አፕዎርክ ፕላትፎርም ላይ ገንዘብ ልትሰሩ ትችላላችሁን?አፕዎርክ? መልሱ በእርግጠኝነት አዎ የሚል ነው። የሌላ ሰው ተቀጣሪ ሳትሆኑ ማለትም በፍሪላንሰርነት በአፕዎርክ ፕላትፎርም ላይ ገንዘብ መስራት ከፈለጋችሁ መጀመር ያለባችሁ የአፕዎርክ አካውንት በመክፈት ነው። ይህን አካውንት በነፃ መክፈት ትችላላችሁ።
Contents
አፕዎርክ ምንድን ነው?
እ.ኤ.አ. 2013 ዓ.ም. ላይ ኤላንስ እና ኦዴስክ የተባሉ ፕላትፎርሞች በመዋሃድ ኤላንስ-ኦዴስክ የተሰኘ ኩባንያ መስርተው ነበር። በ 2015 ይኼ ኩባንያ ስሙን በመቀየር አፕዎርክ ተባለ። ይህ አፕዎርክ የተባለው ኩባንያ የተመዘገቡ ደንበኞችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍሪላንሰሮች ጋር የማገናኘት ስራን ያከናውናል። አፕዎርክ በፕላትፎርሙ ላከናወነው ለእያንዳንዱ የማገናኘት ስራ ክፍያን ያስከፍላል። ከቅርብ አመታት ወዲህ፣ ኩባንያው ከፍተኛ እድገት በማሳየቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በይፋ ሊታወቅ ችሏል። በአሁኑ ወቅት ይህ ኩባንያ 1.8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ አለው። ከ 475 ሺህ በላይ ደንበኞች እና ከ 1 ሚሊዮን በላይ ፍሪላንሰሮች አሉት።
አፕዎርክን መጠቀም ለምን አስፈለገ?
አፕዎርክ ለሚሰራው ስራ የሚያስከፍለው ክፍያ ከፍተኛ ቢሆንም፣ እንደ አንድ ፍሪላንሰር ገንዘብ ለመስራት ሊያግዟችሁ ከሚችሉ አማራጮች ውስጥ ዋነኛውና እጅግ ተመራጩ ነው። ይህ ደግሞ የሆነው በበርካታ ምክንያቶች ነው፡
- ከ 5000 በላይ ክህሎቶች። ይህ ካሉት 5000 በላይ ክህሎቶች በአንደኛው ገንዘብ መስራት ትችላላችሁ ማለት ነው። ከእነዚህ ክህሎቶች ውስጥ መሳሌዎችን ለመጥቀስ ያህል፣ የፈጠራ ጽሁፍ፣ የመረጃ መፈላለጊያ (ማለትም ሰርች ኤንጅን ኦፕቲማይዜሽን) አገልግሎቶች፣ የሂሳብ አያያዝ ወይም አካውንቲን፣ እና ፕሮግራሚንግ ክህሎቶች ጥቂቶቹ ናቸው።
- ለመግባት ብዙ መሰናክሎች መኖር። አፕዎርክን ስኬታማ እንዲሆን ካስቻሉት ምክንያቶች አንደኛው ወደ ቢዝነሱ ለመግባት በጣም ከባባድ የሆኑ መሰናክሎች መኖራቸው ነው። ከአፕዎርክ ጋር ተፎካካሪ የሆኑት ኩባንያዎች በአንፃራዊነት ትናንሽ በመሆናቸው በዙ ገንዘብ እንድትሰሩ አያስችሏችሁም።
- በጣም የታወቀ የንግድ ስም ወይም ብራንድ መሆኑ። ኩባንያው በራሳቸው በሚሰሩ ወይም በፍሪላንሰር ማህበረሰብ ውስጥ በጣም የታወቀ ስም ወይም ብራንድ ያለው ነው።
- ትልቅ ስም ባላቸው ኩባንያዎች መታመኑ። እንደ ድሮፕቦክስ፣ ፌስቡክ፣ ዜንዴስክ፣ እና ማይክሮሶፍት የመሳሰሉ ትላልቅ ኩባንያዎች ፍሪላንሰሮችን ለመቅጠር አፕዎርክን ይጠቀማሉ።
- ተጨማሪ መሳሪያዎችን ወይም መገልገያዎች የሚያቀርብ መሆኑ። የኩባንያው ፕላትፎርም እንደ የክፍያ መከላከያ፣ የአፕዎርክ የጊዜ መከታተያ ወይም ታይም ትራከር፣ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ የግንኙነት መሳሪያዎች የመሳሰሉ ተጨማሪ መሳሪያዎችን ወይም መገልገያዎችን ያቀርባል።
