ኢትዮጵያ ውስጥ ዩኒቨርሲቲ እያሉ እንዴት ገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል

ትርጉሞች:

የኮሌጅ ትምህርት ዘመን የአንድ ሰው ህይወት አስደሳች ጊዜ ሊሆን ይችላል። ለእኔ በግሌ ኮሌጅ የህይወቴ ምርጡ ህይወት ነበር። ነፃነቱ፣ ነፃ ጊዜው እና እዚያ የምታገኟቸው ሰዎች ህይወታችሁን በመቅረጽ ረገድ ሊያግዟችሁ ይችላሉ። ኮሌጅ በተለይ እንደ የሂሳብ ቀመርና ስታስቲካዊ ሳይንስ፣ ፋይናንሺያል ኢንጂነሪንግ እና ህክምና ትምህርት ያሉ አስቸጋሪ ኮርሶችን ስትወስዱ እጅጉን ስራ የሚበዛበት ቦታም ነው። ይህም ሆኖም ግን፣ ኮሌጅ ህይወወታችሁን ሊቀርጽ ይችላል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥአንድም የትምህርት ክፍለ ጊዜ ሳያመልጣችሁ ኮሌጅ ውስጥ እየተማራችሁ ገንዘብ ለማግኘት የሚያስችሏችሁን 8 ምርጥ መንገዶችን እንመለከታለን። ከእነዚህ ዘዴዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በየወሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ወይም ዶላሮችን ሊያስገኙላችሁ ይችላሉ።

ማስተማር

በካምፓስ ውስጥ ትምህርት ላይ ሆናችሁም በአንድ የተወሰነ መስክ ባለክህሎት የመሆን እድል አላችሁ። እንደ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ፣ በኮድ አመሰጣጠር ወይም ኮዲንግ እና ሂሳብ ባሉ መስኮች የተካናችሁ ወይም ባለክህሎት ልትሆኑ ትችሉ ይሆናል። የእነዚህ ክህሎቶች ባለቤት ከሆናችሁ ክህሎቶቻችሁን ማባከን የለባችሁም ምክንያቱም ሌሎች ይፈልጓቸዋልና። እንደውም፣ እነዚህን ክህሎቶቻችሁን በኦንላይን ሌሎችን ማስተማር ትችላላችሁ። ይህንን ለማድረግ የምትችሉባቸው ብዙ መንገዶች አሉ። አንደኛ፣ የራሳችሁን በኦንላይን ማስተማሪያ ድረ ገጽ መፍጠርና ደንበኞችን ማግኘት ትችላላችሁ። ይህን ሞዴል ወይም ዘዴ በመጠቀም የሚያገኙትን ትርፍ ሁሉ ያለማንም ተጋሪ ለራሳችሁ ትወስዳላችሁ። ሁለተኛ፣ ዛሬ ያሉትን የተለያዩ የኦንላይን የስልጠና መድረኮችን ወይም ፕላትፎርሞችን በመጠቀም የማስተማር ስራችሁን ለመጀመር ትችላላችሁ። ለምሳሌ፣ የምትሰጡትን ኮርሶች በኡዴሚ (Udemy) ላይ በመለጠፍ ወይም ፖስት በማድረግ ተማሪዎችን መሳብ ትችላላችሁ። እንደ ኡዴሚ (Udemy) ያለ ፕላትፎርምን መገልገል ያለው ጥቅም በዓለም ዙሪያ ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉት መሆኑ ነው። እዚህ ላይ ያለው ዋናው ፈተና ወይም ተግዳሮት ገንዘቡን ከኩባንያው ጋር መጋራት የሚኖርባችሁ መሆኑ ነው።

የጥበብ ስራ / አርት

አርቲስት ከሆናችሁ ወይም የጥበብ ስራ ከህሎት ካላችሁ፣ ጥሩ የሆነው የገንዘብ ማግኛ መንገድ የጥበብ ስራዎችን መፍጠር ወይም መስራትና መሸጥ ነው። እንደ መልካም አጋጣሚ ወይም ዕድል እነዚህን የጥበብ ውጤቶች ለመሸጥ የግድ መደብር እንዲኖራችሁ አያስፈልግም። ብዙ ተጠቃሚዎች በኦንላይን ላይ ያሉ በመሆኑ ስልቱን ተጠቅመው ገንዘብ ለማግኘት ምርጡ መንገድ በኦንላይን መሸጥ ነው። የራስችሁን የኪነ ጥበብ እና የዕደ ጥበብ ድረ ገጽ መፍጠር፣ ለገበያ ማቅረብ እና ምርቶቹን ለደንበኞች መሸጥ ትችላላችሁ። የተሻለው አማራጭ ደግሞ የራሳችሁን ድረ ገጽ ከማህበራዊ ሚዲያ እና እንደ ኢቲሲ (Etsy) እና አማዞን ካሉ ኢ-ኮሜርስ መደብሮች ጋር ማጣመር ወይም ማስተሳሰር ነው።

