የትብብር ወይም የቁርኝት የግብይት ስራ ገንዘብ ማስገኘት ይችላልን? የትብብር ወይም የቁርኝት ግብይት ስራ በአሁኑ ጊዜ በኦንላይን ላይ ገንዘብ ለማግኘት በጣም ታዋቂ ከሆኑ መንገዶች መካከል አንዱ ነው። ስለዚህ ርዕሰ ጉዳይ መረጃዎችን ስታስሱ፣ እንዴት እንደሚሰራ ጠቃሚ ምክሮችን እና መመሪያዎችን የሚሰጡ በጣም ብዙ ሰዎችን ታገኛላችሁ። አንዳንድ ‘ሚሊየነሮች’ም በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ ግብይት እንዴት ሀብታቸውን እንደገነቡ ሲናገሩ ታያላችሁ። ሁሉም በንግግራቸው ድምፀት ይኽንን ስራ ቀላል ቢያስመስሉትም እውነታው ግን ይኽ አይደለም። ይህ ጽሑፍም በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ የግብይት ስራ ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ማብራሪያዎችን ያቀርብላችኋል።
በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ የግብይት ስራ ገንዘብ ስለማግኘት በቅድምያ የተሰጡ ማሳሰቢያዎች
በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ የግብይት ስራን እንዴት መጀመር እንደምትችሉ ከማብራራታችን በፊት ማወቅ ያለባችሁ ጥቂት ማሳሰቢያዎች እንደሚከተለው እናሳውቃችሁ።
- በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ የግብይት ስራ በፍጥነት ሀብታም የሚኮንበት እቅድ አይደልም።
- ይኽ የንግድ ስራ በእርግጥ ገንዘብ ማስገኘት ከመጀመሩ በፊት የበዛ ጊዜን ሊፈጅ ይችላል።
- በትብብር ወይም በቁርኝት የብይት ስራን እንደሚሰሩ የንግድ ሰዎች ገንዘብ ለማግኘት ወይም ለመስራት ጊዜን ወይም ገንዘብን የመሳሰሉ የበዙ ሀብቶችን ሊጠይቃችሁ ይችላል።
- በትብብር ወይም በቁርኝት የሚሰራ የግብይ ስራን የጀመሩ በዙ ሰዎች ስኬታማ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በዚህ የንግድ ስራ ስኬታማ ለመሆን፣ ዋነኞቹ ብልሃቶች ሳይታክቱ መትጋት እና ፈጠራ የታከለበት እውቀት መኖር ናቸው።
ይኽን ማሳሰቢያ ካሳወቅናችሁ ዘንድ፣ ከዚህ በታች ደግሞ በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ የግብይት ስራ ገንዘብ ለማግኘት መከተል የሚገቧችሁን ደረጃዎች ልብ ማለት ይኖርባችኋል።
Contents
በትብብር ወይም በቁርኝት ስለሚሰራ የግብይት ስራ ምንነት
ኩባንያዎች ምርቶቻቸውን በኦንላይን ላይ ሲያገበያዩ ብዙ አማራጮች አሏቸው። አንደኛ፣ የተለመዱትን በየአንዳንዱ ጠቅታ ክፍያ የማድረግን እና ለእያንዳንዱ በተሰጠ አስተያየት ወይም የስሜት መጠቆሚያ ምስል ወይም የተሰጠ አስተያየትን መሰረት ያደረጉ ዘዴዎችን ሊጠቀሙ ይችላሉ። እነዚህን በተመለከተ ጥቂት ነጥቦችን እንደምሳሌ እናቅርብ። በየአንዳንዱ ጠቅታ ክፍያ ማድረግ (ወይም በእንግሊዘኛው pay per click) የሚባለውን የክፍያ ዘዴ በምሳሌ ለማስረዳት፣ አንድ ድርጅት በሆነ ድረ ገጽ ላይ ማስታወቂያው እንዲታይለት ሊለጥፍ ይችላለ፤ ታድያ አንድ ሰው ድረ ገጹን ሲጎበኝ ማስታወቂውን ጠቅ (click) አድርጎ በተመለከተ ቁጥር የድረ ገጹ ባለቤት ከማስታወቂያ አስነጋሪው ድርጅት ክፍያ ያገኛል ማለት ነው።