ስኬታማ የአፕዎርክ ፍሪላንሰር መሆን እንዴት እንደሚቻል
ስኬታማ የአፕዎርክ ፍሪላንሰር ለመሆን፣ የሚከተሉትን ማከናወን ይገባችኋል፡
ክህሎቶቻችሁን መለየት
አፕዎርክ ከ 5000 በላይ ክህሎቶች ያሉት በመሆኑ፣ ምርጥ ናቸው የምትሏቸውን ክህሎቶቻችሁን መለየት ያስፈልጋችኋል፤ ምክንያቱም ለደንበኞቻችሁ ስራችሁን እየወደዳችሁት ምርጥ የሆኑ አገልግሎቶችን መስጠት ስለምትሹ ነው።
ስለራሳችሁ አጠር ያለ ጥሩ መግለጫ ወይም ፕሮፋይል ማዘጋጀት
ክህሎቶቻችሁን ከለያችሁ በኋላ፣ ስለራሳችሁ የሚገልጽ አጠር ያለ ጥሩ የአፕዎርክ ፕሮፋይል ማዘጋጀት አለባችሁ። ይህ አጠር ያለ ፕሮፋይል በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም እናንተ ለስራው ካመለከታችሁ በኋላ ድንበኞቻችሁ የሚመለከቱት ሁለተኛው ጉዳይ በመሆኑ ነው። በአጭሩ፣ ስለእናንተ የሚያስረዳ ጥሩ የአፕዎርክ ፕሮፋይል፡
- >የእናንተን በጥሩ ሁኔታ የተነሳ ፎቶግራፍ ሊይዝ ይገባል።
- ምን እንደምትሰሩ በቀላሉና በግልጽ ሊያብራራ ይገባል።
- የትምህርት እና የሞያ ስራችሁን ሊያብራራ ይገባል።
- አጭር እና ሞያዊ ርዕስ ሊኖረው ይገባል።
- በጥሩ ሁኔታ የተዘጋጀ የመግቢያ ወይም መተዋወቂያ ቪዲዮ በመጨመር ለፕሮፋይላችሁ ተጨማሪ ጉልበት መስጠት መልካም ነው።
- ስለእናንተ ሊመሰክሩ ወይም ሊያስረዱ የሚችሉ የውጭ አስረጂዎችን ማካተት ይገባል።
የስራ ልምዳችሁን ፖርትፎሊዮ የሚያሳይ ሰነድ ማዘጋጀት
በፕሮፋይላችሁ ላይ ፖርቶሊዮዋችሁንም ማካተት አለባችሁ። ይህ ፖርትፎሊዮ ከዚህ ቀደም የሰራችኋቸውን ስራዎች ጥቂቶቹን ይጨምራል። ለምሳሌ፣ የመተግበሪያዎች ፈጣሪ ወይም አፕልኬሽን ዴቨሎፐርስ ከሆናችሁ፣ የሰራችኋቸውን ጥቂቶቹን መተግበሪያዎች ወይም አፕልኬሽኖች በጥሩ ሁኔታ በስዕል ወይም በፎቶ ማሳየት ማለትም ሾውኬስ ማድረግ አለባችሁ። ጸሀፊ ከሆናችሁ ደግሞ፣ የቀድሞ የጽሁፍ ስራዎቻችሁን መገኛ ሊንኮች ማቅረብ አለባችሁ። ለሌሎች ሁሉም የክህሎት ክፍሎች ይኽንኑ መፈፀም ይገባል።
የስራ ማመልከቻ
ፕሮፋይላችሁን በጥሩ ሁኔታ ካዘጋጃችሁ በኋላ፣ ከእናንተ ብቃቶች ጋር ለሚጣጣሙ ስራዎች ማመልከቻችሁን ማስገባት መጀመር አለባችሁ። ይህን ለመፈጸም የሚከተሉትን ማረጋገጥ ይገባችኋል፡
- ማመልከቻችሁ የእናንተን ምርጥ ክህሎቶች የሚገልጹ መሆኑን፤
- በማመልከቻችሁ እናንተ ከሌሎች አመልካቾች ይበልጥ የምትሻሉባቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ማሳየታችሁን፤
- በማመልከቻችሁ ከቀድሞ ስራዎቻችሁ ጥቂት ዋና ዋናዎቹን ማሳየታችሁን፤
- በማመልከቻችሁ የቀድሞ ስራዎቻችሁ የተሰነዱባቸው ሾውኬዞችን መያዛቸውን፤
- በቅድሚያ ካመለከቱት ጥቂቶቹ ውስጥ አንዱ መሆናችሁን፤
- የስራውን ዝርዝር ነገሮች ሁሉ ማንበባችሁን፤
ስራ
