የበጀት እቅዶች: ከፋይናንሳዊ ስጋት ወደ ፋይናንሳዊ እፎይታ

ትርጉሞች:
en_USsw

የበጀት እቅድ ማዘጋጀት ገቢን እና ወጪዎችን ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው። ይህ ለሁሉም ሰው እውነት ነው። የበጀት እቅድ ማሰናዳት ገንዘብን ለመቆጠብ እና የፋይናንስ ህይወታችሁን በራሳችሁ ቁጥጥር ስር ለማዋል የመጀመሪያው እርምጃ ነው። የበጀት እቅድ ማዘጋጀት ውስብስብ መሆን የለበትም። ቀላል የበጀት እቅድ በፋይናንስ ነክ ጠባያችሁ ላይ ትልቅና አዎንታዊ ተጽእኖ ይኖረዋል።

ህይወታችንን የምንገፋው ከወር እስከ ወር ደሞዛችንን እንዴት ማብቃቃት እንደምንችልና ወጪዎቻችንን ለመሸፈን የሚያስችለን በቂ ገንዘብ አለን ወይስ የለንም በሚል ስጋት ውስጥ ተውጠን ነው። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ይህ በሁላችንም ዘንድ ያለና መጋፈጥ ያለብን እውነታ ነው። ነገር ግን እንደ የቀደመው ዘመን አባባል “ፈቃደኝነቱ ካለ፣ መንገድ ወይም መፍትሄ አለ” አሁንም ይሰራል። ይህን መጣጥፍ ማንበብ ስትጀምሩ የበጀት እቅድ አውጥታችሁ ህይወታችሁን መምራት እንደሚገባችሁ መረዳት ጀምራችኋል ማለት ነው። አሁን እንዴት የቁጠባ እቅድ ማውጣት እንደምትችሉና እቅዳችሁም ላይ እንዴት እንደምትፀኑ ይህ መጣጥፍ አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን ሊያሳውቃችሁ ይሞክራል።

ማስረጃዎችን ማሰባሰብ

ገንዘባችንን ከመጠን በላይ የምናወጣው ብዙውን ጊዜ ገንዘባችንን በትክክል ምን ላይ ማውጣት እንዳለብን መረዳት ሲሳነን ነው። ይህንን አግባብ ያለሆነ ነገር የምንገነዘበው ግን ገቢያችን ተሟጦ ሲያልቅ እና የሚቀጥለው ክፍያም ገና ርቆ ባለበት ጊዜ ብቻ ነው። ምን ያህል ገንዘብ እንደምናወጣና በምን በምን ነገሮች ላይ ማውጣት እንደሚያስፈልገን መወሰን የግድ ይለናል። ገንዘብን የት መቆጠብ እንደሚቻል ለማወቅ የመጀመሪያው እርምጃ ገንዘቡ የት እንደሚሄድ ወይም በምን ላይ እንደሚወጣ ማወቅ ነው።

ወጪዎችን ምን ምን ላይ እንደዋሉ ለመከታተል በጣም በብዙዎች ዘንድ ተመራጩና ተቀባነት ያገኘው ዘዴ እነሱን በጽሁፍ ማስፈር ነው። ይህንን በስፕሬድሺት፣ በማስታወሻ ደብተር ውስጥ ወይም የበጀት አወጣጥ መተግበሪያን ወይም አፕልኬሽንን በመጠቀም ማከናወን ትችላላችሁ። ምርጫው የእናንተ ነው። የበጀት እቅድዎን ከማውጣትዎ ቢያንስ ከአንድ ወር በፊት ይህንኑ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ጥናት መጀመር

የወር ወጪዎቻችሁን አንዴ ካወቃችሁ በኋላ፣ በጣም የሚያስፈልጓችሁን እና በዝቅተኛ ደረጃ የምትፈልጓቸውን ወጪዎች ዝርዝር በጽሁፍ ማስፈር አለባችሁ። የትኛው እቃ የትኛው ዝርዝር ውስጥ እንደሚካተት ለመወሰን፣ አስቀድማችሁ የተለያዩ የወጪ አይነቶችን ተመልከቱ።