በሌላ በኩል፣ የስሜት መጠቆሚያ ምስል ወይም የተሰጠ አስተያየትን መሰረት ያደረገ የክፍያ አፈጻጸም ዘዴ (Pay-per-impression) ደግሞ እንመልከት። አንድ “መታየት” ወይም “የስሜት” ማሳያ (ወይም በእንግሊዘኛው ‘impression’) የሚባለው አንድ የድረ ገጽ ተጠቃሚ ሰው ድረ ገጹን ሲጎበኝ በገጹ ላይ የሚታየውን ማስታወቂያ ያመለክታል። አንድ የድረ ገጽ ተጠቃሚ ማስታወቂያው የታየበትን ገጽ በጎበኘ ቁጥር ይህ አንድ እይታን ይወክላል። አንድ ማስታወቂያ አስነጋሪ ድርጅት የድረ ገጹ ጎብኚ ማስታወቂያውን ጠቅ አድርጎ ይመልከትም አይመልከትም የተለጠፈው ማስታወቂያ ከጎብኚዎች በተሰጡት እያንዳንዱ አንድ ሺህ ኢምፕሬሽን ወይም አስተያየት የድረ ገጹ ባለቤት ከማስታወቂያ አስነጋሪው ድርጅት ክፍያ የሚያገኝበት ዘዴ ነው። እንደ ጎግል፣ ትዊተር እና ፌስቡክ ያሉ ኩባንያዎች በእነዚህ ዘዴዎች አማካኝነት በርካታ ገቢዎችን ከማስታወቂያ አስነጋሪ ድርጅቶች ይሰበስባሉ።
ኩባንያዎቹ የሚጠቀሙበት ሌላኛው አማራጭ መላ ደግሞ፣ ከድረ ገጽ ባለቤቶች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች (ታዋቂ ሰዎችም ሊሆኑ ይችላሉ) የአጋርነት ጥምረት በመፍጠር እነዚህ አካላት ደንበኞችን ወደ ኩባንያዎቹ እንዲያመጡላቸው የሚያደርጉበት ነው። እነዚህ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በቁርጥ የተወሰነ የገንዘብ መጠን ሊከፈላቸው ወይም ለተሸጡት እቃዎች ሁሉ ቅናሽ ሊያገኙ ይችላሉ። ይህ ስልት ወይም ስትራተጂ ነው እንግዲህ በትብብር ወይም በቁርኝት የሚካሄድ ግብይት በመባል የሚታወቀው።
በኦንላይን ላይ ራሳችሁን ማኖር ወይም ማስገኘት የሚገባችሁ ስለመሆኑ
እንደ አንድ የግብይት ስራ ተባባሪ በመሆን ገንዘብ ለማግኘት ራሳችሁን በኦንላይን ማኖር የምትችሉበትን መላ ማበጀት አለባችሁ። ይኽን ለማድረግ ደግሞ መጠቀም የምትችሏቸው ሁለት መንገዶች አሉ።
- ስለኢንዱስትሪው (ማለትም በትብብር ወይም በቁርኝት ሰለሚካሄድ ግብይት) ያሏችሁን አስተያየቶች ወይም አመለካከቶች የምታገሩበት የግላችሁን ደረ ገጽ መፍጠር ወይም መገንባት ትችላላችሁ። ይኽን የማድረጋችሁም ግቡ ብዙ ተከታዮችን ማፍራት ነው። ድረ ገጻችችሁን በማህበራዊ ሜዲያው ላይ ማስተዋወቅ ወይም/እና የመረጃ መፈለጊያ ማመቻቻ ወይም ማስማሚያ (ሰርች ኤንጅን ኦፕቲማይዜሽን/ SEO) ስትራተጂ ማዘጋጀት ትችላላችሁ።
- በተሰማራችሁበት ዘርፍ ላይም ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን ትዊትውር፣ ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ስናፕቻት፣ ኢንስታግራም እና ቲክቶክን የመሳ ሰሉ የማህበራዊ ሜዲያ መድረኮች ማለትም ፕላትፎርሞችን መጠቀም ትችላላችሁ። ራሳችሁን በኦንላይን ላይ የማኖር ወይም የማስገኘት መላን የመገንባቱ ምክንያት እንደ አንድ የኦንላይን የትብብር ወይም የቁርኝት ግብይት ተዋናይ ራሳችሁን ስኬታማ ለማድረግ ቁጥራቸው እጅግ የበዛ ተከታዮችን ማፍራት እጅግ የግድ የግድ መሆኑ ነው። ይኽን ሳያደርጉ በዘርፉ ስኬታማ ለመሆን ከቶም የሚቻል አይሆንም።
ጥራት ያለው እና ደረጃውን የጠበቀ የግል የትብብር ግብይት ስራ ድረ ገጽን ስለመገንባት አንዳንድ ጠቃሚ ጥቆማዎች
ጥራት ያለው እና ደረጃውን የጠበቀ የግል የግል የትብብር ግብይት ስራ ድረ ገጽን የመገንባቱን ስራ ስኬታማ ማድረግ በጣም ከባድ ነው። ስኬታማ ለመሆን፣ ድረ-ገጹን ለማሰስ ወይም በድረ ገጹ ላይ መረጃ የመፈለግ ተግባርር ቀላል መሆኑን ማረጋገጥ አለባችሁ። ስለዚህ፣ እንደ SquareSpace እና WordPress ያሉ የተለመዱ ፕላትፎርሞችን እንድትጠቀሙ እንመክራለን። እነዚህ ፕላትፎርሞች ድረ ገጻችሁ ቀላል እና በባህሪይውም በፍጥነት ምላሽ ሰጪ መሆኑን ያረጋግጣሉ።
