ቢዝነስ ለመጀመር ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በርካታ ተግዳሮቶች ወይም ችግሮች ያጋጥሟቸዋል። ከእነዚህ ተግዳሮቶች መካከል ዋነኛው የመነሻ ካፒታል አለመኖር ነው። በአነስተኛ ወይም ደግሞ ምንም የመነሻ ካፒታል ሳይኖር አንድ ሰው ሊያከናውናቸው የሚችሉ የቢዝነስ ስራዎች አሉ። ከዚህ በታች የተመለከቱትን ጥቂት የቢዝነስ ሃሳቦች ለእናንተም ሊሰሩ ይችላሉ።
ይህንን ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ያንብቡ: Business Ideas Without Startup Capital
1. የቢዝነስ እቅዶችን መንደፍ ወይም መቅረጽ
ብዙ ሰዎች የቢዝነስ ሃሳቦችአሏቸው፣ ነገር ግን እነዚህን የቢዝነስ ሃሳቦች ወረቀት ላይ ማስፈር አይችሉም። አንድን ቢዝነስ በገንዘብ ሊሰራ የሚመኝ ኢንቨስተር የቢዝነስ እቅድ ሊኖረው የግድ ነው። ይህ እቅድ በቢዝነሱ ውስጥ ባለ ሰው ከተፃፈ ወይም ከተነደፈ፣ ስለቢዝነሱ አስቀድመው ያልታዩ ዝርዝሮችን ሊያስቀምጥ ይችላል። ከዚያም ለተለያዩ የቢዝነስ ሃሳቦች የሚጠይቀውን ክፍያ ወስኖ ሊያስቀምጥ ይችላል።
2. በድረ ገጾች ላይ መጻፍ ወይም ተንቀሳቃሽ (ቪዲዮ) ምስሎችን ማስቀመጥ
ሰዎችን ለማሰልጠን የምትሹበት ክህሎት አላችሁን? ክህሎቱ ከምግብ ስራ ጀምሮ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ወይም ሙዚቃን መጫወት ወይም ሶፍትዌሮችን መጠቀም ሊጨምር ይችላል። ስለዚህ ክህሎት ለዓለም ሁሉ ልትነግሩትና እንዴት ማከናወንም እንደሚቻል ልታሳዩት ትችላላችሁ። ከእናንተ የሚፈለገው በድረ ገጽ ላይ መጻፍ ወይም ቪዲዮውን መቅረጽ ከዚያም ይዘታችሁን ማለትም የሰራችሁትን የምትለጥፉበትን (ፖስት የምታደርጉበትን) የራሳችሁን የዩቲዩብ ቻነል መፍጠር ብቻ ነው። ይህን ካከናወናችሁ በኋላም በፕላትፎርማችሁ ላይ የምርቶች ማስታወቂያዎችን እና ስለምርቶቹ የሚሰጡ አስተያየቶችን በማውጣት ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ። ከ YouTube Creator Academyገጽ ላይ በዩቲዩብ ላይ ወይም የዩቲዩብ ፕላትፎርምን በመጠቀም ገንዘብ እንዴት መስራት እንደሚቻል መማር ትችላላችሁ።
3. የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ መግለጫዎችን የመጻፍ አገልግሎቶች
የትምህርት ደረጃ እና የስራ ልምድ መግለጫዎችን ጥሩ አድርጋችሁ የመጻፍ ክህሎት አላችሁን? ይህ ጥሩ ገንዘብ ሊያስገኝላችሁ የሚችል ክህሎት ነው። ብዙ ሰዎች የኮሌጅ እና የዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እያጠናቀቁ ስራ ለማግኘት የስራ ገበያ ፍለጋውን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። ይህን ለመስራት የመነሻ ካፒታል አያስፈልጋችሁም። ይልቁንም የሚያስፈልጋችሁ አንድ ኮምፒውተር ብቻ ነው። ለአገልግሎታችሁ በቁርጥ ወይም በሰአት የማስከፈል መላን መጠቀም ትችላላችሁ።
