በ Shopify ላይ ገንዘብ እንዴት መስራት እንደሚችሉ የሚያመለክቱ 4 ደረጃዎች

ትርጉሞች:
en_USes_ESsw

የኦንላይን የዕቃ መሸጫ መደብር ለመጀመር እያሰባችሁ ቢሆንም ይኼን ግን እንዴት ማድረግ እንደምትችሉ አታውቁም አይደል? በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ከ3 ቢሊዮን በላይ የኢንተርኔት ወይም በአማርኛው የበይነ መረብ ተጠቃሚዎች አሉ። ይህ ደግሞ በእነዚህ ተጠቃሚዎች ላይ በማነጣጠር ገንዘብ ለመስራት የሚያስችል ይህን የመሰለ እድል በጭራሽ ኖሮ አያውቅም ማለት ነው። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ዛሬ በገበያ ውስጥ ያሉቱ በርካታ የይዘት አስተዳደር ስርዓቶች (ሲኤምኤስ) በኦንላይንየዕቃ መሸጫ መደብር የመጀመር ሂደትን ቀላል አድርጎታል።

ይህንን ጽሑፍ በእንግሊዝኛ ያንብቡ: How to Make Money Online in Ethiopia with Shopify

ከእነዚህ ፕላትፎርሞች መካከል WooCommerce፣ Wix፣ Weebly እና Squarespace ተጠቃሽ ናቸው። ሆኖም የኢኮሜርስ መደብርን ከፍቶ የንግድ ስራን ለማከናወን የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ የሚያካትትውና የተሻለው ፕላትፎርም Shopify (ሾፒፋይ) ነው። ይህ እ.ኤ.አ. በ 2006 ዓ.ም. ስራ የጀመረው ኩባንያ ዛሬ ላይ የ 31 ቢሊዮን ዶላር ግምት ያለው ለመሆን የበቃ ነው። ይህ ጽሑፍ በ Shopify ፕላትፎርም ላይ እንዴት ገንዘብ መስራት እንደምትችሉ ቀለል ያሉ ደረጃዎችን ያብራራላችኋል።

ለመሆኑ Shopify ምንድን ነው?

ኢኮሜርስ ኢትዮጵያ

ቀደም ባለው ጊዜ እንደ አማዞን ያሉ የኢ-ኮሜርስ መደብሮችን መጀመር ትንሽ አስቸጋሪ ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስከፍሉ ልምድ ያላቸው የድረ ገጽ ዲዛይነሮች ያስፈልጉዋችሁ ነበር። የ Shopify መስራቾች ግን በእነዚህ ተግዳሮቶች ውስጥ ዕድሎችን አሻግረው ለመመልከት በመቻላቸው ማንኛውም ሰው የራሱን የኦንላይን የንግድ መደብር ሊፈጥርበት የሚችለውን ፕላትፎርም ለመስራት ችለዋል። ዛሬ ላይ ታድያ፣ ይህ ፕላትፎርም የኦንላይን የንግድ መደብራችሁን በደቂቃዎች ውስጥ መጀመር ወደሚያስችላችሁና ሙሉ በሙሉ እንደየሰው ፍላጎት ልታበጁት ወይም ካስተማይዝ ልታደርጉት የምትችሉት ሶፍትዌር ለመሆን
በቅቷል። ፕላትፎርሙ እንደ የክፍያ ማሳለጫ ወይም ፕሮሰሲንግ፣ የፎርም ዲዛይን፣ እና ገበያ ማካሄጃ ያሉና የኦንላይን የንግድ መደብራችሁን ልታሻሽሉባቸው የሚያስችሏችሁን መሳሪያዎች መግዛት የምትችሉበት የገበያ ስፍራም አለው።

በመስመር ላይ የቢዝነስ ሀሳቦች በኢትዮጵያ

እንደ ማስጠንቀቂያ አለያም እንደማሰታወሻ እንዲሆናችሁ፣ አብዛኞቹ የ Shopify ኦንላይን የንግድ መደብሮች አለመሳካታቸውን ማወቅ አለባችሁ። አብዛኛዎቹ ስራቸውን የጀመሩበትን አንድኛ አመት እንኳን ሳያከብሩ ይወድቃሉ። ስኬታማ እንዳይሆኑ ካደረጓቸው ምክንያቶች አንዱ ከኋላቸው ያለው ሃሳብ ሁልጊዜ ጥሩ አለመሆኑ ነው። ስለዚህ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በመስመር ላይ የቢዝነስ ሃሳብ ለማግኘት ጥልቅ ምርምር ማድረግ አለብህ። ይህን በምታደርጉበት ጊዜም ለሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ መስጠትን ኢላማ ማድረግ አለባችሁ፡

  1. ይዤ የተንሳሁት ሃሳብ በአይነቱ ለየት ያለ ነውን?
  2. ከደንበኞች የሚሰጡኝን ትእዛዞች ማሟላት እችላለሁን?
  3. ይህን ምርት ሰዎች በእርግጥ ይፈልጉታልን?
  4. ኢላማ የተደረገው ገበያ ምንድን ነው?
  5. ገበያው ላይ ያሉት ተፎካካሪዎች እነማን ናቸው?