ዕድለኛ ሆናችሁ ደንበኛ ካገኛችሁ፣ በተቻላችሁ መጠን ከፍተኛ ጥራት ያለው ምርጥ ስራ ሰርታችሁ ማስረከብ አለባችሁ። ስለማናቸውም ነገር እርግጠኛ ካልሆናችሁ፣ ደንበኛችሁን መጠየቅ እንዳለባችሁ ማረጋገጥ ይገባችኋል። እንዲሁም ደንበኛው ስራውን ዳግም አይታችሁ ማሻሻያ እንድታደርጉበት ከጠያቃችሁ፣ በተቻለ ፍጥነት ሁሉ ይህንኑ ማድረግ አለባችሁ።
ስራውን ካጠናቀቃችሁ በኋላ፣ አዎንታዊ ደረጃን (ፖዘቲቭ ሬቲንግ) እና የራሱንም የግምገማ አስተያየት እንዲሰጣችሁ ደንበኛችሁን መጠየቅ አለባችሁ። ደንበኞች ሁሌም ቢሆን ትልቅ ደረጃዎች እና አዎንታዊ አስተያየቶች የተሰጧቸውን ፍሪላንሰሮች ይመርጣሉ።
እንዲሁም ያንብቡ: ክሪፕቶከረንሲን ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት መግዛት ይቻላል
አንድ ሌላ ተጨማሪ ጉዳይ
እንደ አንድ የአፕዎርክ ፍሪላንሰር ስኬታማ ለመሆን፣ በኩባንያው የተዘረዘሩ መመሪያዎችን መከተላችሁ የግድ ነው። ይህን ለማድረግ አለመቻል የአፕዎርክ አካውንታችሁን ሊያሰርዝ ይችላል። የተለመዱ ግን ደግሞ ማስወገድ ካሉባችሁ ጥሰቶች ወይም ስህተቶች መካከል ጥቂቶቹ እንደሚከተለው ያሉ ናቸው፡
- ከአፕዎርክ ውጪ ክፍያን እንዲፈፀም መጠየቅ፤ ይህን ማድረግ ከፍተኛ የሆነ ክፍያን ለማስወገድ ቢረዳም፣ የአፕዎርክ አካውንታችሁን ሊያሳጣችሁ ግን ይችላል።
- በውሉ መሰረት ስራን ለመፈጸም አለመቻል፤ ይህን ካደረጋችሁ፣ ደንበኞቻችሁ ቅሬታቸውን ለአፕዎርክ ሊያቀርቡ ይችላሉ፣ አፕዎርክም አካውንታችሁን ሊያሳጣችሁ ይችላል።
- አፕዎርክ የግል አድራሻዎቻችሁን ከደንበኞች ጋር እንድትለዋወጡ አይፈቅድም።
- የተሰጠን ግብረ ምላሽ አለአግባብ መጠቀም እና ደንበኞች ላይ ትንኮሳ መፈጸም።
ክፍያዬን ከአፕዎርክ የማገኘው እንዴት ነው?
አፕዎርክ ክፍያዎቻችሁን እንድታገኙ የሚያስችሏችሁን በርካታ አማራጮች አቅርቧል። ክፍያችሁ በቀጥታ ወደ ባንክ አካውንታችሁ እንዲገባላችሁ ማስደረግ ትችላላችሁ ወይም ደግሞ እንደ PayPal, Payoneer እና በኬንያም እንደ Mpesa ያሉ ሶስተኛ ወገኖች ሻጮችን መጠቀም ትችላላችሁ።
የክፍያ ዘዴዎቹ እንደ የአገሩ ይለያያል። አካውንታችሁን ስተከፍቱና yeክፍያ ዘዴውንም ስትሞሉ የክፍያ አማራጮችን ታገኛላችሁ።
የአፕዎርክ ክፍያዎች
“አፕዎርክ ገንዘብ የሚሰራው እንዴት ነው?” ብላችሁ ምናልባት ራሳችሁን ልትጠይቁ ትችሉ ይሆናል።
አፐዎርክ በነፃ መቀላቀልና ፕሮፋይልንም መፍጠር ወይም መጫን ይቻላል። ሆኖም ግን፣ እንደ አንድ ፍሪላንሰር ከእያንዳንዱ ድርጅት ያልሆነ ደንበኛ ጋር በአንዴ የሚደረግ ክፍያን (lifetime billings) መሰረት በማድረግ እንደገቢያችሁ መጠን ክፍያን እንድትፈጽሙ ይደረጋል። ውሎቹ በሰአት፣ በቁርጥ ዋጋ፣ ወይም ፕሮጀክት ካታሎጉ ላይ ባሉ ፕሮጀክቶች መሰረት ይሁኑም አይሁኑም የአገልግሎት ክፍያዎቹ ተመሳሳይ ናቸው። እነዚህም እንደሚከተለው ቀርበዋል፡
- $0 – $500፡ 20%
- $500.01 – $10,000: 10%