4. የዶሜየን ስሞችን መሸጥ
ሰዎች ምርቶቻቸውን እና አገልግሎቶቻቸውን ለመሸጥ ድረ ገጾችን ይጠቀማሉ። በዚህም ምክንያት፣ በርካታ ድረ ገጾች በመፈጠር ላይ ናቸው። ሰዎች ሊፈልጓቸው ይችላሉ ብላችሁ የሚሰሟችሁን እና ለማስታወስም ቀላል የሆኑ የዶሜየን ስሞችን መግዛት ትችላላችሁ። ከዚያም እነዚህን የዶሜየን ስሞች የዶሜየን ገበያ ስፍራዎች ላይ አትርፋችሁ ሽጧቸው። Make sure you have some skills in በፍለጋ ወይም ሰርች ኤንጅን ኦፕቲማይዜሽንእና የቁልፍ ቃላት ፍለጋ ላይ የተወሰኑ ክህሎቶች እንዳላችሁ ግን በቅድሚያ እርግጠኞች መሆን አለባችሁ።
5. የምክር አገልግሎቶች
ሰዎች በእለት ተእለት ህይወታቸው በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ችግሮች የሚያጋጥሟቸው በመሆኑ ለእነዚህ ችግሮቻቸው መፍትሄ ለሚሰጧቸው ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኞች ናቸው። ለምሳሌ፣ ሰዎች በምን አይነት ቢዝነሶች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ እንደሚችሉ ወይም ደግሞ በየትኛው ኩባንያ ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚችሉ ለማወቅ ይፈልጋሉ። በጣም ጥሩ የሆኑ የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶች ካላችሁ እነዚህ ክህሎቶቻችሁ አማካኝነት ሰዎች ተገቢ የሆኑ ውሳኔዎችን እንዲሰጡ ልትረዷቸው ትችላላችሁ። ይህ አይነቱ ቢዝነስ ደግሞ ምንም የመነሻ ካፒታል አያስፈልገውም።
6. የግል አሰልጣኝነት
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አፍቃሪ ናችሁን? ከአካል ብቃትና ከምግብ አወሳሰድ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ችግሮች እያጋጠሟቸው ይገኛሉ። እነዚህ ሰዎች በአብዛኛው በየቤታቸው ጂሞች ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወኛ ስፍራ ያላቸው በመሆኑ እናንተ የጂም ቤት ማቋቋም አያስፈልጋችሁም። እነዚህ የተጠቀሱት ችግሮች ያሉባቸው ሰዎች የሚፈልጉት የአካል ብቃት አሰልጣኝ ብቻ ነው። በአማራጭም ደግሞ፣ ሰዎቹን በየአካባቢያቸው ባሉ ጂሞች ውስጥ ልታሰለጥኗቸው ትችላላችሁ።
እንዲሁም ያንብቡ: የንግድ ሀሳቦች ዝርዝር 2022
7. የግል የምግብ አዘጋጅነት
ብዙ ሰዎች በስራ ላይ ተውጥረው የሚገኙ በመሆኑ ምግብ ለማዘጋጀት ጊዜ የላቸውም። ከዚህ በተጨማሪም፣ በሆቴሎች የሚዘጋጁ ምግቦች ካሎሪ በጣም ይበዛባቸዋል እየተባለ ስለሚነገርም እነዚህ ሰዎች የሆቴል ምግቦችን መመገብ አይፈልጉም። እነዚህ ሰዎች ገንዘብ ያላቸው በመሆኑ እናንተ ጤናማ ምግብ ካዘጋጃችሁላቸው በደንብ አድርገው ለመክፈል ፈቃደኞች ናቸው። እናንተን ታድያ በምግብ አዘገጃጀታችሁ ከሌሎች ላቅ ያላችሁ መሆኑን እርግጠኛ ልትሆኑ ይገባል። የምግብ እቅዶችን ተገቢ ከሆኑት የአመጋገብ መስፈርቶች ጋር ማቅረብ መቻላችሁንም እንዲሁ ልታረጋግጡ ይገባል።
