮጵያ ውስጥ ፓክስፉልን ከሚደግፉ የክፍያ ዘዴዎች መካከል ጥቂቶቹ እንደ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የክሪፕቶከረንሲ የስጦታ ካርዶች፣ ፔይፓል፣ ስክሪል፣ ክሬዲት ካርድ፣ ዴቢት ካርዶች፣ ወዘተ ያሉ የአገር ውስጥ የባንክ ማስተላለፊያዎች ናቸው።, ,creditcard,

ኢትዮጵያ ውስጥ ከፓክስፉል ክሪፕቶከረንሲን እንዴት መግዛት እንደሚቻል

ኢትዮጵያ ውስጥ ከፓክስፉል ክሪፕቶከረንሲን ለመግዛት የሚከተሉትን ደረጃዎች ተከተሉ:

 • የፓክስፉል ድረ ገጽ ላይ ተመዝገቡና (ሳይን አፕ) የራሳችሁን አካውንት አረጋግጡ።
 • ፕላትፎርሙ ላይ ክሪፕቶ ሻጮችን ፈልጉና ደንቡና ሁኔታዎቹ የተስማማችሁን መልካም ስም ያለውን ሻጭ ምረጡ።
 • አንዴ በምርጫችሁ ከተስማማችሁ ወይም ከረካችሁ ያረጋገጣችኋቸውን ዘዴዎች በመጠቀም ክፍያውን መፈጸም ትችላላችሁ፤ በዚያው ቅጽበትም ክሪፕቶዎቻችሁ ይደርስዋችኋል።

ሎካልቢትኮይንስ በኢትዮጵያ

localbitcoinsethiopia

ኢትዮጵያ ውስጥ ቢትኮይንን ለመግዛት ሌላኛው ጥሩ አማራጭ ሎካልቢትኮይንስ ነው። በሎካልቢትኮይንስ ፕላትፎርም አማካኝነት የባንክ ማስተላለፊያን ወይም ጥሬ ገንዘብን በመጠቀም ቢትኮይንን መግዛት ትችላላችሁ።

በሎካልቢትኮይንስ ፕላትፎርም ላይ ክሪፕቶ ሻጮች ቢትኮይኖችን ከሌሎች ወይም ለሌሎች ተጠቃሚዎች ለመግዛት ወይም ለመሸጥ የክፍያ ዘዴን እና የግብይት ዋጋን ለመምረጥ ማስታወቂያዎችን ይለጥፋሉ። ፕላትፎርሙ ክፍያ እስኪፈጸም እና ሻጩም ቢትኮይኖቹን ለገዢው እስኪለቅ የቢትኮይኖቹን ደህንነት ለመጠበቅ ገዢንም ሆነ ሻጭን ለመከላከል ኤስክሮውን ይጠቀማል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ሎካልቢትኮይንስ ቢትኮይንን ለመላክም ሆነ ለመቀበል የምትችሉበትን ካስቶዲያል ዋሌት ያቀርባል።

የክሪፕቶከረንሲ ዋሌታችሁ በ “ግል ቁልፎች” (የይለፍ ቃል ወይም ፓስወርድ አይነት ነው) ይጠበቃል። የራሳችሁን ክሪፕቶከረንሲ በግል ቁልፋችሁ (የይለፍ ቃል ባለው ማለት ነው) ዋሌት ውስጥ እንድታስቀምጡ እንመክራለን። እንደ ሎካልቢትኮይንስ ያሉ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያዎች የራሳቸው የሆነና እናንተም ቢትኮይኖን ሊያስቀምጡባቸው የሚችሉበት ዋሌት ሊኖራቸው ይችላል፤ ሆኖም በእነዚህ ላይ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር አይኖራችሁም። በክሪፕቶ ማህበረሰብ ገጽ ላይ እንደተገለጸውም፣ “ቁልፎችዎ ከሌሉ ሳንቲሞችዎም የሉም።”

ኢትዮጵያ ውስጥ ከሎካልቢቲኮይንስ ኢትዮጵያ ክሪፕቶከረንሲን እንዴት መግዛት እንደሚቻል

ቢትኮይንን ከሎካልቢትኮይንስ ለመግዛት የሚከተሉትን ደረጃዎች ተከተሉ:

 • ነፃ አካውንት እንዲኖራችሁ ተመዝገቡ።
 • አካውንታችሁ አንዴ ከተረጋገጠ፣ የገንዘቡን መጠን፣ አይነቱን፣ እና የክፈያ ስልቱን እንዲሁም ስፍራውን በመዘርዘር ክሪፕቶዎቻችሁን መግዛት ትችላላችሁ።
 • እንደምርጫችሁ የክሪፕቶ ሻጮችን ዝርዝር ለማጣራት ‘ፍለጋ’ የሚለውን ተጫኑ።
 • ትክክለኛውን የአቅርቦት ቃል (ኦፈር) ካገኛችሁ በኋላ ራሱኑ ተጫኑት፣ ከዚያም ስለክፍያ ያሉትን መመሪያዎች ተከተሉ።
 • በሎካልቢትኮይንስ ዋሌታችሁ ውስጥ ክሪፕቶዋችሁ ይገባል። ክሪፕቶዋቻችሁን ወደ ውጫዊ ዋሌትም ማዞር ወይም መውሰድ ትችላላችሁ።

 

በቴሌግራም ቢትኮይን ይግዙ

 • በአሁኑ ወቅት ፈጣን የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያ ወይም ሜሴጂንግ አፕ የሆነውን የቴሌግራም ኦንላይን ቻነልን በመጠቀም የዲጂታል ገንዘብን ወይም ክሪፕቶከረንሲን ኢትዮጵያ ውስጥ መቀበል፣ ልውውጥ ማካሄድ፣ እና ወደሌሎች ዋሌቶች መላክ ይቻላል። አሁን ላይ ግን እናንተ በባንክ ካርድ መግዛት ብቻ ነው መግዛት የምትችሉት።
 • ፕላትፎርሙን ለመጠቀም የሚከተለውን አካሄድ ይከተሉ፤ የቴሌግራም ሜሴንጄርን ይክፈቱና “ዋሌት” የሚለውን ይፈልጉ። የቴሌግራም ይፋዊ ዋሌት ቦት ይክፈቱ፣ ከዚያም “ስታርት/start” የሚለውን ከነኩ በኋላ እንደፍላጎትዎ ማለትም ዲጂታል ገንዘብን ወይም ክሪፕቶከረንሲን መግዛት፣ መላክ፣ መቀበል ወይም ደግሞ ማስቀመጥ የሚሹ ከሆነ ከተዘረዘሩት ውስጥ ይምረጡ።

ስፔክትሮኮይን በኢትዮጵያ

spectrocoinethiopia

ስፔክትሮኮይን የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ እና የቢትኮይን ዋሌት ነው። በፕላትፎርሙ ላይ ቢቲኮይንን ጨምሮ ከ 50 በላይ ክሪፕቶከረንሲዎችን መግዛት ትችላላችሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶከረንሲን በስፔክትሮኮይን ለመግዛት ያሉ ደጋፊ የክፍያ ዘዴዎች ቪዛን እና ማስተርካርድን ያካትታሉ።

ስለ ስፔክትሮኮይን በጣም አስገራሚው ነገር የአውሮፓን የዓለም አቀፍ የባንክ አካውንት ቁጥር ማረጋገጫ (አይቢኤኤን) ያለው የአውሮፓ ነዋሪ ያልሆነ አካውንትን ልታገኙ መቻላችሁ ነው። ከዚህ በተጨማሪም፣ ክሪፕቶከረንሲያችሁን በክሪፕቶ የሚደገፍ ብድር ለማግኘትም ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ። IBAN, crypto የሚደገፉ ብድሮች.

በኢትዮጵያ ውስጥ በስፔክትሮኮይን ክሪፕቶከረንሲዎችን እንዴት መግዛት እንደሚቻል

ክሪፕቶዎችን ከስፔክትሮኮይን ፕላትፎርም ላይ የመግዛት ሂደት ቀላል እና ቀጥተኛ ነው:

 • የመመዝገቢያ ቅጹን ወይም ፎርሙን በመሙላት አካውንት ክፈቱ።
 • ምዝገባውን ከጨረሳችሁ በኋላ የማረጋገጫ መልዕክት በኢሜይል አድራሻችሁ ይደርሳችኋል።
 • አካውንታችሁ አንዴ ከተረጋገጠ፣ ከአካውንታችሁ የማጠራቀሚያ ክፍል በጣም አመቺ የሆነውን አማራጭ በመምረጥ ክሪፕቶውን ወይም የመንግስት ማዕከላዊ ባንክ የሚያትመውን ገንዘብ ማጠራቀም (ዲፖዚት) ማድረግ ትችላላችሁ። ገንዘቦቻችሁም ወዲያው በስፔክትሮኮይን ዋሌታችሁ ላይ ይመጣል።
 • ቢትኮይን ለመግዛት፣ የአካውንታችሁ ክፍል ላይ “መገበያያ” የሚለውን ክፈቱ፣ ከዚያም የምትፈልጉትን የቢትኮይን መጠን አስገቡ እና ደረጃዎቹን ወይም ቅደም ተከተሎቹን ተከተሉ።

