በዩቲዩብ ቻነል ላይ እንዴት ገንዘብ መስራት እንደሚቻል ማሳያ ሃሳቦች (YouTube)

ትርጉሞች:
en_USswuk

በየነ መረብ ወይም ኢንተርኔት በራሱ አንድ ዓለም ነው ብንል ማጋነን አይሆንም። አንድ ሰው ኢንተርኔትን በመጠቀም መገብየት፣ መማር፣ መዝናናት እንዲሁም መሰረታዊ በሆነ ሁኔታ ሁሉንም የህይወት ዘርፎቹን ሊኖርበት ይችላል። ትምህርትም ሆነ ገቢ ለማግኘት ሰዎችን እያገለገሉ ካሉት የዲጂታል መድረኮች ወይም ፕላትፎርሞች መካከል አንዱ [ዩቲዩብ] ነው። ዩቲዩብ እ.ኤ.አ. ከ 2005 ዓ.ም. ከተፈጠረበትና በቀጣዩ 2006 ዓ.ም. ጎግል የተሰኘው ዋነኛ የመረጃ ቴክኖሎጂ ኩባንያ በባለቤትነት ከያዘው ጊዜ አንስቶ ከጎግል በመከተል በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለተኛው እጅግ ታዋቂ የዲጂታል ተቋም ወይም setup ለመሆን በቅቷል።

በእያንዳንዱ ደቂቃ ከ 500 ሰአት በላይ ርዝመት ያላቸው ቪዲዮዎች በዩቲዩብ ላይ ይጫናሉ። ከዚህ በተጨማሪም፣ በአሃዝ ወደ 1.9 ቢሊዮን አካባቢ የሚደርሱ ተጠቃሚዎች በየወሩ የዩቲዩብ ቻነልን ይጎበኛሉ። አንዳንድ ሰዎች ይኽን ቻነል ወይም ሳይት እንደ መረጃ የማግኛ መላ የሚጠቀሙበት ሲሆን ሌሎች ደግሞ እንደ ገቢ የማግኛ አድርገው ይገለገሉበታል። በራሳቸው ጥረት ዝነኛ ለመሆን የበቁ አንዳንድ ዩቲዩበሮች ከዚህ ዲጂታል ፕላትፎርም በየዓመቱ እስከ 20 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ገቢ ለመሰብሰብ ችለዋል። እናንተም እንግዲህ የዚህ የዩቲዩብ ዓለም አካል መሆን የምትሹ ከሆነ፣ ይኽ ጽሁፍ በዩቲዩብ ቻነል ላይ እንዴት ገንዘብ መስራት እንደሚቻል ማሳያ ሃሳቦችን በጣም ጠቃሚና ዘርዘር ባለ ሁኔታ ያሳያችኋል።

make money on youtube
በ2020 ከፍተኛ 5 የዩቲዩብ ገቢዎች.

ካለ ምንም አይነት ማስታወቂያ በዩቲዩብ ላይ ገንዘብ መስራት ይቻላልን?ማስታወቂያዎችን በመጠቀም በዩቲዩብ ላይ ገንዘብ የሚያገኙ በርካታ ዩቲዩበሮች አሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ይህ ጽሁፍ እንደሚያመለክተን በዩቲዩብ ቻነሎች ላይ ማስታወቂያዎችን መለጠፍ ብቸኛው የገንዘብ ማግኛ መንገድ አይደለም።

ምርቶቻችሁን መሸጥ

ዩቲዩብን እንደ ገንዘብ ማግኛ መላ ከመገልገል አኳያ፣ ሁለት አይነት ቡድኖች አሉ፡ አንደኛውና ስራ ፈጣሪ ወይም አንተርፕረነር ብለን ልንጠራው የምንችለው ቡድን የዩቲዩብ ፕላትፎርምን ለንግድ ስራው ገበያና ገዢ ለማግኘት የሚጠቀምበት ሲሆን ሌላኝውና ይዘት ፈጣሪ ወይም በእንግሊዘኛው ኮንቴት ክሪኤተር ብለን ልንጠራው የምንችለው ቡድን ታዋቂነቱን በመጠቀም ዩቲዩብ ላይ አትራፊ ስራዎችን የሚሰራ ነው።

በዩቲዩብ ላይ ምርቶቻችሁን በመሸጥ ጥሩ ገንዘብ ለመስራት በቅድሚያ የሚከተሉትን ማከናወን ይገባችኋል:

  • ቻነላችሁን በብቃትና በትክክል የሚወክል እና ታሳቢ ካዳረጋችኋቸው አድማጭና ተመልካቾቻችሁ ጋር ይበልጥ ለመገናኘት የሚረዳችሁን ምርት ንደፉ ወይም ዲዛይን አድርጉ። በአንድ ጊዜ ብዙ ምርቶችን በማስተዋወቅ ወይም በመለጠፍ ተመልካቾቻችሁን ማጨናነቅ የለባችሁም።
  • ታማኝ የሆኑ ወይም አስተማማኝ አቅራቢዎችን ወይም አምራቾችን ለዩ።
  • እንደ መደብር ሆኖ ሊያገለግላችሁ የሚችል ድረ ገጽ ወይም በእንግሊዘኛው ዌብሳይት ፍጠሩ። ለተመልካቾቻሁ በቀላሉ ተደራሽ ለመሆን ደረ ገጹን ከቪዲዮዎቻችሁ ጋር አገናኙ ወይም ሊንክ አድርጉት።
  • በምርት ግብይት ሼልፍ ፊቸሮች ተጠቃሚ ለመሆን በዩቲዩብ ፓርተነር ፕሮግራም ላይ ተመዝገቡ ወይም ሳይን አፕ አድርጉ።
  • ቪዲዮዎቻችሁን በመጠቀም እና የምርታችሁ ተጠቃሚ የሆኑ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችን በማሳየት ምርታችሁን አስተዋውቁ።

 

ስፖንሰር የተደረጉ ይዘቶችን ማዘጋጀት

አድማጭ ተመልካቾቻችሁን በማስፋት በራሳችሁ ጥረት ታዋቂና ዝነኞች መሆን ትችላላችሁ። ይኽን ደረጃ ከተጎናጸፋችሁ በኋላ ምርቶቻችሁን እንድታስተዋውቁላቸው የሚሹና ክፍያም ሊፋጽሙላችሁ ፈቃደኛ የሚሆኑ ታዋቂ ኩባንያ እና አምራቾችን ወደ እናንተ ለመሳብ መንገዱ ቀላልና ቀና ይሆናል። በዚህ አይነት መልኩ የምታገኟቸውን ገቢዎች ከማናቸውም ጋር መካፈል ስለማያስፈልጋችሁ በእርግጥም በዩቲዩብ ላይ ገንዘብ መስራት ከሚያስችሉ ውጤታማ መንገዶች መካከል ይኼ አንዱ ነው። ይኽን ስታደርጉም በቻነላችሁ ላይ እናንተን የሚመጥንና የራሳችሁ ብቻ የሆነ መለያ መለጠፋችሁን ማረጋገጥ አለባችሁ።

 

ይዘቶቻችሁን ለመገናኛ ብዙሃን መሸጥ

ያዘጋጃችኋቸውን የቪዲዮ ይዘቶች ለአገር ውስጥም ሆነ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ወይም ሜዲያዎች መሸጥ ትችላላችሁ። እንደ ኔትፍሊክስ, እና ፕራይም ቪዲዮ የመሰሉ አለም አቀፋዊ ተደራሽነት ያላቸው ታዋቂ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሁሌም ቢሆን አዳዲስ እና ትኩስ ይዘቶችን ለተመልካቾቻቸው ለማቅረብ አሰሳ ላይ መሆናቸውን መረዳት ይገባል። እንደ Jukinmedia፣ ባሉ የቪዲዮ መብቶች የገበያ ስፍራዎች አማካኝነት ቪዲዮዎቻችሁ በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ወደ ሆኑ ለአብነትም ሲኤንኤን፣ ቢቢሲ፣ እና ኤምቲቪ ለመሳሰሉ ጣቢያዎ በቀላሉ ሊደርሱ ይችላሉ። እናንተም ጊዜ ወስዳችሁ በአገራችሁ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉና ይዘቶቻችሁን ሊገዙ የሚችሉትን የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶችን መፈለግ ይኖርባችኋል።

ከማህበረሰብ ገንዘብ መሰብሰብ ወይም ክራውድፈንዲንግ

የዩቲዩብን ኩባንያ ፈቃድ እና ማረጋገጫ ያገኙ የተለያዩ ከማህበረሰብ ገንዘብ የመሰብሰቢያ ገጾች ወይም ሳይቶች አሉ። የገንዘብ ማሰባሰቡ ተግባር ለአንድ ጊዜ ብቻ ለፕሮጀክት ማስፈጸሚያና በዘመቻ መልክ ሊከናወን ወይም ደግሞ ለተከታታይ ጊዜያት የሚደረግ ጥሪ ሊሆን ይችላል። ከማህበረሰብ ገንዘብ ማሰባሰብያ ወይም ክራውድፈንዲንግ ዘመቻችሁን ለማስተዋወቅ የዩቲዩብ ቻነላችሁን እና ሌሎች የማህበራዊ መገናኛ ወይም ሶሻል ሜዲያ ፕላትፎርሞችን ተጠቀሙ። በንቃት ተሳታፊ የሚሆኑ አድማጭ ተመልካቾችን መገንባት ወይም ማግኘት ለዚህ በዩቲዩብ ገንዘብ ለመስራት የሚያስችለውን መላ ስኬታማ ከሚያደርጉት ስልቶች አንዱ ነው።