ትምህርት ነክ ወይም አካዳሚያዊ እና በፍሪላንስ ጽሁፎችን መጻፍ

በካምፓስ ውስጥ እየተማራችሁ ገንዘብ ለማግኘት ሌላው መንገድ ይዘትን ወይም ጽሁፎችን መጻፍ ነው። ለዚህ ደግሞ በርካታ አቀራረቦች አሉ። በመጀመሪያ፣ ሌሎች ተማሪዎች በተሰጧቸው ስራዎች ላይ ልትረዷቸው በሚያስችሏችሁ አካዳሚያዊ ጽሁፎች ላይ ማተኮር ትችላላችሁ። ይህንን ለማድረግ፣ የራሳችሁን የአካዳሚያዊ ጽሑፍ ድረ ገጽ መፍጠር ነው። በአማራጭ፣ ይህንን ስራ ለማግኘት የተለያዩ የአካዳሚያዊ የቤት ስራዎች የገበያ ቦታዎችን (marketplaces) መጠቀም ትችላላችሁ። ጥሩ ጸሃፊ ከሆናችሁም፣ በኦንላይን የጽሁፍ ስራዎች ፈላጊዎችን ማፈላለግና ማግኘት ትችላላችሁ። በአሁኑ ጊዜ፣ ብዙ ኩባንያዎች ለስራዎቻቸው ኦንላይንን ወደመጠቀም ስለዞሩ ለይዘት ወይም ለጽሁፍ ያለው ፍላጎት በጣም በፍጥነት እያደገ ነው። እንደ ፋይቨ (Fiverr) እና Upwork ያሉትን የወቅቱ የገበያ ስፍራዎች በመጠቀም ደንበኞችን ማግኘት ትችላላችሁ።

የግራፊክ እና የድረ ገጽ ዲዛይን እና የመረጃ መፈላለጊያዎችን ማሳለጥ (SEO)

ገንዘብ ለማግኘት እና ክህሎቶቻችሁን ለማሻሻል ካሻችሁ አሁን ላይ እነዚህ ሶስቱ በጣም ታዋቂ ዘዴዎች ናቸው። የግራፊክ ዲዛይን እንደ Photoshop፣ Illustrator እና Indesign ያሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም በራሪ ወረቀቶችን፣ አርማዎችን እና ብሮሹሮች ያሉ ጠቃሚ ምርቶችን የመፍጠሪያ ወይም የማዘጋጃ ሂደት ነው። ብዙ ኩባንያዎች ስራ ሲጀምሩ የእነዚህ ግራፊክ ንድፎች ፍላጎት ሁልጊዜ እየጨመረ ይሄዳል።

የኢንተርኔት ወይም የበይነ መረብ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር የድረ-ገጾች ባለሙያችን በተመለከተ ያለው ፍላጎት እያደገ በመሄድ ላይ ነው። ስለዚህ፣ ድረ ገጾችን የሚቀርጽ ወይም ዲዛይን የሚያደርግ እና ለፍለጋ ፕሮግራሞች ወይም ሰርች ኤንጂኖች የሚያመቻች ኩባንያ ማቋቋም ወይም መመስረት ትችላላችሁ። የዲጂታል ሽያጭ አስፈላጊነት እየጨመረ በመምጣቱም አንዳንድ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ድረ-ገጾቻቸውን ለመንደፍ እና ለማሻሻል ወይም ኦፕቲማይዝ ለማድረግ በየወሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ብሮችን ወይም ዶላሮችን በመክፈል ላይ ናቸው።

ድሮፕ ሺፒንግ (Drop Shipping)

ድሮፕ ሺፒንግ አንድን ድረ-ገጽ የሚፈጥሩበት፣ ከምርት አቅራቢ ወገን ጋር የሚነጋገሩበት፣ ምርቶቹንም በዝርዝር የሚይዙበትና ለገበያ የሚያቀርቡበት ሂደት ማለት ነው። አንድ ተጠቃሚ ምርቱን ከገዛ በኋላ፣ እናንተ ሻጩ ምርቶቹን ወደተጠቃሚው እንዲልክ ትነግሩታላችሁ። ይህንን በተለያዩ መንገዶች መፈጸም ትችላላችሁ። በቅድሚያ፣ በርካታ ተስማሚ የሆኑ ድረ ገጾችን መፍጠር ትችላላችሁ። ቀጥሎም፣ እነዚህን ሁሉ ነገሮች የሚሸጡበት አንድ ድረ ገጽ መፍጠር ትችላላችሁ። የድሮፕ ሺፒንግ ጥቅሙ Shopify ተብሎ የሚጠራውን የንግድ ፕላትፎርም በመጠቀም በቀላሉ ድረ ገጽን ለመፍጠር ማስቻሉ ነው። ሌላው ጥቅም ደግሞ ብዙ ሀብቶች ላይ ኢንቬስት ማድረግ አያስፈልጋችሁም። የሚያስፈልጓችሁ ድረ ገጽ፣ ጥሩ ጥሩ ምስሎች እና ጥሩ አቅራቢ ብቻ ነው።