- $10,000.01 ወይም ከዚያ በላይ፡ 5%
የአፕዎርክ ክፍያዎች እንዴት እንደሚሰሩ፡ ከአንድ አዲስ ደንበኛ ጋር ለሚኖር የ $600 (ዶላር) ፕሮጀክት፣ የአገልግሎት ክፍያችሁ ከመጀመሪያው $500 ላይ 20% ሲሆን ከቀሪው $100 ላይ ደግሞ 10% ይሆናል። በዚህ ምሳሌ መሰረትም እናንተ እጅ የሚገባው ክፍያ $490 ይሆናል ማለት ነው።
እንደየገቢው መጠን ማስከፈል ከድርጅት ወይም ኢንተርፕራይዝ ደንበኞች ጋር ለሚደረጉ ውሎች አይሰራም። የአፕዎርክ የድርጅት ደንበኞች በቁጥር እየበዙ ከመጡ ጀማሪዎች አንስቶ እስከ ፎርቹን 500 ውስጥ ያሉ ግዙፍ ዓለም አቀፋዊ ኩባንያዎች ናቸው። አፕዎርክ ከእነዚህ ኩባንያዎች ጋር የግል ውሎችን እያንዳንዱን ጉዳይ መሰረት በማድረግ ይደራደራል። በአጠቃላይ፣ የድርጅት ወይም ኢንተርፕራይዝ ውሎች በቁርጥ የአንድ ጊዜ 10% የአገልግሎት ክፍያን ይከፍላሉ።
በግልጽ ለተፈለጉ ስራዎች (“Featured Jobs”) የተቀጠራችሁ ቶፕ ሬትድ ወይም ራይሲንግ ታለንት ከሆናችሁ፣ ዝቅ ያለ የአገልግሎት ክፍያ ትከፍላላችሁ። በግልጽ ለተፈለጉ ስራዎች (“Featured Jobs”) የሚባሉት አንድ ተነሳሽነት ያለው ደንበኛ አፕዎርክ ላይ ከሌሎች ልቆ ለመታየት እንዲረዳው በማሰብ ክፍያን ፈጽሞ የሚያስለጥፋቸው የስራ መደቦች ናቸው።
የሚከተሉት የስራ ክፍያን ከመውሰድ ጋር የተያያዙ ክፍያዎች ናቸው፤
- በቀጥታ ወደ አሜሪካ ባንክ (ኤሲኤች) ገቢ ሲደረግ – ከክፍያ ነፃ
- በቀጥታ ወደ አገር ውስጥ ባንክ ገቢ ሲደረግ – በአንድ ማስተላለፍ ወይም ትራንስፈር$0.99
- በአሜሪካ ዶላር በኤሌክትሮኒክ ዘዴ ሲተላለፍ – በአንድ ማስተላለፍ $30
- ለአሜሪካ ፍሪላንሰሮች ወዲያው ወይም በፍጥነት (Instant Pay) ክፍያ ሲደረግ – በአንድ ማስተላለፍ $2.00
አፕዎርክ ህጋዊ ነውን?
አዎ፣ አፕዎርክ ህጋዊ የኦንላይን የስራ ገበያ ስፍራ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ፕላትፎርሙ ወይም መድረኩ ላይ አጭበርባሪዎች ሊከሰቱ ይችላሉ። ፕላትፎርሙ (ከጀርባው ያለው ኩባንያ ማለት ነው) ግን ህጋዊ እና ሊታመን የሚገባ ነው። ክፍያችሁ የሚፈጸመው ራሳችሁና ደንበኛው ስራውን ከገመገማችሁት በኋላ ነው። እንደ ዕድል ሆኖ፣ ክፍያችን አልተፈጸመልንም በምትሉ ጊዜም አፕዎርክ አለመግባባትን የሚፈታበት ሂደትና አሰራር አለው።
ከአፕዎርክ ሌላ ያሉ አማራጮች
ሌሎች አማራጭ የኦንላይን የፍሮላንስ ስራዎች ፕላትፎርሞች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡
የመጨረሻ ሃሳቦች
አፕዎርክ ለአመታት በዓለም ዙሪያ ያሉ ፍሪላንሰሮችን ከቢዝነሶች እና ከግለሰቦች ጋር የሚያገናኝበትን ጠንካራ ስም ወይም ብራንድ ሲገነባ ቆይቷል። በውጤቱም፣ በርካታ ሰዎች በፍሪላንሰርነት በየአመቱ ብዙ ሚሊዮን ዶላሮችን እየሰሩ ወይም እያገኙ ነው። ከላይ የተመለከቱትን ደረጃዎችና አካሄዶች በመከተል እናንተም ስኬታማ መሆን ትችላላችሁ።