 

ፑርሳ መገበያያ በኢትዮጵያ

pursaethiopia

ፑርሳ ኢትዮጵያ ውስጥ በባንክ በማስተላለፍ እና በዴቢት ወይም በክሬዲት ካርድ ቢቲኮይንን በፍጥነት ለመግዛት ከሚያስችሉ ምርጥ መገበያያዎች አንዱ ነው። ፑርሳ በፕላትፎርሙ ላይ ገንዘብ ማጠራቀም ወይም ማስቀመጥ ሳያስፈልጋችሁ ለመገበያየት የሚያስችላችሁ የመገበያያ መላ ነው። ከፕላትፎርሙ ላይ ለመግዛት በመጀመሪያ ወርልድሬሚትን፣ ዌስተርን ዩኒየንን፣ መኒግራምን፣ በባንክ ማስተላለፍን እና ዴቢት/ክሬዲት ካርድን በመጠቀም ገንዘብ ማስገባት ይኖርባችኋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ በፑርሳ መገበያያ ክሪፕቶዎችን እንዴት መግዛት እንደሚቻል

 • የኢሜይል አድራሻችሁን አስገቡ። በኢሜይል አድራሻችሁም የማረጋገጫ ኮድ ይደርሳችኋል።
 • ኢሜይላችሁ ላይ ካረጋገጣችሁ በኋላ የራሳችሁን አጭር ግለ ታሪክ ወይም ፕሮፋይል መሙላት እና ዘወትር የምትጠቀሙበትን ገንዘብ (ዲፎልት ከረንሲ) መምረጥ ይኖርባችኋል።
 • አካውንታችሁ ላይ ባለ 6 ዲጂት ፒን ኮድ አስገቡ፣ ይህም ወደ ፑርሳ ዳሽቦርድ ይወስዳችኋል።
 • “ቢቲኮይን መግዛት” የሚለውን ተጫኑ እና የክፍያ ዘዴውን ምረጡ፣ የሚፈልጉትን መጠን በኢትዮጵያ ብር ስታስገቡ ወዲያው የቢቲኮይን ዋጋውን ያሳያችኋል።
 • የቢቲኮይን ዋሌታችሁን አድራሻ አስገቡ እና ካስገባችኋቸው ገንዘቦች ላይ በፍጥነት ግዢዉን ፈጽሙ።

 

የሎካልክሪፕቶዎች መገበያያ በኢትዮጵያ

localcryptosethiopia

ሎካልክሪፕቶስ በራሳችሁ ሙሉ ቁጥጥር ስር (non-custodial) ዋሌቶችን እና በራሳችሁ የምትቆጣጠሩትን ኤስክሮው ሲስተም በመጠቀም አክሪፕቶን (acrypto) ለመግዛት የሚያስችላችሁ የአቻ ለአቻ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ ነው። እንደ በራስ ቁጥጥር ስር ያለ የአቻ ለአቻ የመገበያያ ስፍራነቱም፣ ሎካልክሪፕቶስ የክሪፕቶዋችሁን ቁልፎች አይዛቸውም። ሎካልክሪፕቶስ በራሳችሁ ሙሉ ቁጥጥር ስር (non-custodial) ዋሌቶችን እና በራሳችሁ የምትቆጣጠሩትን ኤስክሮው ሲስተም በመጠቀም አክሪፕቶን (acrypto) ለመግዛት የሚያስችላችሁ የአቻ ለአቻ የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ ነው። እንደ በራስ ቁጥጥር ስር ያለ የአቻ ለአቻ የመገበያያ ስፍራነቱም፣ ሎካልክሪፕቶስ የክሪፕቶዋችሁን ቁልፎች አይዛቸውም።

ክሪፕቶዎችን ከሎካልክሪፕቶስ ስትገዙ በቀጥታ ከሌላ ሰው ጋር ትገበያያላችሁ። ይህም የክፍያ ዘዴውን በተመለከተ የምትነጋገሩት እናንት ሁለታችሁ ናችሁ ማለት ነው። ደጋፊዎቹ የሆኑት ክሪፕቶከረንሲዎችም ቢትኮይን፣ ኤተሪየም፣ ላይትኮይን፣ ዳሽ እና ቢትኮይን ካሽ ናቸው።