  • ቋሚ ወጪዎች —እነዚህ በየወሩ የማይለዋወጡ ወጪዎች ናቸው፤ ለምሳሌ፣ የቤት ኪራይ፣ የመድን ዋስትና፣ የባንክ እዳ፣ የብድር ክፍያ ወጪዎች።
  • ተለዋዋጭ ወይም ተቀያያሪ ወጪዎች —እነዚህ በየወሩ ሊለዋወጡ የሚችሉ ወጪዎች ናቸው፤ ለምሳሌ፣ የግሮሰሪ፣ የግል ንጽህና እቃዎች፣ የነዳጅ፣ የአልባሳት፣ ለስጦታ ግዢ የሚወጡ ወጪዎች።
  • ድንገተኛ ወጪዎች —እነዚህ ያልታሰቡ ሁኔታዎች በድንገት በሚከሰቱበት ወቅት የሚኖሩ ወጪዎች ናቸው፤ ለምሳሌ፣ ለጤና ምርመራ ወይም ህክምና፣ የተበላሸ ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ላፕቶፕ ጥገና፣ የሚወጡ ወጪዎች። ከዚህ አኳያ፣ ተመራጭ የሚሆነው እነዚህ ወጪዎች ከድንገተኛ ጉዳዮች ቁጠባ አካውንት ወጪ ተደርገው ቢሸፈኑ ወይም ቢከፈሉ ነው።
  • ተጨማሪ ወይም ልዩ ወጪዎች —እነዚህ በጣም አስፈላጊ ያልሆኑ ወጪዎችን ሁሉ ያመለክታሉ፤ ለምሳሌ፣ ወደ ሆቴሎች ሄዶ ለመመገብ፣ ለፊልም ወይም ሲኒማ፣ በመንገድ ዳር ካሉ ቡና መሸጫዎች ለቡና መጠጣት የሚወጡ ወጪዎች ናቸው።

በመዘርዝራችሁ ውስጥ፣ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆኑት ወጪዎች፣ ለምሳሌ፣ የቤት ኪራይ እና የዕዳ ክፍያ ወጪዎች ከላይ መስፈር አለባቸው።

ከውስጣዊ መጨናነቅ መዳን

በመዘርዝራችሁ ውስጥ ያሉትን ነገሮች የመተው ጉዳይ ከባድ ወይም አስቸጋሪ ይሆን ይሆናል። ጧት ላይ አንዲት ስኒን ቡና በውድ ዋጋ ገዝቶ መጠጣት አስፈላጊያችሁ ላይሆን ይችላል፣ ግን ደግሞ ቡናዋ ቀናችሁን ፈካ ብላችሁ እንድትውሉ ልታደርጋችሁ ትችላለች።

ምን ያህል ወጪያችሁን ማቆም እንደምትችሉ ለመወሰን ለወጪዎቻችሁ ተርታ ስጡ። ይህን ዋና ዋና ወጭዎቻችሁን ከዕለታዊ ወጪዎቻችሁ በመለየት ጀምሩ። ይህን ማድረጉ የበጀት እቅዳችሁን እንድታደራጁ እና ተገቢውን የወጪ መጠናችሁን በመቶኛ ለማስቀመጥ ይረዳችኋል።

ለአብነትም፣ ቀላል ቻርት በመስራት ጀምሩ። ያወጣችኋቸውን ወጪዎች ከደማመራችሁ በኋላ በምድብ በምድብ አስቀምጧቸው። ይህን በአንድ ልሙጥ ወረቀት ላይ ወይም ስፕሬድሺት ላይ ወይም ደግሞ ሞባይላችሁ ባሉ የበጀት መተግበሪያዎች ወይም አፕልኬሽኖች ላይ መስራት ትችላላችሁ። ከታች ባለው ቦታም ላይ ለእያንዳንዱ መስመር ወይም ክፍል ቁጥሮቹን ወይም የወጪ አሃዞቹን ድምር አስቀምጡ፣ ከዛም ይህን ድምር ከገቢያችሁ አኳያ ታነጻጽራላችሁ። እንደ href=”https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bunnatech.moneysaving&hl=en&gl=US”>ብር እንዴት ገንዘብ መቆጠብ እንደሚቻል.

የበጀት እቅድ አሰራር ምሳሌያዊ ማሳያ

አበበች የተባለች አንዲት ሴት ወርሃዊ ገቢዋ 1450.00 ብር ነው ብላችሁ አስቡ። ከሶስት ወራት በኋላ አበበች ባለፉት ወራት ከባንክ የተበደረችው የገንዘብ መጠን በባንኩ ካላት ተቀማጭ ወይም ቁጠባ በ 450 ብር ብልጫ ማሳየቱን ተረዳች። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ብዙ ወጪዎች እያወጣች እንዳልሆነ በማሰቧ ይኼ እንደተከሰተ አልገባትም። ሆኖም ግን አንዴ ወጪዎቻችሁን በጽሁፍ በዝርዝር ማስፈር ስትጀምሩ በእርግጥም ገቢያችሁ ከሚፈቅድላችሁ በላይ ወጪዎችን እያወጣችሁ መሆኑን ወዲያው ትረዳላችሁ።

የወጪ መደብ/ርእስወርሃዊ ወጪዎች በገንዘብ
ቤት ኪራይ750
ግሮሰሪዎች450
ትራንስፖርት150
መዝናኛ250
ጠቅላላ የወጪ ድምር1600