ድረ ገጻችሁ ለመረጃ መፈለጊያ ኤንጂኖች በጥሩ ሁኔታ የተመቻቸ ወይም የተስማማ ሊሆን ይገባዋል። ለመረጃ መፈለጊያ ኤንጂኖች በጥሩ ሁኔታ የተመቻቸ ወይም የተስማማ ድረ ገጽ ፈልጎ ለማግኘት ቀላል ከመሆኑም ባሻገር ከግብይት ስራውም ብዙ ገንዘብ እንድታገኙ ያስችላችኋል። ጥሩ የሆነ የመረጃ መፈለጊያ ማመቻቻ ወይም ማስማሚያ (ሰርች ኤንጅን ኦፕቲማይዜሽን/ SEO) ስትራተጂ መኖር ትኩረት ባደረጋችሁበት ስራ ላይ ተፈላጊና ከፍ ያለ እውቀት እንዲኖራችሁ ያግዛችኋል።
ጥሩ የሆነ የመረጃ መፈለጊያ ማመቻቻ ወይም ማስማሚያ (ሰርች ኤንጅን ኦፕቲማይዜሽን/ SEO)
ጥሩ የሆነ የመረጃ መፈለጊያ ማመቻቻ ወይም ማስማሚያ (SEO) የመረጃ ማፈላለጊያ ሮቦቶች ይዘታችሁን (content) በመልካም መዋቅራዊ መንገድ ለማመላከት ማስቻላቸው ብቻ ሳይሆን አድማጮቻችሁን ወይም ደንበኞቻችሁን እንዴት ማስተናገድ እንደምትችሉ ጭምር ታውቃላችሁ ማለትም ነው። እዚህ ላይ እንግዲህ መመሪያው፡ ጎብኚዎቻችሁ ምን እንደሚፈልጉ ማወቅ ወይም መረዳት እና በእናንተ አማካኝነት የሚፈልጉትን ማግኘታቸውንም ማረጋገጥ የግድ መሆኑ ነው። ጎብኚዎቻችሁን በመልካም ሁኔታ ስታገለግሉ የመፈለግ ደረጃዎቻችሁ ይሻሻላሉ፤ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ የመረጃ ማፈላለጊያው አልጎሪዝሞች ተጠቃሚዎች የሚሰጧቸውን ግብረ-መልሶች (feedback) ከግምት ስለሚያስገቧቸው ነው።
ይኽን ንዑስ ርዕስ ለመደምደም፣ እንደ ስማርት ስልኮች ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማስተዋወቅ ገንዘብ ማግኘት ቢቻልም፣ ስኬታማ የመሆን ዕድላችሁ ግን እጅግ ውስን ነው። ምክንያቱም እነዚህ ምርቶች ኩባንያዎችን ወክለው ለገበያ የሚያቀርቡ ተዓማኒነት ያላቸው ተፅዕኖ ፈጣሪዎች አስቀድሞ ስላሏቸው ነው። ስለሆነም፣ በምትኩ፣ እንደ ኩሽና ቢላዋ ወይም ተመሳሳይ በሆኑ አነስተኛ ገበያዎች ላይ ትኩረት ልታደርጉ ትችላላችሁ። በእነዚህ ገበያዎች ላይ መልካም ስማችሁን ከገነባችሁ፣ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ነገር ግን ብዙ ገንዘብ የሚያወጡ ደንበኞችን ወደ እናንተ መሳብ ትችላላችሁ።
ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን የሚያግዙ ጥቆማዎች
ቴክኖሎጂ ነክ ነገሮችን ከወደዳችሁ፣ እንደ Linus Tech Tips፣ MKBHD፣ እና Unbox Therapy ያሉ የዩቲዩብ ቪዲዮዎችን አይታችሁ ይሆናል። እነዚህ ዩቲዩበሮች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች አሏቸው፤ በዚህም ምክንያት ከዩቲዩብ ገቢ በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ያገኛሉ። ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር ይሰራሉ። በእርግጥም፣ OnePlus የመሳሰሉ የስልክ ብራንዶች በእነዚህ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አማካኝነት እጅግ ለማደግ ችለዋል። እናንተም በየራሳችሁ ገበያዎች ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሆን ትችላላችሁ። ለዚህ ደግሞ፣ የሚከተሉትን ጠቃሚ ጥቆማዎች መከተል ተገቢ ይሆናል:
- ለተመልካቾች እሴት (value) የሚጨምሩ ጥራት ያላቸው ቪዲዮ ማዘጋጀት።
- በጣም ጥሩ የሆኑ የተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) እና የድምፅ ወይም ኦዲዮ ውጤቶች ላይ ኢንቬስት ማድረግ።
- ስራን በጽናትና ያለመዛነፍ መስራት። በየሳምንቱ ቢያንስ አንድ ቪዲዮ መጫናችሁን (upload) ማረጋገጥ አለባችሁ።
- ሁሌም ተከታዮቻችሁን እንዲመለከቷችሁ አስታውሷቸው።
- በስራቸው ላይ ጥሩ ውጤት እያመጡ ያሉ ዩቲዩበሮች ይዘቶቻችሁን ለተከታዮቻቸው እንዲያሳዩላችሁ ጠይቋቸው።
ከዚያስ?