በዓለም ዙሪያ ከሰዎች ገነዘብ ለማሰባሰብ (ክራውድፈንዲንግ) ጥቅም ላይ ከሚውሉ ፕላትፎርሞች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

 

በዩቲዩብ የፓርትነር ፕሮግራም ላይ መመዝገብ

በአሁኑ ወቅት፣ በዩቲዩብ የፓርትነር ፕሮግራም ላይ ድጋፍ ከሚደረግላቸው አገራት አንደኛዋ አይደለችም። ሆኖም እናንተ የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን አካውንታችሁን በፕሮግራሙ ድጋፍ ከሚደረግላቸው አገራት መካከል በአንዱ ማውጣት አለባችሁ። ኢትዮጵያ ውስጥ ቪዲዮ የምታዘጋጁ ከሆነ፣ እዚህላይ ከተዘረዘሩት በፕሮግራሙ ድጋፍ ከሚደረግላቸው አገራት መካከል በአንደኛው ውስጥ ኑሮውን ካደረገ አንድ ሰው ጋር በመጣመር ችግሩን መፍታት ትችላላችሁ።

ቻነላችሁን ገንዘብ ማግኛ ለማድረግ የግድ የዩቲዩብ ፓርትነር መሆን አያስፈልጋችሁም። እናንተ የተመልካቾቻችሁን ቁጥር ብዛት መጨመር ላይ በትኩረት ስትሰሩ፣ የዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም በዩቲዩብ ላይ ገንዘብ መስራት የሚያስችላችሁን መሰረት ያሰፋላችኋል። የዩቲዩብ ፓርትነር ለመሆን፣ በዝርዝር የሰፈሩትን ፖሊሲዎች መቀበልና መፈጸም አለባችሁ። ይኽን ከፈጸማችሁም በኋላ፣ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጨምሮ ሊሻሩ በማይችሉ ፊቸሮች አማካኝነት ገንዘብ ለመስራት ትችላላችሁ:

  • Super chat and stickers (ሱፐር ቻት እና ስቲከርስ). በቻት ስትሪም ለሚለጥፏቸው ጽሁፎች (ቴክስቶች) ተመልካቾች ክፍያ ይከፍላሉ።
  • Channel memberships (የቻነል አባልነት). የዩቲዩብ ቻነላችሁ አባላት (members) ከእናንተ ቻነሎች የተለየ ስጦታዎች ወይም ሽልማቶች (offers) ለማግኘት ወርሃዊ ክፍያን ይፈጽማሉ።
  • YouTube premium revenue (የዩቲዩብ ፕሪምየም ገቢ) . ለዩቲዩብ ፕሪምየም የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች (subscribers) ቪዲዮዎቻችሁን በተመለከቱ ቁጥር ከሚከፍሉት ክፍያ ላይ የተወሰነ የክፍያ ድርሻ ይኖራችኋል።
  • Advertising revenue (የማስታወቂያ ገቢ). ይኽ ከቪዲዮ፣ በቻነሉ ላይ በቋሚነት ወይም በጊዜያዊነት ከሚለጠፉ እንዲሁም ከሚተላለፉ ማስታወቂያዎች የሚገኙ ገቢዎችን ይጨምራል።
  • Merchandise shelf (የሸቀጦች መደርደሪያ). ይኽ ገጽታ ወይም ፊቸር ተከታቶቻችሁ በገጾቻችሁ ወይም በፔጆቻችሁ ላይ የተለጠፉትን ምርቶች ለመፈለግ እና ለመግዛት ያስችላቸዋል።

 

ብዙ ገንዘብ ሊያስገኙ የሚችሉት የዩቲዩብ ቻነል አይነቶች ምንድን ናቸው? ብዙ ገንዘብ የሚያስገኙት ቻነሎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡

  • በኦንላይን ገንዘብ መስራት (Make Money Online)
  • የህይወት ዘይቤ (Lifestyle)
  • ገንዘብ ነክ ጉዳዮች እና መዋዕለ ነዋይ ስለማፍሰስ (Finance and Investing)
  • ትምህርታዊ ቪዲዮዎች (Educational Videos)
  • ፋሽን እና አልባሳት (Fashion and Clothing)
  • ዜና ዘገባ እና ኮሜዲ ነክ ጉዳዮች (News and Comedy)