አንድ ሃሳብ ላይ ከማረፋችሁ በፊት፣ ሰዎች ስለ ሃሳቡ ምን እንደሚሰማቸው እንድትጠይቁ ይመከራል። ይህ ምርቱ አስፈላጊ ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ ሃሳብ ይሰጣችኋል።

በኢትዮጲያ ውስጥ Shopify በመጠቀም ገንዘብ ለማግኘት በመዘጋጀት ላይ

ለመጀመር በምትሹት ንግድ ላይ ከወሰናችሁ በኋላ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋችኋል። በመጀመሪያም ማድረግ ያለባችሁ ለንግድ ስራችሁ የሚሆን አርማ ማዘጋጀት ነው። በዚህ ላይ ስራ ፈጣሪዎችን ለማገዝ Shopify በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ አርማ ለማዘጋጀት የሚረዳ Hatchful የሚባል ከክፍያ ነፃ የሆነ አርማ ዲዛይን ማድረጊያ መሳሪያ አለው። አርማው የድርጅታችሁ ስም ሊኖረው ይገባል። የሚከተሉት ባሕርያት ቢኖሩት ደግሞ ይበልጥ ጥሩ ይሆናል:

  1. እጥር ምጥን ያለ መሆን አለበት።
  2. ማራኪ ወይም ሳቢ መሆን አለበት።
  3. የማይረሳ ሊሆን ይገባል።
  4. ከምትሸጡት ምርቶች ጋር የተያያዘ ትርጉም ሊኖረው ይገባል።

በመቀጠልም፣ ለንግድ የምትይዟቸውን እቃዎች በደንብ ማወቅና መንከባከብ አለባችሁ። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ኩባንያ ምርቶቻችሁን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርቡ የውጭ አቅራቢዎችን እንድታገኙ ይመከራል። ይህንን ለማድረግ፣ እንደ Alibabaባሉ ፕላትፎርሞች አማካኝነት ከቻይናዊያን ወይም ከቬትናምዊያን ወይም ከሌሎች አምራቾች ጋር ድርድር ማድረግ ትችላላችሁ።

የኦንላይን ንግድ መደብራችሁን ማደራጀት ወይም መገንባት

የንግድ መደብራችሁን ስም እና የንግድ ዕቃዎችን ዝርዝር ካዘጋጃችሁ በኋላ፣ የኢ-ኮሜርስ መደብራችሁን መገንባት መጀመር አለባችሁ። የመጀመሪያው እርምጃ መመዝገብ እና የምትፈልጉትን ጥቅል ወይም ፓኬጅ መምረጥ ነው። ለአንድ ወር የመሰረታዊ ጥቅል ዋጋ $29 ነው። የአንድ ወር የሾፒፋይ (Shopify) ጥቅል እና የሾፒፋይ (Shopify) ፕላስ ዋጋ (Plus) $79 እና $299 ነው። እንደ ጀማሪ፣ የምትፈልጉትን ሁሉንም ገጽታዎች የያዘ በመሆኑ ከመሰረታዊ ጥቅል ወይም ፓኬጅ ብትጀምሩ የሚመከር ይሆናል።

Make Money With Shopify
የምትልጉትን ጥቅል ከመረጣችሁ በኋላ፣ አሁን ከብዙ ነፃ ገጽታዎች (themes) ውስጥ አንዱን ምረጡና ምርታችሁን ማከል ወይም ማስገባት ጀምሩ። ይህን በምታደርጉበት ጊዜም የሚከተሉትን ማከናወናችሁን ማረጋገጥ አለባችሁ:

  1. የምርቶቻችሁን ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ፎቶግራፎችን ማስገባታችሁን።
  2. ስለምርቶቻችሁ ጥሩ የሆኑ ማብራሪያዎችን መስጠታችሁን።
  3. ስለቁልፍ ቃላቶች በደንብ ጥናት ማድረጋችሁን።
  4. የምታስገብዋቸው ምስሎች ሁሉ ስማቸውን ማስገባትና ስለእነሱ በደንብ የሚገልጽ ማብራሪያ መስጠታችሁን ማረጋገጥ።

በመጨረሻም፣ ተገቢ የሆኑ ደንቦች እና ሁኔታዎችን፣ ፖሊሲዎችን እና ዕቃዎችን የመመለሻ መመሪያዎችን እንዳሰፈራችሁ ማረጋገጥ አለባችሁ። በኦንላይን ቀጥታ ስርጭት ላይ መግባት የሚኖርባችሁ ዕቃዎቹን ዝግጁ ስታደርጉ ብቻ መሆኑን ማስታወስ አለባችሁ።