ስለሆነም፣ አበበች በየወሩ ታወጣ የነበረው የገንዘብ መጠን 150.00 ብር ነው። ከሶስት ወራት በኋላም የብድር እዳ መጠኗም ወደ 450.00 ብር ከፍ ብሏል። የገንዘብ አወጣጥ ልማዷን የምትለውጥበት እና የወጪ አወጣጧን አካሄድ የምታስተካክልበት ጊዜ አሁን ነው። በመሆኑም፣ አበበች ገንዘቧን እንዴት ወጪ ማድረግ እንዳለባት ለማወቅ ስለፈለገች አዲስ የበጀት አወጣጥ እቅድ አወጣች። ይህ አዲስ እቅዷም ያለባትን እዳ 450.00 ብር መክፈልን፣አጠቃላይ ወጪዋም ከ 1450.00 ብር እንዳይበልጥ ማድረግን ያካትታል።

የወጪ መደብ/ርእስወርሃዊ ወጪዎች በገንዘብ
ቤት ኪራይ750
ግሮሰሪዎች350
ትራንስፖርት150
መዝናኛ125
ለእዳ ክፍ75
ጠቅላላ የወጪ ድምር1450

ከ6 ወራት በኋላ አበበች ዕዳዋን ሙሉ በሙሉ ከፈለች። አዲሱን በጀትዋንም አትቀይርም። በየወርይ 75 ብር ለቁጠባ ትመድባለች። ከዚህም ላይ 50 ብሩን በቁጠባ አካውንቷ ውስጥ፣ 25 ብሩን ደግሞ በኢንቨስትመንት አካውንቷ ውስጥ ታስገባለች።

ፈጣን ወይም አውቶማቲክ በጀት

ገንዘባቸውን ሁሉ በአንድ አካውንት ብቻ መቀበል በብዙ ሰዎች ዘንድ የተለመደ ነው። እነዚህ ሰዎች ወጪዎቻቸውን በደንብ አያውቁም። ስለዚህ፣ ብዙ የቁጠባ ገንዘብ ተቀማጮች ወይም የባንክ ሂሳቦች ወይም አካውንቶች መኖራቸው ጠቃሚ ነው። ለምሳሌ፣ ቋሚ ሂሳቦችን ከወጪዎች መለየቱ ብልህነት ሊሆን ይችላል። የተወሰነውን መጠን በየሳምንቱ ወይም በወር አንድ ጊዜ ወደ አንድ የተለየ የወጪ አካውንት ወይም ሂሳብ ማስተላለፍ በዚህ ሂደት ውስጥ ሊረዳ ይችላል። ይህ ለግሮሰሪዎች ብዙ ገንዘብ እንዳታወጡ ማረጋገጫችሁ ሊሆን ይችላል። ለልብስ እና ለመዝናኛ ወጪዎችም ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል።

የበጀት ደንቦችን ማዘጋጀት

የበጀት እቅድ ማሰናዳት እና የፋይናንሺያል ወይም የገንዘብ ወጪዎችን በደንብ ማጤን አንድ ነገር ነው። በጀት ማውጣት ደግሞ ሌላ ነገር ነው። ይህ እናንተ ራሳችሁ በምታዘጋጇቸው የግል የበጀት ደንቦች በቀላሉ ሊከናወን ይችላል።

ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ ከሚውሉት ምርጥ የበጀት ደንቦች አንዱ 50/30/20 የሚባለው ነው። ይህ እንዴት ነው የሚሰራው? ይህ ቀላል የበጀት እቅድ ከገቢያችሁ 50% በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ወጪዎች፣ 30% አስፈላጊ ለሆኑ ወጪዎች 20% ደግሞ ለቁጠባ ተቀማጫችሁ እንድታወጡ የሚያበረታታችሁ ነው። ይህ የበጀት ደንብ በጣም ጠቃሚና ወሳኝ ነው ምክንያቱም የገቢያችሁን 1/5 (አንድ አምስተኛ) ለቁጠባ እንድታውሉ ያስችላችኋል። ስለዚህ ጠቃሚ ጉዳይ የበለጠ ለማወቅ የበጀት ደንብን መመልከት ትችላላችሁ።

ልዩ ልዩ የበጀት ስልቶች ወይም ታክቲኮች

በበጀት መኖር ማለት በህይወት መደሰትን ማቆም አለባችሁ ማለት አይደለም። በበጀት መኖር የፋይናንስ ህይወታችሁ ላይ አጠቃላይ የሆነ እይታ መኖር ማለት ነው። ገንዘባችሁን በምታወጡበት ነገር ላይ ቁጥጥር ለማድረግ መቻል ማለትም ነው።

በበጀት እቅድ መሰረት መኖራችሁ ከእገዛው ይልቅ ገዳቢነቱ ከበዛባችሁ ድጋሚ ሌላ ስልት ወይም ታክቲክ መሞከር ትችላላችሁ። አግባብነት ባለው አመለካከት እና ትእግስት፣ ዓላማዎቻችሁን ሁሉ ማሳካት እንደምትችሉ እርግጠኛ መሆን ትችላላችሁ።