8. የልብስ እጥበት ወይም ጽዳት አገልግሎቶች
የጽዳት ስራ መደበኛ የሆነ ስልጠና የሚያስፈልገው አይነት ሞያ አይደለም። እርግጠኛ መሆን ያለባችሁ በደንብ አድርጋችሁ ማጽዳት መቻላችሁን እና ከሌሎችም ላቅ ያላችሁ መሆኑን መሆኑን ነው። ብዙ ደምበኞችን ለመሳብም፣ አገልግሎቶቹን በቅናሽ ዋጋ እንደምታቀርቡ እንዲሁም በአካባቢያችሁ ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች የማያቀርቧችውን ሌሎች አገልግሎቶች እናንተ ማቅረብ እንደምትችሉ አሳውቁ። ለቤተሰብ አባላት የልብስ እጥበት አገልግሎት ወይም ደግሞ ሰራተኞቻቸውን ዩኒፎርም ለሚያስለብሱ ተቋማት የእጥበት ወይም የጽዳት አገልግሎቶችን መስጠት ትችላላችሁ።
9. የቤት ውስጥ ዲዛይነርንነት
የቢዝነስ እና የቤት ባለቤቶች ለመኖሪያ ቤቶቻቸው እና ለቢሮዎቻቸው ምርጥ የሆኑ ዲዛይኖች እንዲኖራቸው ይሻሉ። አንድ ቢሮ ወይም መኖሪያ ቤት ምን መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለበት ለማወቅ መስፈርቶቹን በቅድሚያ ማወቅ ወይም መረዳት ያስፈልጋል። ከዚህ በማስከተልም፣ ደምበኛችሁ ቢሮው ወይም መኖሪያ ቤቱ እንዴት እንዲሆንለት እንደሚፈልግ እንዲሁም ክፍሉ ለምን አላማ እንደሚውል መገንዘብ ይኖርባችኋል።
10. የጉዞ አስጎብኝነት አገልግሎት መስጠት
ቱሪስቶች ብዙ ስፍራዎችን በሚጎበኙበት ወቅት ስለስፍራዎቹ ሁሉንም መረጃዎች ለማግኘት ይሻሉ። ጉዞዎች ማድረግን፣ የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ወይም የአስተርጓሚነት አገልግሎቶችን ጨምሮ የተለያዩ የጥቅል አገልግሎቶችን ወይም ፓኬጆችን ማዘጋጀት ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ ቱሪስቶች በሚጎበኟቸው ስፍራዎች ውስጥ ካሉ ወይም ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ለመገናኘትና ለማውራት ይፈልጋሉ። በሁለቱ መካከል ባለው የመግባቢያ ቋንቋ ችግር ግን ይህን ማድረግ አስቸጋሪ ይሆናል። በዚህ ጊዜ እናንተ የአስተርጓሚነት አገልግሎት በመስጠት ቱሪስቶቹን መርዳትና ገቢም ማግኘት ትችላላችሁ።
11. የምግብ አዘገጃጀት ዘዴዎች
ሰዎች የሚወዷቸውን ምግቦች አዘጋጅተው እንዲመገቡ ለማገዝ ትችላላችሁ። እናንተ ማድረግ ያለባችሁ ዘርዘር የምግብ አዘገጃጀት ዘዴዎችን ወይም ሬፔሲ ካሰናዳችሁ በኋላ በኦንላይን መለጠፍ ወይም ፖስት ማድረግ ነው። የራሳችሁን ብሎግ መፍጠር ወይም ራሳችሁም ምግቦቹን ስታዘጋጁ የሚያሳይ ቪዲዮ መለጠፍ ትችላላችሁ። አንዴ ምን አይነት ሰዎች ምግቦችን ማዘጋጀት እንደሚወዱ ከለያችሁ በኋላ ለእነዚህ ሰዎች የሚፈልጓቸውን መረጃዎች ልታቀርቡላቸው ትችላላችሁ።