የአካባቢ ስራዎች

በኮሌጅ ውስጥ እየተማራችሁ ገንዘብ ለማግኘት ሌላው መንገድ አካባቢያዊ ተግባራትን ማከናወን ነው። በአሜሪካ ውስጥ፣ እናንተ ልታከናውኗቸው የምትችሏቸው አካባቢያዊ ስራዎች ብዛት እየጨመረ ነው። ለምሳሌ፣ እንደ ሮቨር ያለ ፕላትፎርምን በመጠቀም የሰዎችን ውሻዎች ይዞ በመጓዝ ወይም በማንሸራሸር በየቀኑ ከ30 ዶላር በላይ ማግኘት ትችላላችሁ። ለኡበር (Uber) እና ሊፍት (Lyft) የትራንስፖርት አገልግሎትም የራሳችሁን መኪና በመጠቀም ገንዘብ መስራት ትችላላችሁ። እንደ ቤት ጽዳት፣ የቤት እቃዎች መገጣጠም እና ማሸግ የመሳሰሉ ስራዎችን ለመስራትም እንደ Task Rabbit ያለ ድረ ገጽን መጠቀም ትችላላችሁ። እንደ Amazon Flex የአቅርቦት አገልግሎት ፕላትፎርሞችን በመጠቀምም ጥቅሎችን ወይም እሽጎችን ለሰዎች የማድረስ አገልግሎት መስጠት ትችላላችሁ።

ቪዲዮዎችን መጫን እና ጨዋታዎች

በዚህ የዩቲዩብ እና Twitch ዘመን፣ ብዙ የኮሌጅ ተማሪዎች የሚወዱትን በማከናወን ገንዘብ እያገኙ ነው። አንዳንድ በጣም የታወቁ የዩቲዩብ እና የ Twitch ሱፐር ኮከቦች የኮሌጅ ተማሪዎች ናቸው። ጎግል ቪዲዮዎቻቸውን ባዩላቸው ሰዎች ቁጥር ብዛት ላይ በመመስረት ለዩቲዩበሮች ገንዘብ ይከፍላል። ዩቲዩበሮች ከትላልቅ ኩባንያዎች ድጋፍ ሲያገኙም ቪዲዮዎችን በስፖንሰርሺፕ ይሰራሉ። በ Twitch የመዝናኛ ፕላትፎርም ላይ የሚጫወቱት ደግሞ በስፖንሰሮች እና የጨዋታ ቪዲዮውን በተመለከቱት ሰዎች ገንዘብ ይከፈላቸዋል።

እለታዊ ንግድ (Day Trading)

Day Trader

በካምፓስ ውስጥ እየተማራችሁ ገንዘብ ለማግኘት ሌላኛው መንገድ Another way to make money in campus is to በአንድ የንግድ ቀን አክሲዮኖች እና ገንዘቦችን መነገድ ነው። ይህ ስራ የድለላ ሂሳብ ወይም አካውንት የምትከፍቱበት፣ ገንዘብ የምታስቀምጡበት እና ንግድ የምትጀምሩበት ሂደት ነው። ይህንን ለማድረግ ገበያው እንዴት እንደሚሰራ እና የንግድ ልውውጦቹን እንዴት ያሉ አዋጭ የንግድ ስፍራዎች ማኖር እንዳለባችሁ መማር ያስፈልጋችኋዋል። በዚህ መንገድ ብዙ የኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ተፈጥረዋል። ለምሳሌ፣ ቢሊየነሩ ኬን ግሪፊን የሄጅ ፈንድ (hedge fund) ንግዱን የጀመረው ገና ተማሪ ሳለ ነው።

ማጠቃለያ

ኮሌጅ ህይወታችሁን የምትቀርጹበት ስፍራ ነው። በካምፓስ ውስጥ፣ አብዛኛውን ጊዜያችሁን በትምህርት ክፍል ውስጥ አስተማሪዎቻችሁን በማዳመጥ ማሳለፍ ይኖርባችኋዋል። በትርፍ ጊዜያችሁ፣ ለህይወታችሁ ዋጋ ወይም እሴት የሚጨምሩ ነገሮችን ማከናወን አለባችሁ። እዚህ የጠቀስናቸው አንዳንድ ጠቃሚ ጥቆማዎች ገንዘብ ለማግኘት እና ወደ ሥራ ገበያውም በምትወጡበት ጊዜ ጠቃሚ ልምድ እንድታገኙ ይረዱዋችኋዋል።