ምርቶችን በእጃችሁ ከመያዝ በተጨማሪ፣ የድሮፕ ሺፒንግ የንግድ ስልትን መጠቀምም ትችላላችሁ (Shopify dropshipping)። ይህ እናንተ ምርቶችን በእጃችሁ ሳታስገቡ ወይም የምርቶቹ ባለቤት ሳትሆኑ ነገር ግን ሰዎችን ወደ ሌሎች ኩባንያዎች የሚያመለክቱበት የሚጠቁሙበት ስልት ነው። ይህ በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች እየተጠቀሙበት ያለ የንብረት አስተላላፊነት ስልት ነው። በተጨማሪም፣ እንደ Printful ያሉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ያለምንም ሎጂስቲክስ የራሳችሁን ቲ-ሸርት እና ሌሎች ሊታተሙ የሚችሉ ንድፎችን መገንባት ትችላላችሁ።

ምርቶቻችሁን ለገበያ ማቅረብ

የኦንላይን የንግድ መደብራችሁን ከገነባችሁ ወይም ካደራጃችሁ በኋላ፣ አሁን እነሱን ለገበያ ማቅረብ ይኖርባችኋል። ይህንን ለማድረግ ምርጡ መንገድ ንግዳችሁን ከመጀመራችሁ በፊት በሰዎች ዘንድ መነጋገሪያ እንዲሆን የህዝብ ግንኙነት ዘመቻን ማካሄድ ነው። የመደብራችሁን ድረ ገጽ ለማስተዋወቅም በተሰማራችሁበት የንግድ ዘርፍ ውስጥ ያሉ ታዋቂነት እና ተቀባይነት ያላቸውን ድረ ገጾች መጠቀም ትችላላችሁ። ከዚህ በኋላም፣ ለሸቀጣችሁ ወይም ምርቶቻችሁ ድጋፍን እና ማበረታቻዎችን ለማስገኘት እንደ ኢንስታግራም፣ ፌስቡክ እና ትዊተር ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮችን መጠቀም ትችላላችሁ። ይህ በጣም ውድ የንግድ ልምምድ ቢሆንም፣ ገንዘብ ማግኘት ሲትጀምሩ ግን ይገባዋል ትላላችሁ። የሚከተሉትን ስልቶች ወይም አሰራሮች ተከተሉ፡

  1. የኦንላይን መደብራችሁ ለኢንተርኔት ማፈላለጊያ ኤንጂኖች በደንብ የተስማማ መሆኑን ማረጋገጥ።
  2. የ ‘ይግዙ’ ቁልፍን በኢንስታግራም ላይም እንዲኖር ወይም እንዲካተት ማድረግ።
  3. ገንዘብ ወጪ በማድረግ ገንዘብ የሚያስከፍሉ ማህበራዊ መገናኛዎችን እና የመረጃ ማፈላለጊያዎችን መጠቀም።
  4. በኦንላይን የግንኙነት መድረኮች ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑት ጋር አጋር መሆን።
  5. ሰዎች እየተቀባበሉ ሊመለከቷቸው የሚችሉ ቪዲዮዎችን መፍጠር።

የመስመር ላይ የኢትዮጵያ መደብር (Shopify Stores in Ethiopia)

በኢትዮጵያ ውስጥ የሾፕፋይን የመስመር ላይ መደብሮችን መመልከት ጥሩ ሀሳብ ነው። የሚከተሉትን ያካትታሉ.

ማጠቃለያ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ በመስመር ላይ ገንዘብ ማግኘት

Shopify (ሾፒፋይ) ብዙ ኩባንያዎች የሚጠቀሙበት በጣም ጥሩ መድረክ ወይም ፕላትፎርም ነው። ይህ ፕላትፎርም በጣም ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ አማዞን የራሱን መደብር ለመዝጋት ሲወስን እንኳ ደንበኞቹ ይህን ፕላትፎርም እንዲጠቀሙ ጠቁሟቸዋል። እነዚህ ከዚህ በላይ ያሰፈርናቸው ምክሮችና ጥቆማዎች በ Shopify ፕላትፎርም ገንዘብ እንዴት መስራት እንደምትችሉ እና ስኬታማ የስራ ፈጣሪም እንድትሆኑ ይረዷችኋዋል። ነገር ግን፣ አስቀድመን እንደገለጽነው፣ የኦንላይን የንግድ መደብሩን የማስጀመር ሂደቱ ቀላል ቢሆንም፣ በቀላሉ ግን ስኬታማ አይኮንም። ብዙ እንቅልፍ አልባ ምሽቶችን ማሳለፍ እንዲሁም ገንዘብ ማውጣት ይኖርባችኋል።