12. የህጻናት ማቆያ ወይም እንክብካቤ አገልግሎቶች
ብዙ ወላጆች ከልጆች ማሳደግና ከስራቸው ጋር ትግል ገጥመው ይገኛሉ። ወደስራቸው ሲሄዱ ልጆቻቸውን የሚያቆዩበት ስፍራን ማግኘት አለባቸው። የህጻናት ማቆያ ወይም እንክብካቤ አገልግሎቶችን በተመለከተ የተለያዩ አገራት የተለያዩ መስፈርቶችን ያስቀምጣሉ። እነዚህን አገልግሎቶች ለመስጠት ስትዘጋጁ መስፈርቶቹን ስለማሟላታችሁ እርግጠኛ መሆን አለባችሁ። ይህ ቢዝነስ ምንም የመነሻ ካፒታል አያስፈልገውም። ከእናንተ የሚጠበቀውና የሚያስፈልገው በህጻናት ዘንድ ተወዳጅ መሆን እና ህጻናትንም እንዴት በጥሩ ሁኔታ መንከባከብ እንዳለባችሁ ማወቅ ነው።
እንዲሁም ያንብቡ: በመስመር ላይ ገንዘብ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል
13. የግቢ መስክ እና አትክልት እንክብካቤ አገልግሎቶች
የሰዎችን የአትክልት ስፍራዎች የመንከባከብ አገልግሎቶችን መስጠት ትችላላችሁ። የግቢ የመስክ ሣር ማጨድ፣ የወዳደቁ ቅጠላ ቅጠሎችን መሰብሰብ፣ አትክልት መትከል እና አበቦችን መከርከም የመሳሰሉ ልዩ ልዩ የአገልግሎት ጥቅሎችን ወይም ፓኬጆችን ማዘጀት ትችላላችሁ። ይህን አገልግሎት ከአመት እስከ አመት መስጠት ስለማይቻል ስራው ወቅት ወቅት ሊኖረው ይችላል።
14. የገበያ እና የማስተዋወቅ ስራ
በርካታ ቢዝነሶች የደንበኞቻቸውን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችሏቸውን መላዎች ወይም መንገዶች ዘወትር ያፈላልጋሉ። ለመቋቋም እየሞከሩ ያሉ አዳዲስ ቢዝነሶችን ፈልጉና ገበያ አፈላላጊ ማግኘት ይሹ እንደሆነ ጠይቋቸው። ይህ ቢዝነስ ምንም የመነሻ ካፒታል አይፈልግም። ከእናንተ የሚፈለገው አሳማኝ መሆን እና ሰዎች ምርቶችን እንዲገዙ የሚያስችሏቸውን መንገዶች መፍጠር መቻል ነው።
15. የሙዚቃ መሳሪያ አጨዋወት ማስተማር
የሙዚቃ መሳሪያዎችን የመጫወት ክህሎት ካላችሁ፣ ለመማር ፈቃዱና ፍላጎቱ ያላቸውን ሰዎች በሙዚቃ መሳሪያ አጨዋወት ማሰልጠን ትችላላችሁ። እጅግ ብዙ ሰዎች ፒያኖን፣ ጊታርን ወይም ኪቦርድን እንዴት መጫወት እንደሚችሉ አያውቁም። ለእያንዳንዱ የሙዚቃ መሳሪያ የተለያዩ ጥቅሎችን ወይም ፓኬጆችን ካሰናዳችሁ በኋላ የማሰልጠኛ ስፍራና ጊዜ አመቻችታችሁ ስልጠናውን መስጠት ትችላላችሁ።
16. የኩነቶች ወይም ኢቨንት አዘጋጅነት
ሰዎች የሰርግ ስነ ስርአቶችን፣ የልደት ፓርቲዎችን፣ የትምህርት ምርቃት ስነ ስርአቶችን፣ የቀብር ስነ ስርአቶችን እና ሌሎች የተለዩ በርካታ ኩነቶችን ወይም ኢቨንቶችን ማከናወን ይሻሉ። አንዳንዶች እነዚህን ኢቨንቶች በተመለከተ እቅድ ለመንደፍ ወይም አስፈላጊ የሆኑ ሀብቶችን ለመሰብሰብ ጊዜ አይኖራቸውም። በመሆኑም፣ ሰዎችን ኢቨንቶችን እንዲያዘጋጁ በማገዝ ገቢ ማግኘት ትችላላችሁ። ሰዎቹ ራሳቸው ገንዘቡን ስለሚያቀርቡና እናንተም አገልግሎቱን ለሶስተኛ ወገን ባለሞያዎች ማስተላለፍ የምትችሉ በመሆኑ አገልግሎቱን ለመስጠት ምንም መነሻ ካፒታል አያስፈልገውም።