ኢትዮጵያ ውስጥ በሎካልክሪፕቶስ መገበያያ ክሪፕቶዎችን እንዴት መግዛት እንደሚቻል

 • አካውንታችሁን በነፃ መክፈት ይኖርባችኋል።
 • አንዴ አካውንታችሁ ከተረጋገጠ፣ የሚመቻችሁን ሻጭ ፈልጉ ወይም የራሳችሁን ማስታወቂያ አውጡ ወይም ለጥፉ። የሚቀርቡላችሁን ዋጋዎች በክፍያ ዘዴ፣ በገንዘብ (ከረንሲ)፣ በዋጋ፣ በቦታ እና በሌሎችም መስፈርቶች ማጣሪያ ልታደርጉባቸው ትችላላችሁ።.
 • ደስ የተሳኛችሁበትን ሻጭ ስታገኙ፣ መግዛት የምትፈልጉትን መጠን ምረጡ፣ ከዚያም የመገበያያ ዋጋውን ቆልፉት (ይህ በእንግሊዘኛው አነጋገር lock in an exchange rate ይባላል)።
 • ሌላኛው ወገን ማስታወቂያው ማለትም የቆለፋችሁት የመገበያያ ዋጋ ስለሚደርሰው ወዲያው ምላሹን ትሰማላችሁ ወይም ታውቃላችሁ።
 • ሻጩ ክሪፕቶውን በኤስክሮው አካውንት ላይ ካስቀመጠ በኋላ እርስዎ ከፕላትፎርሙ ውጪ ለሻጩ ይከፍላሉ። ማዕከላዊ ቁጥጥር የሌለበት (ዲሴንትራላይዝድ) አካውንት ክፍያው እስኪፈጸም ድረስ ክሪፕቶውን በአደራ ያስቀምጣል። ይህ ሁለቱም ወገኖች ቃላቸውን አክብረው መጠበቃቸውን ያረጋግጣል።
 • ሻጩ ክፍያው መፈጸሙን አንዴ ሲያረጋግጥ፣ ክሪፕቶው ከኤስክሮው ይለቀቅ እና የእርስዎ ክሪፕቶ ዋሌት ውስጥ ይገባል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የቢትኮይን የግብይት ዋጋ

የቢትኮይን የግብይት ዋጋን የሚወስነው ምን እንደሆነ ለማወቅ ሳትፈልጉ አትቀሩም፤ በርካታ ነገሮች የቢትኮይኖችን ዋጋዎች ለመወሰን ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ። ዋነኛው ፍላጎት እና አቅርቦት ነው። ፍላጎት ሲጨምር፣ የግብይት ዋጋዎችም ከፍ ይላሉ፤ ፍላጎት ሲቀንስ ደግሞ፣ የግብይት ዋጋዎች ይወርዳሉ። ሌሎች ምክንያቶች ደግሞ የወለድ ማደግ የሚፈጥራቸው ሁኔታዎች፣ በአንድ አገር ውስጥ በቢትኮይኖች ላይ የሚደረጉ ቁጥጥሮችን፣ እንዲሁም ተንታኞች የቢትኮይን ዋጋዎችን በተመለከተ የሚሰጡት ትንበያዎችንም ያካትታሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ክሪፕቶን ከመግዛታችሁ በፊት፣ ለመጠቀም ስላሰባችሁት የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ የክፍያ መዋቅር ራሳችሁን በሚገባ ማስተዋወቃችሁን አረጋግጡ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ስለክሪፕቶከረንሲ የመጨረሻ ሃሳቦች

በኢትዮጵያ ውስጥ የክሪፕቶከረንሲ ንግድ ላይ መንግስት ቁጥጥር አያደርግም፣ በመሆኑም ነጋዴዎች ሊከሰቱ ከሚችሉ የክሪፕቶ ማጭበርበሮች ራሳቸውን ለመጠበቅ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ሆኖም ግን፣ ሰዎች ከቢቲኮይን ንግድ እና ከቢቲኮይን ኢንቨስትመንት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ገንዘቦችን እየሰሩ ነው፤ እናንተም ከእነዚህ ሰዎች አንዱ ልትሆኑ ትችላላችሁ። እናንተ ማድረግ ያለባችሁ በምትገበያዩበት ወቅት ሁሉ ከፍተኛ ትጋት ማሳየት ነው።