በዩቲዩብ ላይ ብዙ እይታን (ተመልካችን) እንዴት ማግኘት ወይም ማፍራት እንደሚቻል አመላካች ነጥቦች

በዩቲዩብ ላይ ገንዘብ ለመስራት ወይም ለማግኘት እንደሚቻል መሰረታዊው ጉዳይ የበርካታ ተመልካቾች እና ተመዝጋቢዎች (ወይም ሰብስክራይበርስ) መኖር ነው። ገቢው የተገኘው ከዩቲዩብ ከእይታዎች (ተመልካቾች) ወይም ከስፖንሰርሺፕ ስምምነቶች ይሁንም አይሁንም፣ ብዙ ተከታዮች ያሏቸው ዩቲዩበሮች ከዚህ ዲጂታል መድረክ ወይም ፕላትፎርም ጥሩ ኑሮን ለመምራት የሚያስችል ገንዘብን ለማግኘት ችለዋል።

በአንድ የቪዲዮ ክሊፕ አማካኝነት ኢላማ ያደረጋችሁት የእይታ ወይም የተመልካች ቁጥር ላይ ለመድረስ ስታስቡ የሚከተሉትን ስልቶች ወይም ስትራተጂዎች ልታጤኑ ወይም ከግምት ልታስገቡ ይገባል፡

  • ደጋፊዎቻችሁ በቻነላችሁ ላይ እንዲመዘገቡ በተደጋጋሚ ንገሯቸው፣ ጠይቋቸው። ተመዝጋቢዎች (ወይም ሰብስክራይበርስ) ወደፊት የምትለቋቸውን ይዘቶች የማየት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው።
  • ተመልካቾቻችሁን ምን ምን አይነት ይዘቶች እንዲዘጋጁላቸው እንደሚፈልጉ ሃሳባቸውን እንዲያቀርቡላችሁ ጠይቋቸው።
  • በአውቶ-ፕሌይ ሃሳብ ተጠቃሚ ለመሆን አንድ የምታስተላልፉት የሙዚቃ መዝገብ ወይም ፕሌይሊስት አዘጋጁ።
  • ስለማናቸውም ነገር እና ስለሁሉም ጉዳዮች ይዘቶችን ከማዘጋጀት ይልቅ በአንድ የተለየ ገበያ ወይም ምርት ላይ አተኩራችሁ ይዘቶችን አዘጋጁ።
  • ለቪዲዮ ርዕሶች እና ዝርዝር መግለጫዎች/ማብራሪያዎች ተገቢ የሆኑ ቁልፍ ቃላቶችን ተጠቀሙ።
  • አስደሳች፣ አይን የሚይዙና የሚስቡ የግራፊክስ ምስሎችን ተጠቀሙ።
  • ከተከታዮቻችሁ እና ከሌሎች ዩቲዩበሮች ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር ከሁሉም ጋር ተግባቢ ለመሆን ሞክሩ።
  • የዩቲዩብ ቻነላችሁን የተደራሽነት መጠን ለመጨመር እንደ ኢንስታግራም፣ ፌስቡክ እና ትዊተርን ያሉ ሌሎች ማህበራዊ መገናኛ ፕላትፎርሞችን ተጠቀሙ።

 

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሆነ ተምልካች ያላቸው የዩቲዩብ ቪዲዮ ቻነሎች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡

ማጠቃለያ

ዲጂታል መድረኮች ወይም ፕላትፎርሞች ኢትዮጵያንም ሆነ መላው ዓለምን በከፍተኛ ደረጃ ለውጠውታል። ዩቲዩብ አንድ ሰው የተለያዩ መረጃዎችን የሚያገኝበት እና አርኪ ስራን የሚገነባበት አንደኛው መንገድ ከሆነ ሰነባበተ። በእርግጥ በዩቲዩብ ላይ በኦንላይን ገንዘብ መስራት የሚቻልባቸው የተለያዩ መንገዶች በዩቲዩብ ላይ አሉ። ዋናው ወይም መሰረታዊው ነገር ኢላማ ላደረጋችኋቸው ተከታዮቻችሁ የሚስብና አስደሳች ይዘትን በተከታታይ መፍጠር ወይም ማዘጋጀት ነው። ብዙ ተመልካቾችን ለማግኘት እና ታዋቂ ተፅዕኖ ፈጣሪ ለመሆን ተጨማሪ ስልቶችን መጠቀም እንደሚገባችሁም ማስተዋል ይገባል።