ራሳችሁን እንደ አንድ ብራንድ ማቋቋም ከቻላችሁ በኋላ፣ በትብብር ወይም በቁርኝት ግብይት ስራ ገንዘብ ለመስራትየኢትዮጵያ አየር መንገድከመሰሉ በትብብር ወይም በቁርኝት ግብይት ስራ ላይ ገንዘብ የሚያወጡ ኩባንያዎችን መፈለግ ይገባችኋል። የቁርኝት ወይም የትብብር ግብይት ፕሮግራሞችን የሚፈልጉ በርካታ ኩባንያዎች አሉ። ምንም እንኳን ትላልቅ ኩባንያዎች ራሳቸው የሚመሯቸው ወይም የሚያስተዳድሯቸው የቁርኝት ወይም የትብብር ግብይት ፕሮግራሞች ቢኖሯቸውም እናንተም ቁጥራቸው የበረከተ የቁርኝት ወይም የትብብር ግብይት ፕሮግራሞችን ወይም ትስስሮችን (affiliate networks) ማግኘትም ትችላላችሁ።
በጣም በርካታ የቁርኝት ወይም የትብብር ግብይት ትስስሮሾች አሉ። ግንባር ቀደም የሆኑትም የሚከተሉት ናቸው:
ሌላው አማራጭ መንገድ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሀገር ውስጥ ብራንዶችን ራሳችሁ ግንኙነት በመፍጠር ማነጋገር ነው። ለዚህ ደግሞ፣ አብረዋችሁ የሚሰሩ የኩባንያዎችን የሽያጭ ኃላፊዎች መገናኘት እና ብሎጋችሁን ወይም የማህበራዊ ሜዲያ ፕላትፎርማችሁን እንደ የእነሱ ተቀጽላ የግብይት ፕላትፎርም እንዲያደርጉላችሁ መጠየቅ ነው።
ለጎብኚዎቻችሁ እነሱ በጎበኟቸው ሊንኮች ገንዘብ እንደምታገኙ ልትነግሯቸውና ታማኝ መሆንን ልትመርጡ ትችላላችሁ።
በትብብር ወይም በቁርኝት በሚሰራ ግብይት ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል መረዳትን በተመለከተ የመጨረሻ ሃሳቦች
የትብብር ወይም የቁርኝት ግብይት ስራ ቢዝነሳችሁን ለማሳደግ ጠቃሚ ዕድልን ወይም አጋጣሚን ይሰጣችኋል። ይኽ የግብይት ስራ በጊዜ ሂደት ውስጥ ገንዘብ ከሚሰራባቸው ዘዴዎች መካከል ምርጡ ነው። ሆኖም ግን፣ ከላይ ለማብራራት እንደሞከርነው፣ ስኬታማ የትብብር ወይም የቁርኝት ግብይት ስራ ተዋናይ መሆን በራሱ እንደ አንድ ረጅም ጉዞ ነው። በዚህም ጉዞ ስኬታማ መሆን ወራትን እና አመታትን ይጠይቃል። ያልተቆጠበና ያልተቋረጠ ጥረት ካደረጋችሁ ግን፣ በረጅም ጊዜ ውስጥ በርካታ ገንዘብን ለመስራት ራሳችሁን በመልካም ስፍራ ላይ ታስገኙታላችሁ።